Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ስሜት ብቻ የቅድስና ማመልከቻ አይደለም፡፡

    ደስተኛ ስሜት ወይም ደስታ የሌለው መሆን ሰው የተቀደሰ ወይም ያልተቀደሰ ለመሆኑ ማስረጃ አይደለም፡፡ የወረት ቅድስና የሚባለው ነገር የለም፡፡ እውነተኛ ቅድውና ዕለታዊ ሥራ ሕይወት እስካለብን የሚቀጥል ነው፡፡ ዕለታዊ ፈተናዎችን የሚዋጉ ሁሉ ኃጢአተኛ ዝንባሌዎቻቸውን አሸንፈው የልብና የሕይወት ቅድስና የሚሹ በራሳቸው ቅድስና እንዳለባቸው የፉከራ አነጋገር አይናገሩም፡፡ እነርሱ ለጽድቅ የሚራቡና የሚጾሙ ናቸው፡፡ ኃጢአት በእነሱ ዘንድ እጅግ የኃጢዓት ሥራ ሆኖ ይታያቸዋል፡፡ ፲፮16SL10; CCh 100.1

    እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን አይተወንም፡፡ ስህተት አድርገን መንፈሱን፣እናሳዝን ይሆናል ነገር ግን ንስሐ ስንገባና በተጸጸተ ልብ ወደርሱ ስንመጣ እርሱ አያስወግደንም፡፡ የሚወገዱ ክልከላዎች (እንቅፋቶች) አሉ፡፡ የስሕተት ስሜቶችን ወድደናል፣ ትእቢት፣ በራስ መብቃት፣ ትዕግስት ማጣትና ማጉረምረም ኑረውብናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከአምላክ ይለዩናል፡፡ ኃጢአትን መናገዘዝ ተገቢ ነው በልባችንም ውስጥ የጠለቀ የጸጋ ሥራ ሊሆንብን ይገባል፡፡ ደካሞችና ተስፋ የቆረጡ (የተስፈራሩ) እንደሆኑ የሚሰማቸው ጠንካሮች አምላክ ሰዎች ሆነው ለጌታ የተከበረ ሥራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከፍ ካለው አቋም መሥራት አለባቸው ራስን በመውደድ ሐሳቦች መመራት የለባቸውም፡፡CCh 100.2

    አንዳንዶች በረከቱን ለመለመን ከመቻላቸው በፊት በምርመራ ላይ መሆንና እንደታደሱ ለጌታ ማስረዳት እንደሚገባቸው የሚሰማቸው ይመስላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተወዳጆች ነፍሳት አሁን እንኳ በረከቱን ሊለምኑ ይችላሉ፡፡ ደካማነታቸውን ለመርዳት ጸጋው የክርስቶስ መንፈስ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ክርስቲያናዊ ጠባይ ሊያበጁ አይችሉም፡፡ እንዲሁ እንዳለን፣ ኃጢአተኞች ረዳተቢሶች ጥገኞች ሁነን ወደ እርሱ እንድንመጣ የሱስ ይወዳል፡፡CCh 100.3

    ንስሐ መግባት እንደዚሁም ይቅርታ ማግኘት በክርስቶ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ ስለ ኃጢአታችን የምንረዳውና ይቅርታ ማግኘት የሚያስፈልገን መሆኑ የሚሰማን በመንፈስ ቅዱስ አነቃቂነት ነው፡፡ ከሚጠጠቱት በስተቀር ማንም ይቅርታ አያገኝም ነገር ግን ልብን ንስሐ እንዲገባ የሚያደርግ የአምላክ ጸጋ ነው፡፡ እርሱ ድክመታችንና ሕመማችንን ሁሉ ያውቃልና ይረዳናል፡፡ ፲፯172TT91— 94;CCh 100.4

    ጨለማና ተስፋ መቁረጥ አንዳንድ ጊዜ ነፍስን ይወርርና ሊያጥለቀልቀን ያስፈራራናል ነገር ግን እምነታችንን መጣል የለብንም፡፡ ቢሰማን ባይሰማንም ዓኖቻችንን በሱስ ላይ አተኩረን መጠበቅ አለብን፡፡ የታወቀውን ተግበር ሁሉ በታማኝነት ለመሥራት መሻት አለብን ከዚያም በኋላ በአምላክ ተስፋዎች ላይ በጸጥታ ማረፍ ነው፡፡CCh 100.5

    በየጊዜያቱ የማንገባ የመሆናችን የጠለቀ ስሜት ሲያድርብነ በነፍሳችን ውስጥ ትልቅ ፍርሃት ያመጣብናል ነገር ግን እግዚአብሄር በና ላይ እንደ ተለወጠብን እኛም በአምላክ ላይ እንደተለወጥንበት ማስረጃ አይደለም፡፡ ሐሳብን ወደ የተለየ የስሜት ደረጃ ለመለጎም ጥረት ማድረግ የለብንም፡፡ ትናንትና የተሰማንን ሰላምና ደስታ ኤሴማንም ይሆናል፣ ነገር ግን በሃይማኖት የክርስቶስን እጅ መጨበጥና በብርሃንም ሆነ በጨለማ በምሉ በእርሱ መታመን አለብን፡፡CCh 100.6

    ለሚያሸንፉ የተዘጋጁላቸውን አክሊሎች በሃይማኖት ወደ ላይ ተመልከት የዳኑት የዕልልታ መዝሙር የታረደው በግ ይገባዋል ለእግዚአብሔር ገዝተህናልና! ሲሉ የሚዘምሩትን ስማ፡፡ ይህ ሁኔታ እርግጠና መሆኑን ትመለከተው ዘንድ ተጣጣር፡፡CCh 101.1

    ሐሳባችን ይበልጥ በክርስቶስና በሰማያዊ ዓለም ላይ እንዲያርፍ የምንፈቅድ ከሆን የጌታን ጦርነት በመዋጋት ረገድ ኃያል የሆነ አነቃቂነትና ድጋፍ ማግኘት አለብን፡፡ በተሎ የኛ ቤት ሊሆን የተቃረበውን ን የተሻለውን አገር ክብሮች ስናስብ የዓለም ትዕቢት ፍቅር ኃይላቸውን ያጣሉ፡፡ በክርስቶስ ተወዳጅነት አጠገብ ምድራዊ ድምቀቶች (ሐሳቦች) ሁሉ ዋጋቸው ትንሽ ይመስላል፡፡CCh 101.2

    ጳውሎስ በመጨረሻ በሮም እሥር ቤት ውስጥ ታስሮ ከሰማይ ብርሃንና አየር ተዘግቶበት የቀለጠፈ የወንጌል ሥራውን ከማድረግ ታግዶ በዚያኑ ጊዜም የሞት ፍርድ የሚፈረድበት መሆኑነ ሲተባበቅ ሳለ ሆኖም ወደ መጠራጠርና ተስፋ መቁረጥ አላደላም፡፡ ከዚያው ከጨለማው ግዞት ቤት ውስጥ ዓይነተኛ የሆነው ሃይማኖትና ድፍረት የመላበት በተከታዮቹ ዘመኖች ሁሉ የነበሩትን የጻድቃንና የሰማዕታትን ልቦች ያነቃቃው የአሟሟቱ ምስክርነት መጣ፡፡ ‹‹እኔ እነሆ እሠዋለሁ የመሰናበቴም ጊዜ ደርሷል፡፡ መልካሙን ገድል ተጋደልሁ ሩጫዬንም ጨረስሁ ሃይማኖንም ጠበቅሁ፡፡ እንግዲህም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል እግዚአብሔር የሚሰጠን በዚያች ቀን ያ ጻድቅ ፈረጅ፡፡ ለኔም ብቻ አይደለም መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ እንጂ ደግሞ›› (፩ ጢሞ ፬፣፮-፰) ሲል የተናገራቸው ቃላት በነዚህ ገጾች ውስጥ ለመግለጽ የሞከርነውን የቅድስና ውጤቶች (ፍሬዎች) በሚገባ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ፲፰18SL89—96CCh 101.3