Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክርስቲያናዊ ቅንነት፡፡

    በንግድ ሥራ ሁሉ ጽኑ ታማኝ ሁን፡፡ ምንም ብትፈተን በትንሽም ነገር ቢሆን አትታለል ወይም ከእውነት አትራቅ፡፡ በየጊዜያቱ የተፈጥሮ ሐሳብ ከትክክለኛው (ከቀናው)የመታዘዝ ጎዳና ለማራቅ ፈተና ያመታብህ ይሆናል ነገር ግን ከፕሪንሲፕል አንዲት የጸጉር ቅንጣት እንኳ አትራቅ፡፡ በማንኛውም ነገር ምንም እንደምታደርግ ንግግር ብታደርግና በኋላ ለራስህ ጉዳት ሁኖብህ ለሌሎች ሞገስ ማድረግህን ብታገኝ አንዲት የጸጉር ቅንጣት ከፕሪንሲፕል አትራቅ፡፡ የተስማማህበትን አካሒደው (ግፋበት)፡፡ 2CG154;CCh 157.2

    መጽሐፍ ቅዱስ አሰትን አድራጎት ያለመታመንን ሁሉ በብርቱ አነጋገር ይነቅፈዋል፡፡ እውነትና (የቀናውና) ስሕተት በግልጽ ይነገራሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በጠላት ሥፍራ ላይ ራሳቸውን እንዳኖሩ ታየኝ፡፡ ስሜቶቻቸው በሚያስፈራ አኳኋን እስኪደነዝዙ ድረስ ለፈተናዎቹ ተበግረዋል ተንኮሎቱንም ተከትለዋል፡፡ ገንዘብ የማትረፍና የኪሳራ ጉዳይ ሲገባበት ከእውነት ትንሽ መራቅ ከአምላክም ፍላጎቶች ትንሽ መለየት ከሁሉም እጅግ ኃጢአተኛ አያሰኝም ተብሎ ታስቦአል፡፡ ነገር ግን በሚልዮኔሮች ወይም በአውራ መንገዶች ባለው ለማኝ ኃጢአት ቢደረግም ኃጢአት ነው፡፡ በአሰት በማስመስሰል ንብረትን የሚያገኙ በነፍሳቸው ላይ ኩነኔ ማምጣታቸው ነው፡፡ በማታለልና በማሳት የሚገኘው ሁሉ ለተቀባዩ እርግማን ብቻ ይሆንበታል፡፡ 34T311;CCh 157.3

    አሰትን የሚናገር ወይም የሚያታልል የራሱን ከበሬታ ያጣል፡፡ እግዚአብሔር እንደሚያየውና የሚያደርገውን የንግድ ሥራ ሁሉ እንደሚያውቅ ቅዱሳ ን መላእክትም ሐሳቦቹን እንደሚመዝኑና ቃሎቹን እንደሚያዳምጡ የሚያገኘውም ዋጋ እንደሥራዎቹ መሆኑን አያውቅም ይሆናል፡፡ ነገር ግን የስሕተት አደራጎቱን ከሰብዓዊና ከመለኮታዊ ፈተሻ (ምርመራ) ለመሠወር የሚቻል ቢሆን ኑሮ በውነቱ ራሱ የሚያውቀው በመሆኑ ሐሳቡንና ጠባዩን ማዋረዱ ነው፡፡ አንድ አድራጎት ጠባይን የሚወስን አይደለም ነገር ግን ማገጃው ይሰበርና ቀጥሎ ያለውም ፈተና በይበልጥ ዝግጁ ሆኖ ይታደማል በመጨረሻም በንግድ ከእውነት የመራቅና የአለመታመን ልምድ እስኪፈጠርና ሰውየውም ለመታመን እስከማይቻል ድረስ፡፡ 45T396;CCh 157.4

    እግዚአብሔር ሰዎች በአገልግሎቱ በሰንደቅ ዓላማው በታች ሆነው ምላሳቸው የውሸት ምክንት እንዳይናገር በጥብቅ ታማኞች በጠባይም የማነቀፉ እንዲሆኑ ይፈልጋቸዋል፡፡ ምላስ እውነተኛ መሆን አለበት ዓይኖችም እውነተኞች መሆን አለባቸው አድራጎቶችም በምሉ በፍጹምም እግዚአብሔር ሊቀበላቸው (ሊመሰከርላቸው) እንደሚችል መሆን አለባቸው፡፡ ‹‹ሥራህን አውቃለሁ›› ሲል በጥብቅ በሚናገረው ቅዱስ አምላክ ፊት እንኖራለን፡፡ መለኮታዊ ዓይን ዘወትር በኛ ላይ ነው፡፡ አንዲት የግፍ አድራጎትን ከአምላክ ልንሠውር አንችልም፡፡ ለአድረጎታችን ሁሉ ያምላክ ምሥክርነት እውነት ነው ይህንኑ ጥቂቶች ብቻ ይገነዘቡታል፡፡CCh 158.1