Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፭—ሚስስ ኢ ጂ ኋይትን ሌሎች እንዳወቋት፡፡

    የጌታ መልእክተኛ ስለ መሆንዋ ያልተለመደውን የሚስስ ኋይት ሁኔታ አውቀው አንዳንዶች ምን ዓይነት ሴት ናት እያሉ ጠይቀዋል፡፡ በኛ የሚደርስብን ችግር ደርሶባታልን? ሐብታም ወይንስ ድሀ ነበረች? የፈገግታ ፊት ነበራትን?CCh 16.1

    ሚስስ ኋይት አሳቢ እናት ነበረች፡፡ ጠንቃቃ ባለትዳር ነበረች፡፡ እርሷ ተደሳች፤ እንግዳ ተቀባይ፤ ሰዎቻችንን ብዙ ጊዜ እቤትዋ ስታስተናግዳቸው ነበር፡፡ ረዳት ጐረቤትም ነበረች፡፡ አስተዋይ ሴት፤ ባሕርይዋ የሚያስደስት በጠባይዋና በድምጽዋ (በአነጋገርዋ) ገር ነበረች፡፡ ፊት ማጨምገግ፤ ፈገግታ የሌለው መሆን፤ በሃይማኖትም ደስታ ማጣት በደረሰባት ሁኔታ ውስጥ ሥፍራ አልነበረውም፡፡ ማንም ከርሷ ጋር ሳለ ፍጹም የሆነ ደስታ ይሰማው ነበር፡፡ ምናልባት ከሚስስ ኋይት ጋር ለመተዋወቅ የተሻለው መንገድ በ፲፰፻፶፱ ዓ.ም እ.ኤ.አ ለመጀመሪያው ዓመት ዕለታዊ የመዝገብ ሂሳብን ስትይዝ በነበረችበት ጊዜ እቤትዋ ከርሷ ጋር መነጋገር ነበር፡፡CCh 16.2

    ሚስተርና ሚስስ ኋይት በበትል ክሪክ ዳርቻ በሰፊው መሬት በተሠራው ጎጆ ለአትክልት ቦታ ለጥቂቶች የፍሬ ዛፎች ለላምና ጥቂቶች ዶሮች ማርቢያ ምቹ በሆነው ሥፍራ ይኖሩ እንደነበር እናገኛለን ልጆችም የሚሠሩበትና የሚጫወቱበት ሥፍራ ነበር፡፡ ሚስስ ኋይት በዚህ ጊዜ እድሜዋ ሰላሳ አንድ ዓመት ፤ ኤልደር ኋይትም ሰላሣ ስድስት ዓመቱ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በቤታቸው ሶስት ልጆች ነበሩዋቸው እድሜያቸውም አራት ፤ ዘጠኝና አሥራ ሁለት ዓመት ነበር፡፡CCh 16.3

    በቤታቸው ደግሞ የቤትን ሥራ ትረዳቸው ዘንድ የተቀጠረች አንዲት መልካም ክርስቲያን ልጃገረድ እንደነበረች ደግሞ እናገኛለን፤ ሚስስ ኋይት ብዙ ጊዜ ከቤት ርቃ ትሔድ ስለነበርና በመናገርና በመጻፍ ብዙ ጊዜ ሥራ ይበዛባት ነበርና፡፡ ሆኖም፤ ሚስስ ኋይት ምግብ በመሥራት፤ በማጥዳት፤ በማጠብና በስፌት ሥራ የቤትን ኃላፊነት ይዛ እንደነበረች እናገኛለን፡፡ አንዳንድ ቀንም ለመጻፍ ጸጥታ ሥፍራ ወደ ነበራት ወደ ማተሚያ ቤት ትሔድ ነበር፡፡ ሌላ ቀንም በአትክልት ቦታ ውስጥ አበቦችንና ጐመና ጎመኖችን ስትተክል እናገኛት ነበር፤ አንዳንድ ጊዜም ከጐረቤት ጋር የአበባ አትክልቶችን ሲለዋወጡ እናገኛታለን፡፡ ለቤተሰብዋ የሚያስደስት ለማድረግ እንደ መቻልዋ መጠን ቤትንም የሚደሰቱበት ለማድረግ ቁርጥ ሐሳብ አደረገች፤ ልጆቹ ቤትን እጅግ የሚያስመኝ ሥፍራ መሆኑን ዘወትር ያስቡ ዘንድ ፡፡CCh 16.4

    ሚስስ ኋይት ጠንቃቃ የሆነች ዕቃ ገዢ ነበረች፤ የአድቬንቲስት ጐረቤቶችም ከርሷ ጋር ወደ ሱቅ ሲሔዱ ደስ ይላቸው ነበር፤ የዋጋ ግምት ታውቅ ነበርና፡፡ እናቷ ጥብቅ ሴት ነበረች፤ ሴቶች ልጆችዋንም ብዙ ጠቃሚዎች ትምህርቶች አስተምራቸዋለች፡፡ ጥሩ ዓይነት ዕቃ ከተባለው ይልቅ የበለጠውን መናኛ ሥራ የሆኑ ነገሮች የተወደዱ መሆናቸውን አገኘች፡፡CCh 16.5

    የሰንበት ቀን ለልጆቹ ከሳምንቱ እጅግ የሚያስደስት ቀን ነበር፡፡ ቤተሰባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን አገልገሎት ይገቡ ነበር፤ ኤልደርና ሚስስ ኋይት በኃላፊነታቸው ከመናገር ነጻ ሲሆኑ ቤተሰባቸው በአገልግሎቱ ጊዜ ባንድነት ይቀመጡ ነበር፡፡ ለምሳ በሌሎች ቀናት ያልቀረበው የተመረጠው ምግብ ይቀርባል፤ ቀኑ ጥሩ ቀን የሆነ እንደሆነ ሚስስ ኋይት በጫካ ውስጥ ወይም ወደ ወንዝ አጠገብ ከልጆቹ ጋር ትሔድና የተፈጥሮን ውበት ተመልክተው የተፈጠሩትን የእግዚአብሔርን ሥራዎች ያጠኑ ነበር፡፡ ቀኑ የዝናም ቀን ወይም ብርድ የሆነ እንደሆን፤ ልጆቹን በቤት እሳት ዙሪያ ትሰበስባቸውና ታነብላቸው ነበር፤ ስትጓዝም ሳለች ከዚህም ከዚያም ካጠራቀመቻቸው ነገሮች ብዙ ጊዜም ታነብላቸው ነበር፡፡ ሌሎች ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያነቡት እንዲኖራቸው ከነዚሁ ታሪኮች ጥቂቶቹ በመጽሐፎችዋ ውስጥ ቆይተው ታትመዋል፡፡CCh 16.6

    ሚስስ ኋይት በዚህን ጊዜ እምብዛም በጎ አልነበረችም፤ በቀኑ ውስጥ ብዙ ጊዜ ድክም ይላት ነበር፤ ይህ ግን ለጌታ ሥራ ለመሥራትም ሆነ የቤት ሥራዋን ወደፊት ከማካሔድ አላገዳትም፡፡ ጥቂት ዓመታት ቆይታ እ.ኤ.አ በ፲፰፻፰፫ ዓ.ም በጤንነት ስለ መጠበቅና ለበሽተኞች ስለ መጠንቀቅ ራእይ አየች፡፡ ጠንካራ፤ ጤናማ ሰውነት ለማግኘት፤ የሚገባ ልብስ ስለ መልበስ፤ የሚገባ ምግብ ስለ መብላት፤ የተገባውንም ኤክስርሳይስና (የሰውነት ማጠንከሪያና) ዕረፍት መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን እንደዚሁም በእግዚአብሔር መታመን ጠቃሚ (አስፈላጊ) መሆኑን በራእይ አየች፡፡CCh 17.1

    ስለሚበላው ምግብና የሥጋን ምግብ መብላት ጐጂ መሆኑን ከእግዚአብሔር የተሰጣት ብርሃን፤ ሚስስ ኋይት የሥጋ ምግብ ለጤናና ለብርታት ጠቃሚ ነው ብላ ያሰበችውን የግል ሐሳብዋን ድምስስ አደረገባት፡፡ አእምሮዋን ለማብራራት በተሰጣት የራእዩ ብርሃን መሠረት ለቤተሰብዋ ምግብ ማዘጋጀትን ትረዳ የነበረችውን ልጃገረድ በማዕዱ ላይ ለጤና ለሆኑ ለስላሳ (ቀላል) ምግቦች ብቻ ከእህል ከጐመና ጐመን ከኦቾሊኒ (ነትስ) ከወተት፤ ከስልባቦትና ከእንቁላል የሆኑትን ምግቦች ታቀርብ ዘንድ መከረቻት፡፡ ብዙም ፍሬ ነበራቸው፡፡CCh 17.2

    ቤተሰብ ወደ ማዕድ በቀረቡ ጊዜ ጥሩ የጤና ምግብ ቀርቦ ነበር፤ የሥጋ ምግብ ግን አልቀረበም፡፡ ሚስስ ኋይት ለሥጋ ምግብ ጓጓች፤ ለሌላው ምግብ ግን አይደለም፤ ስለዚህ ለዚሁ ቀላላ (ለስላሳ) ምግብ ተመልሳ አምሮት እስክታገኝ ማዕዱን ትታ ለመሔድ ቁርጥ ሐሳብ አደገች፡፡ በተከታዩም የምግብ ጊዜ ይኸው ሁኔታ ደረሰባት፤ ቀላሉ (ለስላሳው) ምግብ ምንም አላማራትም፡፡ ከዚያ በኋላ እንደገና ወደ ማዕዱ ቀረቡ፡፡ ለጤናና ለብርታት ለእድገትም እጅግ የተሻለው ምግብ በራእይ እንደታያት ቀለል ያሉ የምግብ ዓይነቶች ቀርበው ነበር፡፡ ግን እርሷ ያንኑ የለመደችው ሥጋ አማራት፡፡ ሆኖም ሥጋ ጥሩ ምግብ አለመሆኑን አሁን አወቀች፡፡ ስለዚህ እጆችዋን በሆድዋ ላይ አድርጋ እነዚህን ቃላት እንደነገረችው ትነግረናለች፤ «ዳቦ ለመብላት እስክትችል ድረስ ቆይ»፡፡CCh 17.3

    እንግዲህ ኤሌን ጂ ኋይት ቀላሉን የምግብ ዓይነቶች እስክትደስትባቸው ብዙ ጊዜ አልቆየም፤ ምግብ ሲለወጥላት ጤናዋም ወዲያው እየተሻላት ሔደ፤ በቀረውም ረዘም ባለው የሕይወቷ ጊዜ ባገኘችው መልካም ጤና በጣም ተደሰተችበት፡፡ ስለዚህ ሚስስ ኋይት ሁላችን ያለብን ችግር እንደነበራት ሊታይ ይቻላል፡፡ ሁላችን ድል መንሳት እንደሚገባን፤ በደረሰባት ሁኔታ በምግብ አምሮት (ፍትወት) ላይ ድል መንሳት ሆነባት፡፡ የጤና አጠባበቅ ሪፎርም በዓለም አካባቢ ላሉት በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩት የአድቬንቲስት ቤተሰቦች እንደሆነ፤ ለኋይትም ቤተሰብ ትልቅ በረከት ሆነ፡፡CCh 17.4

    ስለ ጤና አጠባበቅ ሪፎርም ራእይ ከታያት በኋላና በኋይት ቤት በቀላሉ ሕመምተኞችን በማከም ሜቶድ (ዘዴ) ከደረጀ በኋላ ጐረቤቶቻቸው በሚታመሙበት ጊዜያት ሕክምና በመስጠት ይረዷቸው ዘንድ ኤልደርና ሚስስ ኋይትን ይጠሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም ጥረታቸውን በብዙ ባረከላቸው፡፡ በሌላ ጊዜያትም በሽተኞችን ወደ ቤታቸው አምጥተው፤ ጨርሰው እስኪድኑ በርህራኄ ይጠነቀቁላቸው ነበር፡፡CCh 18.1

    ሚስስ ኋይት በተራሮች ላይ፤ ወይም ባንዳንድ ሐይቅ ወይንም በገላጣው ውኃ ላይ የዕረፍትና የመደሰቻ ጊዜ በመውሰድ ትደሰት ነበር፡፡ በመኻኸለኛ እድሜዋ፤ በምሥራቃዊ አሜሪካ ክፍል ባለው በፓሲፊክ (ፕሬስ) ማተሚያ፤ ቤታችን ስትኖር ሳለች፤ አንድ ቀን በዕረፍትና በመዝናናት ትውል ዘንድ ታቀደ፡፡ ሚስስ ኋይት ከቤትዋና ከጽ/ቤቱ ቤተሰብ ጋር ሆነው፤ ከማተሚያ ቤት ቤተሰብ ጋር ይሆኑ ዘንድ ተጠየቁ፤ እርሷም በደስታ ጥሪውን ተቀበለች፡፡ ባልዋ ለቤተ ክርስቲያን ሥራ በምሥራቅ ነበር፡፡ ስለዚሁ ሁኔታ የተነገረውን ሐተታ ለርሱ በጻፈችው ደብዳቤ ውስጥ እናገኛለን፡፡CCh 18.2

    በወንዝ ዳር የጤና ምግብ ከተደሰቱበት በኋላ ሰዎቹ ሁሉ በሳንፍራንሲስኮ ቤይ (ወሽመጥ) በመርከብ ለመጓዝ ሔዱ፡፡ የመርከቡ ካፒቴን የቤተ ክርስቲያን አባል ነበር፤ ጊዜው አስደሳች የሆነ ከቀትር በኋላ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ገላጣው (የተንሰራፋው) ውቂያኖስ ይሔዱ ዘንድ ታቀደ፡፡ ሁኔታውን ስታወሳ ኤሌን ኋይት እንዲህ ስትል ጻፈች፤CCh 18.3

    «ሞገዶቹ ከፍ እያሉ ሔዱ፤ እኛም በኃይል ወደ ላይና ወደ ታች ተወዛወዝን፡፡ እኔም ስሜቴ እየገነነብኝ ሔደ፤ ግን ለማንም የምናገረው ቃል አልነበረኝም፡፡ በውነቱም፤ ሞገዱ ታላቅ ነበር፤ ውኃው በላያችን ተረጨ፡፡ ነፋሱ ከጎልድን ጌት ውጭ የበረታ ነበር፤ በሕይወቴም ይህን ያህል ማናቸውንም ተደስቼበት አላውቅም” ፡፡CCh 18.4

    ከዚያ በኋላ ትጉ የሆነው የካፒቴኑን ዓይኖችና ትእዛዙንም የመርከብ ሰራተኞች በቀልጣፋነት ሲታዘዙ ተመለከተችና አሰበች፤CCh 18.5

    «እግዚአብሔር ነፍሳትን በእጆቹ ይዞአል፤ ውኃዎችንም ይገታል፡፡ እኛም በሰፊው፤ ጥልቁ የፓስፊክ ውኃዎች ውስጥ ነጥቦች ብቻ ነን፡፡ ሆኖም የሰማይ መላእክት ይህችን ትንሽ መርከብ በሞገዶች ላይ ስትሽከረከር ይጠብቁ ዘንድ ይላካሉ፡፡ ኦ፤ አስገራሚዎቹ ያምላክ ሥራዎች! እኛ ከምናስተውለው በላይ እንዲህ የጠለቁ ናቸው! ባንድ የዓይኑ ጥቅሻ ከፍተኞቹን ሰማዮችና የባሕሩን መኻል የሚመለከት ነው»፡፡CCh 18.6

    ሚስስ ኋይት ቀድሞውንም የመደሰትን ጠባይ የተለማመደች ናት፡፡ አንድ ጊዜ እንዲህ ስትል ጠየቀች፤ «ከቶውንም ፊቴን አጨልሜ፤ ተስፋ ቢስ ወቃሽ ሁኜ አይተኸኛልን? ይህንን የሚከለክል ኃይማኖት አለኝ ወደዚህ ሐሳብ የሚመራ እውነተኛ የሆነውን የክርስቲያናዊ ዓይነተኛ ጠባይና ክርስቲያናዊ አገልግሎትን ባለማሰብ ነው፡፡ . . . ለየሱስ ከልብ የሆነ የፈቃደኝነት አገልግሎት ማገ ልገል፤ ጸሐማ ኃይማኖት ያፈራል፡፡ ክርስቶስን አጥብቀው የሚከተሉ፤ ጨለማ ፊት ከቶ አልነበራቸውም» ፡፡CCh 18.7

    ከዚያ በኋላ ሌላ ጊዜ እንዲህ ጻፈች «መደሰት ከክርስቲያናዊ ጠባይ ክብር ጋር የሚግባባ አይደለም የማለት ሐሳብ ባንዳንድ ነገር ቀርቦአል፤ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ ሰማይ ሁሉ ደስታ ያለበት ነው»፡፡ ፈገግታ ፊት ብታሳይ ፤ ፈገግታ ፊት ይመለስልሃል ፤ መልካም ቃል ብትናገር መልካም ቃል ይመለስልሃል ስትልም ገለጸች፡፡CCh 19.1

    ሆኖም በሕመም ብዙ የተሠቃየችበት ጊዜያት ነበሩ፡፡ አንዱ እንዲህ ያለ ጊዜ ወደ አውስትራልያ በሥራ ለመርዳት ወዲያውኑ ከሔደች በኋላ ነው፡፡ ለዓመት ጥቂት ሲቀራት በጣም ታማ ነበር፤ በኃይልም ተሠቃየች፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አልጋ ላይ ቆየች፤ በሌሊትም ጥቂት ሰዓታት ብቻ ትተኛ ነበር፡፡ ስለዚሁ ሁኔታ ላንድ ወዳጅ በጻፈችው ደብዳቤ ውስጥ እንዲህ ስትል ጻፈች፤CCh 19.2

    «ራሴን ረዳተቢስ ሆኜ መጀመሪያ ባገኘሁ ጊዜ ሰፊዎቹን ውኃዎች ተሻግሬ በመምጣቴ በጣም ተጸጸትሁ፡፡ ለምን በአሜሪካ አልቆየሁም? ለምን ይህን ያህል ወጪ አድርጌ በዚህ አገር ሆንሁ? በየጊዜው (እየደጋገምኩ) በአልጋው ትራስ ፊቴን ሸፍኜ በጣም ሳለቅስ ነበር፡፡ ግን በእንዲህ ያለ የልቅሶ እንባ ውስጥ ለብዙ ጊዜ ልዘፈቅ አልፈለግሁም፡፡ ለራሴም አልሁ፤ ዔሌን ጂ ኋይት ምን ማለትሽ ነው? ኮንፈረንሱ ትሔጂ ዘንድ የተሻለ እንደሆነ ከታሰበበት ሥፍራ ለመሔድ ተግባርሽ መሆኑን ስለ ተሰማሽ ወደ አውስትራልያ አልመጣሽምን? ይህ ሥራሽ አልነበረምን?CCh 19.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents