Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    አሥራት መክፈል በእግዚአብሔር የታዘዘ ነው፡፡

    የፈቃድ ሥጦታዎችና አሥራት የወንጌል ገቢ ገንዘብ ነው ለሰው ከተሰጡት ገንዘቦች (ሐብቶች) አምላክ የተለየ ድርሻ ይኸም አሥራትን ይፈልጋል፡፡ ፯75T149; CCh 75.2

    እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገው ፍላጎት ሌላውን ፍላጎት ሁሉ የሚጠቀልል መሆኑን ሁሉ ሊያስብ ይገባዋል፡፡ እርሱ በልግስና ይሰጠናል ከሰውም ጋር ያደረገው ውል ከንብረቶቹ አሥረኛው ላምላክ እንዲመለስ ነው፡፡ በቸርነቱ መዝገቦቹን ለመጋቢዎቹ ይሰጣል ግን አሥረኛው የኔ ነው ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ንብረቱን ለሰው እንደ ሰጠው መጠን ሰውም ከገንዘቡ (ከንብረቱ) ሁሉ አሥራትን በታማኝነት ለአምላክ መመለስ አለበት፡፡ ይህን ዕውቅ የሆነው ድርጅትን የሱስ ክርስቶስ ራሱ ያደራጀው ነው፡፡ ፰8 6T384; CCh 75.3

    ለዚህ ጊዜ የሚሆን እውነት ወደ ጨለማዎቹ የምድር ማዕዘኖች መድረስ አለበት ይህም ሥራ በቤት ሊጀመር ይቻላል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ራስን የመውደድ ሕይወት መግር አይገባቸውም ግን በክርስቶስ መንፈስ ተቀብተው ከርሱ ጋር ተስማምተው መሥራት አለባቸው፡፡ ፱93T381; CCh 75.4

    የሱስ ሊያደርገው የመጣ መሆኑን የተናገረው ታላቁ ሥራ በምድር ላሉት ተከታዮቹ አደራ ተሰጠ፡፡ የሥራውን ውጥን ራሱን ደጋፊ ያደርገው ዘንድ በቂ ገንዘብ እንዲያጠራቅሙ (እንዲያገኙ) ለሕዝቡ ኘላን ሠጥቷል፡፡ አሥራትን በመክፈል ሥርዓት (ሲስተም) ረገድ እግዚአብሔር ያቀደው ኘላኑ በቅንነቱና በሐቀኝነቱ ያማረ ነው፡፡ አጀማመሩ ካምላክ ነውና ሁሉም በሃይማኖትና በድፍረት ሊቀበሉት ይችላሉ በርሱ ውስጥ ቅንነትና ጠቃሚነት ተጣምረዋል ይህነንም ለማስተዋልና ለመፈጸም የትምህርት ጥልቀት አያስፈልገውም ሁሉም የተከበረውን የደህንነት ሥራ ወደፊት ያካሒዱ ዘንድ ተካፋዮች ሊሆኑ እንደሚቻላቸው ሊሰማቸው አለባቸው ወንድ፣ ሴት፣ ወጣትም ሁሉ ለጌታ ዋና ግምጃ ቤት ሊሆኑ ይችላሉ በግምጃ ቤቱ የሚፈለጉትን ፍላጎቶች ለማከናወን ወኪል ለመሆን ይችላሉ፡፡ ሐዋርያው ‹‹እላንት ሁላችሁ አከማቹ እያንዳንዱም ከርሱ ዘንድ ያኑር እንደ ተቻለው›› ይላል፡፡ 1ቆሮ ፲፫፣ ፪፡፡CCh 75.5

    በዚህ ጐዳና (ሲስተም) ታላላቅ ነገሮች ይፈጸማሉ ማንም ሁሉም ቢቀበለው እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር ትጉና ታማኝ ዋና ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ የመጨረሻውንም የማስጠንቀቂያ መልእክት ለዓለም በመናገር ረገድ ታላቁን ሥራ ወደፊት የምናካሒድበት የገንዘብ እጦት አይሆንብንም፡፡ ሁሉም ይህን ሲስተም ቢከተል ግምጃ ቤቱ ሙሉ ይሆናል ሰጪዎቹም ድሆች የሚሆኑ አይደለም፡፡ በተሰጠው ሥጦታ ሁሉ አማካይነት ላሁኑ የእውነት ጉዳይ በበለጠው ይተባበራሉ ‹‹ለራሳቸው መልካም መሠረት እንዲያከማቹ ለሚመጣው ዘመን የዘላለም ሕይወት ይወስዱ ዘንድ›› ፩ ጢሞቴዎስ ፯፡፲፱፡፡CCh 75.6

    ጽኑዎች ደንበኞች ሰራተኞች የልግሥና ጥረቶቻቸው ዝንባሌ አምላክን ባልንጀሮቻቸውን የመውደድ ፍቅር የሚያስገኝላቸው መሆኑንና የግል ጥረቶቻቸው የጠቃሚነታቸውን ሁናቴ የሚያበረክትላቸው መሆኑን ሲያዩ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሰራተኞች መሆን ታላቅ በረከት መሆኑን ይገነዘባሉ፡፡ ክርስቲያናዊት ቤተ ክርስቲያን የሆኑ በጠቅላላው ዓለምን በሚያጥለቀልቀው የግብረገብ (የሞራል) ጨለማነት ላይ ለመዋጋት ለጦርነቱ መደገፊያ እንዲሆን ባላቸው ነገሮች ምፅዋት ይሰጡ ዘንድ አምላክ የሚፈልግባቸውን ፍላጎቶች አይቀበሉም፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ትጉዎች ቀናተኞች ሰራተኞች እስኪሆኑ የእግዚአብሔር ሥራ ከቶ ሊስፋፋ አይችልም፡፡ ፲103T388, 389;CCh 76.1