Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፲፯—በዓለም ሁሉ ያሉ ክርስቲያኖች በክርስቶስ አንድ ይሆናሉ፡፡

    (የዚህ ምዕራፍ አብዛኛው ምክር፤ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ልማዶች ካሉዋቸው ከልዩ ልዩ አገሮች ተወክለው እንደራሴዎቻቸው በተሰበሰቡበት የሠራተኞች ስብሰባ በሚስስ ኋይት የተሰጠ ነው፡፡ ጌታ በሚስስ ኋይት አማካይነት ለሕዝቡ የሰጠው ምክር ሚስስ ኋይት ያገር ተወላጅ ለሆነችበት ማለት ለኋይት ትራስቲስ ቦርድ ብቻ የተሰጠ መሆኑን አንዳንዶች በስሕተት አስበው ነበር)፡፡CCh 129.1

    ወደ ምድራዊ ወላጆቹ በሚመጣው የልጅ ገርነት ወደ ክርስቶሰ መጥተን ተስፋ የሰጠንን ነገሮች ብንለምንና እንደምንቀበል ብናምን እናገኛቸዋልን፡፡ ሁላችን የሚገባንን ሃይማኖት ከምግባር ላይ ብናውለው ኑሮ በስብሰባችን ውስጥ ካሁን ከደም ከተቀበልነው እጅግ በበለጠው አኳኋን በአምላክ መንፈስ በተባረክን ነበር፡፡ ስብሰባው ጥቂት ቀናት አሁንም የሚቀረን በመሆኑ ደስ ይለኛል፡፡ አሁን ጥያቄው ይህ ነው ወደ ምንጩ መጥተን እንጠጣለንን; የእውነት አስተማሮች ምሳሌ ይሆናሉን; እንደ ቃሉ በኃይማኖት ብንቀበለው እግዚአብሔር ትላልቅ ነገሮች ያደርገልናል፡፡ እዚህ ልብ በጠቅላላ በአምላክ ፊት ዝቅ ያለ ሁኖ እረ ባየነውባCCh 129.2

    እነዚህ ስብሰባዎች ከተጀመሩ ወዲህ በፍቅርና በሃይማኖት ላይ በብዙ እንኖር ዘንድ እንደ ተገደድሁ ተሰማኝ፡፡ ይኸውም ይህንኑ ምሥክርነት ስለሚያስፈልጋችሁ ነው፡፡ አንዳንዶች ወደነዚህ ወንጌላዊ ጣቢያዎች የገቡት፤ ‹‹የፈረንሳዊ ሰዎችን አታስተውሏቸውም፤ ጀርመኖችንም አታስተውሏቸውም›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡CCh 129.3

    ነገር ግን እኔ የምጠይቃችሁ፤ እግዚአብሔር አያስተውላችሁምንአ ለሕዝቡ የሚሆን መልእክት ለአገልጋዮቹ የሚሰጥ እርሱ አይደለምንአ እርሱ የሚፈልጉትን ያውቃል፤ መልእክቱ በአገልጋዮቹ አማካይነት ለሕዝቡ በቀጥታ ከርሱ የሚመጣላቸው (የሚደርስላቸው) ከሆነ በተላከበት ሥፍራ ሥራውን ይፈጽማል፤ ሁሉንም በክርስቶስ አንድ ያደርጋል፡፡ አንዳንዶች ፈረንሳዊዮች፤ ሌሎችም ጀርመኖች፤ ሌሎችም አሜሪካውያን መሆናቸው የተረጎገጠም ቢሆን እንደዚሁም ክርስቶስን መስሎች እንደሚሆኑ የተረጋገጠም ቢሆን፤እንደዚሁም ክርስቶስን መሰሎች እንደሚሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡CCh 129.4

    የአይሁድ መቅደስ የተሠራው ከተራሮች ከተፈነቀሉት የተጠረቡት ደንጊያዎች ነበር፤ ደንጊያውን ሁሉ ወደ እየሩሳሌም ከማምጣታቸው በፊት የተጠረበ፤ ልዝብነት ያለው፤ የተፈተነ ሆኖ በቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚከተትበት ሥፍራ የተሰማማ ነበር፡፡ ደንጊያዎቹን ሁሉ ወደ ሥፍራው ባመጡ ጊዜ የመጥረቢያ ወይም የመዶሻ ድምፅ /ኳክታ/ ሳያሰሙበት ሕንፃው ባንድ ላይ ይገጣጠም ነበር፡፡ ይህ ሕንፃ ከነገድ ከመላስና ከሕዝብም ሁሉ ከሁሉ ደረጃዎች ከፍ ካሉትና ከዝክተኞች ከሐብታሞችና ከድሆች ከተማሩትና ከመሐይሞች (ካልተማሩት) የማሰበሰቡትን በሚይዝ በመንፈሳዊ መቅደስ የሚመሰል ነው፡፡ እነ ዚህ በመዶሻና በመሮ የሚስተካከሉት ሙት ነገሮች አይደሉም፡፡ እነሱ ከዓለም በእውነት ተፈንቅለው የወጡ ሕያዋን የሆኑ ደንጊያዎች ናቸው፡፡ ታላቁም ገንቢው ጌታ የቤተ መቅደሱ አምላክ እነሱን በመጥረብና በማለዘብ ላይ ነው፤ በመንፈሳዊ መቅደስም ውስጥ ለየሥፍራዎቻቸው የተገቡ እንዲሆኑ እያደረጋቸው ነው፡፡ ሲፈጸም ይህ መቅደስ በክፍሎቹ ሁሉ ፍጹም የሆነ የመላእክትና የሰዎች አድናቆት ይሆናል፤ ገንቢውና ሰሪው አምላክ ነውና እንግዲህ በርሱ ላይ ምንም ጉዳት ሊደርስበት አያሻም ብሎ ማንም አያስብ፡፡CCh 129.5

    በዓመሉና በሐሳቡ ፍጹም የሆነ ማንም ሰው ማንም ሕዝብ የለም፡፡ አንዱ ከሌላው መማር አለበት፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከልዩ ልዩ አገሮች የሆኑ ተወልጆች ባንድነት እንዲቀላቀሉ፤ በፍርድ በሐሳብም አንድ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ያለው ኅብረት ይሆንባቸዋል፡፡CCh 130.1

    በአውሮፓ ያሉ ልዩ ልዩ ያገር ተወላጆች የተለየዩ እንደሆኑና በተለየ መንገድ ሊደረስባቸው ያለበት መሆኑን ብዚዎች ሲናገሩ ስለ ሰማሁ ወደዚህ አገር ለመምጣት ፈርቼ ነበር፡፡ ነገር ግን ያምላክ ጥበብ ፍላጎታቸው ለማሰማቸውና ለማለምኑት ተስፋ ተሰጥቷል፡፡ እግዚአብሔር እውነትን ከማቀበሉበት ሥፍራ ሰዎችን ሊያመጣ ይችላል፡፡ እንግዲህ ልዩነቶች አይኖሩም፡፡ ወደ የሱስ ተመልከቱ ወንድሞቼ የርሱን ጠባይና መንፈስ ቅዱ፤ ወደነዚህም ልዩ ልዩ ክፍሎች ለመድረስ ምንም ችግር የለባችሁም፡፡CCh 130.2

    የምንከተል ስድስት ወይም አምስት ምሳሌዎች /አርአያዎች/ የሉንም፤ አንድ ብቻ አለን፤ ይኸውም ክርስቶስ የሱስ ነው፡፡ የኢጣልያን ወንድሞች የፈረንሳዊና የጀርመን ወንድሞችም እንደርሱ ለመሆን ቢሞክሩ፤ እግሮቻቸውን በዚያው የእውነት መሠረት ላይ ይተከላሉ፡፡ በአንዱ ፈቃድ ውስጥ የሚኖር ያው መንፈስ በሌላውም ውስጥ ይኖራል፤ይኸውም ክርስቶስ የክብር ተስፋ በውስጣቸው የሚኖር ነው፡፡ የማስጠነቅቃችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በልዩ ልዩ ያገር ተወላጆች መኻከል የመለያየት ግድግዳ እንዳትሰሩ ነው፡፡ በተቀር ባለበት ሁሉ ልታስወግዱት እሹ፡፡ ለአንድ ዓላማ ይኸውም ለጓድ ሰዎቻችን ደህንነት እይሰራን ሁሉንም በየሱስ ወዳለው ስምምነት እናመጣ ዘንድ መጣጣር አለብን፡፡CCh 130.3

    አገልጋዮች ወንድሞቼ ሆይ የበለጸጉትን ያምላክን ተስፋዎች በመጨበጥ አትፈልጉምንአ እንዳይታይ ራስን አስወግዳችሁ የሱስ እንዲታይበት አታደርጉምንአ እግዚአብሔር በናንተ አማካይነት ለመሥራት ከመቻሉ በፊት ራስ መሞት አለበት፡፡ ራስ በአን፤ በሌላውም ላይ እዝህም ብቅ ሲል ላይ ጭንቀት ይሰማኛል፡፡ በናዝሬቱ በየሱስ ስም እነግራችኋለሁ፤ ፈቃዶቻችሁ መሞት አለባቸው፤ እንደ እግዚአብሔር መሆን አለባቸው እርሱ ሊያቀልጣችሁና ከርኩሰት ሁሉ ሊያነጻችሁ ይፈልጋችኋል፡፡ በእግዚአብሔር ኃይል ልትሞሉ ከሚቻለው በፊት የሚሠራላችሁ ታላቅ ሥራ አለ፡፡ እንግዲህ ይህ ስብሰባ ከመዘጋቱ በፊት የበለጸገውን በረከቱን ትገነዘቡ ዘንድ ወደርሱ እንድትቀርቡ እለምናችኋለሁ፡፡ 19X179— 182; CCh 130.4