Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ራስን ባለመውደድ ሕይወት የአምላክን አርአያ ማሳየት (መምሰል)

    በብዙ ያየለብንና ከአምላክም የሚለየን ደግሞ እጅግ ብዙ የሆኑ መንፈሳዊ ውዘግቦችን (ሽብሮችን) የሚፈጥርብን ራስን መውድድ ነው፡፡ ራስን በመካድ ካልሆነ በስተቀር ወደ አምላክ ለመመለስ አይቻልም፡፡ በራሳችን ምንም ለማድረግ አንችልም፤ ነገር ግን በማያበረታን አምላክ አማካይነት ለሌሎች መልካም ለማድረግ ለመኖር እንችላለን፤ በዚህም መንገድ ራስን ከመውደድ ክፋት ልንርቅ እንችላለን፡፡ ፍላገተችንን ለመግለጽና ጠቃሚ የሆነ ራስን የለ መውደድ ሕይወት በመኖር ሁሉን ላምላክ ቀድሰን እንሰጥ ዘንድ ወደ አረማውያን አገሮች መሔድ አያስፈልገንም፡፡ ይህንኑ በቤት ክበብ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አብረናቸው ባለንበትና ሥራ በመንሰራባቸው መኻከል ማድረግ ይገባናል፡፡ ራስ የሚካድበትና የሚገዛበት ልክ በተለመደው የሕይወት አረማመድ ውስጥ ነው፡፡ ጳውሎስ ‹ዕለት ዕለት እሞታለሁ› አለ፡፡ አሸናፊዎች የማያደርገን፤ በትንሹ የሕይወት ተግባር በራስ ዘንድ ዕለት ዕለት መሞት ነው፡፡ ለሌሎች መልካም ለማድረግ ፍላጎት ካለን ራስን መርሳት አለብን በብዙዎች ዘንድ ሌሎችን የመውደድ ጉድለት ያለባቸው መሆኑ የተረገገጠ ነው፡፡ ተግባራቸውን በታማኝነት በማድረግ ፈንታ የራሳቸውን ደስታ ይሻሉ ፡፡CCh 140.2

    በሰማይ ማንም ስለ ራስ አያስብም፤ ወይም የራሳቸውን ደስታ አይሹም፤ ነገር ግን ሁሉም ንጹህ ከሆነው ዓይነተኛ ፍቅር የተነሣ በአካባቢያቸው ያሉትን የሰማያዊ ፍጥረቶችን ደስታ ይሻሉ በአዲሲቱ ምድር የሰማያዊን ማኅበርነት ለመደሰት ብንፈልግ፤ እዚህ በሰማያዊ ፐሪንሲፐል መተዳደር /መገዛት/ አለብን፡፡ የተረጋገጠው የማይሳሳት ምሳሌ እያለን፤ ተሳሳቾች ሟቾች ከሆኑት በራሳችን መኻከል ካሉት ጋር ራሳችንን ማመዛዘን በብዙ እንዳለ ታየኝ በዓለም ወይንም በሰዎች ሐሳቦች ወይም እውነትን ከመቀበላችን በፊት በነበርንበት ሁኔታ ራሳችንን መለካት /ማመዛን/ የለብንም፡፡ ነገር ግን በዓለም ሃይማኖታችንና ሥራችን አሁን እንዲሁ እንዳሉ፤ የክርስቶስ ተከተዮች ነን ካልን አንስቶ እርምጃችን ዘወትር ወደፊትና ወደ ላይ የመንገሰግስ ቢሆን ኑሮ ከማሆኑበት ሁኔታ ጋር ሊመዛዘኑ ይገባል፡፡ ይህ ብቻ ሊደረግ የሚቻል ደህና የሆነ ማመዛዘኛ ነው፡፡ በሌላው ሁሉ ራስን ማታለል ይሆናል፡፡ የግብረ ገብ /የሞራል/ ጠባይን መንፈሳዊው ያምላክ ሕዝብ ሁናቴ ከተሰጣቸው በረከቶች መብቶችና ብርሃን የማይስማማ ከሆነ በሚዛን ይመዘኑና መላአክት የቀለሉ የሚል ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡CCh 141.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents