Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ማንም ጠቃሚነት ያለው ለመሆን ለመንፈስ ቅዱስ መገዛት (ራስን መስጠት) ይኖርበታል፡፡

    እግዚአብሔር አፊታችን ያለውን ሥራ በገዛ ኃይላችን እናደርግ ዘንድ አይጤቀንሞ፡፡ አቅሞቻችን ብቁዎች ላልሆኑበት አደጋዎች ሁሉ መለኮታዊ እርዳታ አሰናድቶልናል፡፡ ተስፋችንንና ማረጋገጫችንን ሊያጠነክር ሐሳባችንን ለማብራትና ልባችንን ያነጻልን ዘንድ በማንኛውም ችግር ሁሉ ሊረዳን መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል፡፡CCh 161.2

    ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑ የተለወጠች አካል በሰማ ብርሃን የበራች የአማኑኤል ክብር ያላት እንድትሆን መሰናዶ (ዘዴ) አድርጎአል ክርስቲያን ሁሉ በመንፈሳዊ የብርሃንና የሰላም አካባቢነት እንዲከበብ ሐሳቡ ነው፡፡ ራስን አስወግዶ በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንዲሰራበት ክፍል ለሚያደርግለትና ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕይወት የሚኖር ለጠቃሚነቱ ወሰን የለውም፡፡CCh 161.3

    በጴንጤቆስጤ ቀን የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ውጤቱ ምን ነበር( ስለ ተነሳው መድኃኒታችን የተነገረው የደስታ ምስራች በሚኖሩበት ዓለም እስከ መጨረሻዎቹ ወሰኖች ድረስ ደረሰ (ተነዛ)፡፡ የደቀመዛሙርት ልቦች እንዲህ በተመላ በጠለቀ እንዲህም በተትረፈረፈው ቸርነት ተመልተው ወደ ምድር ዳርቻዎች ሔደው ‹‹እኔ ግን አልመካም በጌታችን በየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር›› እስከ ማለት አስገደዳቸው፡፡ (ገላትያ ( (()፡፤ በየሱስ እንዳለው እውነቱን ሲናገሩ ልቦች ለመልእክቱ ኃይል ተገዙ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሁሉ አቅጣጫዎች አማኞች ወደ ርስዋ ሲጎርፉ አየች፡፡ ወደ ኋላ ያፈገፈጉት እንደገና ተመለሱ፡፡ ኃጢአተኞች የታላቁን ዋጋ ዕንቁ በመሻት ከክርስቲያኖች ጋር ተባበሩ፡፡ የወንጌል ታላቅ ተቃዋሚዎች የነበሩ አርበኞቹ ሆኑ፡፡ ትንቢት ተፈጸመ ደካማው ‹‹ውንደ ዳዊት›› ይሆናል የዳዊትም ቤት ‹‹እንደ እግዚአብሔር መልአክ›› ክርስቲያን ሁሉ በወንድሙ ውስጥ መለኮታዊ የፍቅርና የቸርነት ተመሳሳነት አየበት፡፡ አንድ ሐሳብ አየለ፡፡ አንድ የምኞታቸው ጉዳይ ሌሎችን ሁሉ ዋጠ፡፡ የምዕመናን ምኞት የክርስቶስን ተባይ ተመሳሳይነት መግለጽና ለመንግሥቱ ማስፋፊያ ብቻ መሥራት ሆነ፡፡CCh 161.4

    በውነቱ ለመጀመሪዎቹ ደቀ መዛሙርት እንደነበረው የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ ዛሬ ለኛም ነው፡፡ እግዚአብሔር በጴንጤቆስጤ ቀን የደኅንነትን ቃል ለሰሙት እንደ ሰጣቸው ዛሬም ለወንዶችም ለሴቶችም ከላይ ኃይል ይሰጣዋል፡፡ በዚህ ሰዓት መንፈሱና ጸጋው ለሚፈልጉዋቸውና በቃሉ ለሚበቀሉት ሁሉ ናቸው፡፡ ፫38T19, 20:CCh 161.5