Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    አምላክ ለልጆቹ አሳቢ መሆኑ፡፡

    ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔርና በክርስቶስ መኻከል ስላለው ዝምድና ገልጸው ያመለክታሉ ስለ እያንዳንዳቸውም መለኮትነትና አካላትነት በግልጽ ያስረዳሉ፡፡CCh 136.6

    እግዚአብሔር የክርስቶስ አባት ነው ክርስቶስም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ለክርስቶስ ከፍ ያለ ሥራ (ማዕረግ) ተሰጥቶታል፡፡ ከአብ ጋር እኩል ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ምክሮች ሁሉ ለልጁ ግልጽ ናቸው፡፡CCh 137.1

    ይህ ኅብረት በዮሐንስ ((ኛ ምዕራፍ ክርስቶስ ለቀመዛሙርቱ ባቀረበው ጸሎት ደግሞ ተገልጻ(ል፡፡CCh 137.2

    ‹‹ስለዚህም ብቻ የምለምን አይደለሁም፡፡ ደግሞ በቃላቸውም ስለሚያምኑብኝ እንጂ፡፡ ሁሉ አንድ እንዲሆኑ፡፡ አንተ በኔ እንዳለህ አባት ሆይ እኔም ባንተ፡፡ እርሳቸውም ደግሞ አንድ ይሆኑ ዘንድ በኛ፡፡ ዓለም ያምን ዘንድ አንተ እንደ ላክኸኝ፡፡ እኔም የሰጠኸኝን ምስጋና ሰጠኋቸው አንድ ይሆኑ ዘንድ እኛ አንድ እንደ ሆነ፡፡ እኔ በርሳቸው አንተም በኔ፡፡ ባንድ የተፈጸሙ ይሆን ዘንድ፡፡ ዓለምም ያውቅ ዘንድ እንደ ላክኸኝ እርሳቸውንም እንደ ወደድኻቸው እኔን እንደ ወደድኸኝ››፡፡ (ዮሐንስ ((፣ (---(()፡፡CCh 137.3

    ግሩም አነጋገር ነው! በክርስቶስና በደቀመዛሙቱ መኻከል ያለው ኅብረት ሁለት አካላት ያላቸው መሆናቸውን የሚደመስስ አይደለም፡፡ እነዙ በሐሳብ በእቅድ፣ በባሕርይ አንድ ሲሆኑ በአካል ግን አንድ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ክርስቶስ አንድ መሆናቸው በእንደዚህ ነው፡፡ . . .CCh 137.4

    አምላካችን ሰማይና ምድርን በትእዛዙ ሥር አለው፣ የምንፈልገውንም ያውቃል፡፡ በፊታችን ትንሽ መንገድ ብቻ ልናይ እንችላለን፡፡ ‹‹ሁሉ ግን የተከፈተ የተገለጠም ነው ባኑ ፊት፡፡ ከርሱም ጋር ነው ነገር ያለነ››፡፡ (ዕብ ( (() ፡፡ በምድር ሽብሮች በላይ እርሱ የተቀዳጀ ሁኖ በዙፋን ላይ ቀመጣል ሁሉ ነገሮች ለመኮታዊ ምርመራ ግልጽ ናቸው ከታላቁ ጸጥተኛው ዘላለማዊነት አንስቶ ቸርነቱ የተሻለ መሆኑን የሚያየውን ያዛል፡፡CCh 137.5

    አብ ልብ ሳያደርጋት አንዲቷ ድንቢጥ እንኳ ወደ መሬት አትወድቅም፡፡ ሰይጣን በአምላክ ላይ ያለው ጥላቻ ድዳዎቹን ፍጥረቶች እንኳ ለማጥፋት እንዲደሰት ይመራዋል፡፡ ወፎች በደስታ መዝሙሮቻቸው ያስደስቱን ዘንድ የሚጠበቁት በአምላክ የጥበቃ ጥንቃቄው አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እርሱ ደንቢጥዋን እንኳ አይረሳም፡፡ ‹‹እንግዲህም አትፍሩ፡፡ እላንት ከብዙ ድንቢጥ ትሻላላችሁና›› (ማቴ ( (()፡፡(CCh 137.6