Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለድሆች የሚጠራቀሙ የምስጋና ሥጦታዎች

    በየቤተ ክርስቲያኑ ለድሆች ግምጃ ቤት ሊቋቋም ይገባል፡፡ እንግዲህ በጣም እንደሚመቸው እያንዳንዱ አባል ለእግዚአብሔር የምሥጋና ሥጦታ በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በወር አንድ ጊዜ ያቅርብ፡፡ ይህ ሥጦታ የጤና የምግብ፣ የመንፈላሰሻ ልብስ ሥጦታዎች ስለ ተሰጡን ምሥጋና ማቅረባችንን የሚገልጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር በነዚህ ምቾቶች እንደ ባረከን መጠን ለድሆች፣ ለችግረኞችና ለተጨነቁት እናጠራቅም ለወንድሞቻችን ይህን ነገር በተለይ አሳስባቸዋለሁ፡፡ ድሆችን አስቡ (አስታውሱ)፡፡ አንዳንዱን ቅምጥልናዎቻችሁን በውነትም ምቾታችሁን እንኳ ተው በጣም ያነሰ ምግብና ልብስ ሊያገኙ የሚችሉትን እርዱ፡፡ ለነሱ በመሥራታችሁ በጻድቃኑ መልክ ሆናችሁ ለየሱስ መሥራታችሁ ነው፡፡ እርሱ ከሚቸገሩት ሰዎች ጋር ራሱን አንድ ያደርጋል፡፡ የልበ ወለድ ፍላጎታችሁ ሁሉ እስኪሞሉላችሁ ድረስ አትቆዩ በስሜቶቻችሁ ላይ አትታመኑ የምትወዱት መሆናችሁ በተሰማችሁ ጊዜ ለመስጠት የምትወዱት መሆናችሁም ባልተሰማችሁ ጊዜ ለማስቀረት እንዳይሆንባችሁ፡፡ በአምላክ ቀን በሰማያዊ ርኮርድ ላይ ልታዩ እንደምትወዱ አድርጋችሁ በደንበኛው ስጡ፡፡ . . . ፳፫235T150, 151;CCh 82.3