Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፯—ሊነገር ያልተቻለ ራእይ፡፡

    በሰላማንካ ውስጥ በኒዮርክ ኅዳር ፲፰፻፺ ዓ.ም እ.ኤ.አ ስብሰባዎች በተደረጉበት ሚስስ ኋይት ለብዙ ጉባዔዎች ንግግር ስታደርግ በፍጹም ደከመች፤ ወደዚያ ከተማ ስትሔድ ኃይለኛ ጉንፋን ይዞዋት ነበርና ከስብሰባዎቹ አንዱን ካከናወነች በኋላ ተስፋ ቆርጣና ታማ ወደ ክፍልዋ ሔደች፡፡ ነፍስዋን በአምላክ ፊት ለማፍሰስና ለጤንነትዋና ለብርታትዋ ምሕረት ትለምን ዘንድ አሰበች፡፡ በወንበርዋ አጠገብ ተንበርክካ ስለ ደረሰባት ሁኔታ ራስዋ በተናገረች ቃላት እንዲህ አለች፤CCh 25.1

    «መላው ክፍል ብሩህ በሆነው ብርማ (የጠራ) ብርሃን የተመላ በመሰለ ጊዜ ፤ ምንም ቃል አልተናገርሁም ተስፋ የመቁረጥና የመስፈራራት ሕመሜም ተወገደልኝ፡፡ እኔም በመጽናኛና በተስፋ ማለት በክርስቶስ ሰላም ተመላሁ»፡፡CCh 25.2

    ከዚያም በኋላ ራእይ ታያት፡፡ ከራእዩም በኋላ ልትተኛ አልፈለገችም፡፡ ልታርፍም አልፈለገችም ፤ ተፈወሰች ፤ ዕረፍትም አገኘች፡፡CCh 25.3

    በጧቱ አንድ ውሳኔ መስጠት የተገባ ሆነ፡፡ ቀጥለው ያሉት ስብሰባዎች ወደሚደረጉበት ሥፍራ ልትሔድ ነውን ወይንስ በባትል ክሪክ ወዳለው ቤትዋ መመለስ የሚገባት ነው? ኤል ኤ ቱ ሮብንሰን የሥራው ኃላፊ የነበሩ፤ ኤልደር ዊልያም ኋይት የሚስስ ኋይት ልጅ ከርሷ መልስ ያገኙ ዘንድ እክፍልዋ ተጠርተው ነበር፡፡ ልብስዋን ለባብሳና በጎ ሁና አገኙዋት ልትሔድም ስትዘጋጅ ነበር፡፡ ስለ መፈወስዋ ስለ ራእዩም ነገረቻቸው፡፡ ባለፈው ሌሊት የተገለጸልኝን ልነግራችሁ እወዳለሁ፤ በራእይ በባትል ክሪክ ያለሁ ይመስለኝ ነበር ፤ መልእክተኛውም መልአክ «ተከተይኝ» አለኝ ስትል ነገረቻቸው፡፡ ከዚያ በኋላ አሰበችበት በአእምሮዋ ትዝ ሊላት አልተቻለም፡፡ ልትነግራቸው ሁለት ጊዜ ሞከረች ግን የታያት ትዝ ሊላት አልተቻለም፡፡ በተከታዮቹ ቀናት ስለ ታያት ጻፈች፤ ይኸውም ስለ ሃይማኖታዊ ነጻነታችን ስለ ታቀደው ፕላን በዚያን ጊዜ ዘ አሜሪካን ሰንቲኔል ስለ ተባለው ጋዜጣ (ጁርናል) ነበር፡፡CCh 25.4

    «በሌሊት ጊዜ በአያሌዎቹ ምክሮች ውስጥ ነበርሁ ፤ እዚያም ነገራቸው ተሰሚ (እንፍሉየንሺያል) የሆኑ ሰዎች የአሜካን ሰንቲኔል፤ «ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት” የተባሉትን ቃላት ከአምዶቹ ውስጥ ቢያስቀርና ስለ ሰንበት ምንም ነገር ባይል የዓለም ታላላቅ ሰዎች ይደግፉታል፤ የተወደደም (የታወቀ) ይሆናል ፤ ትልቅም ሥራ ያደርጋል እያሉ ደጋግመው የተናገሩትን ቃላት ሰማሁ፡፡ ይህም በጣም የሚያስደስት መሰላቸው፡፡CCh 25.5

    «ፊታቸው በርቶ አየሁ፤ በሰንቲኔሉ የተወደደ ክንውን ያስገኙለት ዘንድ በፖሊሲው መሥራት ጀመሩ፡፡ እውነትን በአሳብና በነፍስ ጽላት ውስጥ በፈለጉት ዘንድ መላው ነገር የታወቀ ሆነ»፡፡CCh 25.6

    ብዙዎች ሰዎች የዚህን ጋዜጣ ኤዲቶሪያል ፓሊሲ ሲከራከሩበት ያየች መሆንዋ ግልጽ ነው፡፡ ጀኔራል ኮንፈረንስ በመጋቢት ፲፰፻፺፩ ዓ.ም እ.ኤ.አ በተከፈተ ጊዜ ሚስስ ኋይት ለሠራተኞቹ በየጧቱ በ፲፩ ሰዓት ተኩል እንድትናገርና በሰንበት በቀትር በላይ አራት ሺህ ለሆኑት ለመላው ኮንፈረንስ ንግግር ታደርግ ዘንድ ተጠየቀች፡፡ በሰንበት ከቀትር በላይ የጠቀሰችው ጥቅስ «እንዲሁ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ መልካሙን ሥራችሁን አይተው የሰማዩን አባታችሁን ያመሰግኑት ዘንድ” የሚል ነበር፡፡ መላው ንግግር ፤ ዕውቅ የሆነውን የሃይማኖታቸውን ዓላማ ብድግ ያደርጉ ዘንድ ለሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች የቀረበው ተማኅፅኖ ነው፡፡ በስብሰባው ጊዜ ሦስት ጊዜያት በሰላማንካ ስለ አየችው ራእይ ለመናገር ተነሳች፤ ግን በእያንዳንዱ ጊዜ ታገደች፡፡ የራእዩ ሁኔታዎች ከአእምሮዋ ወዲያው ጠፉ፤ ከዚያ በኋላ አለች ፤ «ስለዚህ ቆይቼ ጨምሬ የምናገር አለኝ” ፤ ስብከትዋንም ባንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ አከናወነች ፤ በጥሩ አኳኋንም ወደ ፍጻሜ አደረሰችው ፤ የጸሎቱም ስብሰባ ስንብት ሆነ፡፡ ሁሉም ራእዩ ትዝ ሊላት ያልተቻለ መሆኑን ልብ አደረጉ፡፡CCh 25.7

    የጀኔራል ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት ወደርስዋ መጡና የጧት የጸሎት ስብሰባ እንድትወስድ ጠየቋት፡፡CCh 26.1

    «የለም” ስትል መለሰችላቸው ፤ «ደክሞኛል ምሥክሬን መስክሬአለሁ፡፡ ለጧቱ የጸሎት ስብሰባ ሌላ ፕላን ማድረግ አለብዎት ፤ ሌላም ፕላን ታቀደ፡፡CCh 26.2

    ሚስስ ኋይት ወደ ቤትዋ እንደ ተመለሰች የጧቱን የጸሎት ስብሰባ የማትገባ መሆኗን ለቤተሰብዋ አባሎች ነገረች፡፡ ደክማ ነበር ፤ መልካም ዕረፍት መውሰድዋ ነበር፡፡ በእሁድ ጧት ገብታ መተኛት ሆነባት ፕላኑም በዚሁ አኳኋን ታቀደ፡፡CCh 26.3

    በዚያው ሌሊት የኮንፈረንሱ ስብሰባ ወደ ፍጻሜ ከደረሰ በኋላ፤ ጥቂቶች የተሰበሰቡት ሰዎች በሬቪው አንድ ሔራልድ ቤት ውስጥ ከብሮዎቹ በአንዱ ውስጥ ተገናኙ፡፡ በዚያ ስብሰባ ፤ አሜሪካን ሴንቲኔል የተባለውን ጋዜጣ ያወጡ የማተሚያ ቤት አላፊዎች (እንደራሴዎች) ነበሩ ፤ እዚያም የረሊጅየስ ሊበርቲ አሶሲየሺን (የኃይማኖት ነጻነት ማኅበር) መሪዎች ደገሞ ነበሩ፡፡ አስቸጋሪውን ጥያቄ ማለት ስለ አሜሪካን ሴንቲኔል ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ሊነጋገሩበትና ሊያደላድሉ ተገናኙ፡፡ በሩ በዚያን ጊዜ ተዘጋ ጥያቄው እስኪወሰን በሩ እንዳይከፈት ሁላቸውም ተስማሙ፡፡CCh 26.4

    እሁድ ጧት ከሌሊቱ ከዘጠኝ ሰዓት ትንሽ ቀደም ብሎ ስብሰባው በመቃወስ ተፈጸመ የኃይማኖታዊ ነጻነት ሰዎች (ረሊጅየስ ሊበርቲ) የፓሲፊክ ፕረስ ለጥየቃቸው እሺ ባይሉና «ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት” እና «ሰንበት” የሚለውን ቃል ከዚያ የጋዜጣ አምዶች ካላስቀሩ የረሊጅየስ ሊቨርቲ አሶሲየሺን አባል አድርገው ከእንግዲህ አይቀበሉትም (አይጠቀሙበትም) ሲሉ ገለጹ፡፡ ይህም ሲሆን ጋዜጣውን መግደላቸው ነው፡፡ በሩን ከፈቱና ሰዎቹ ሊተኙ ወደየክፍላቸው ሔዱ ፡፡CCh 26.5

    እግዚአብሔር ግን ከቶ የማይተኛ ወይም የማያንቀላፉ መልእክተኛውን መልአክ በዚያው ጧት በዘጠኝ ሰዓት ወደ ዔሌን ኋይት ክፍል ላከው፡፡ ከእንቅልፍዋ ነቃችና ወደ ሰራተኞቹ ስብሰባ ባስራ አንድ ሰዓት ተኩል እንድትሔድና በሰላማንካ የታያትን ታቀርብ ዘንድ እንደሚገባት ተነገራት፡፡ ልብስ ዋን ለብሳ ወደ ቢሮዋ ሔዳ በሰላማንካ የታያትን የጻፈችበትን ጋዜጣ ወሰደች፡፡ ሁኔታው ግልጽ ሁኖ በአእምሮዋ ትዝ ባላት ጊዜ ከዚሁ ጋር ይዛ ለመሔድ ጨምራ ጻፈችበት፡፡CCh 26.6

    ሚስስ ኋይት በክንድዋ ብዙ ረቂቆች ተሸክማ በበሩ ስትመጣ በታየች ጊዜ ሰባኮቹ ወደያውኑ ከቤተ ጸሎት መነሳታቸው ነበር፡፡ ተናጋሪው የጀኔራል ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት ነበሩ ፤ እርሳቸውም ተነጋገሯት፡፡CCh 27.1

    «ሲስተር ኋይት” አሏት «አንቺን በማየታችን ደስ ብሎናል፡፡ ለኛ መልእክት አለሽን?”CCh 27.2

    «በእውነትም አለኝ” አለቻቸውና ወደፊት ተራመደች፡፡ ከዚያ በኋላ በፊተኛው ቀን ካቋረጠችበት ሥፍራ ላይ ጀመረች፡፡ በዚያው ጧት በዘጠኝ ሰዓት ከእንቅልፍዋ አስነስቶዋት ባሥራ አንድ ሰዓት ተኩል ወደ ሠራተኞች ስብሰባ ሔዳ በሰላማንካ ታይትዋት የነበረውን እንድታቀርብ የተነገራት መሆኑን ነገረቻቸው፡፡CCh 27.3

    «በራእይ» አለች «በበትል ክሪክ ያለሁ ይመስለኝ ነበር፡፡ ወደ ሬቪው አንድ ሔራልድ ቢሮ ተወሰድሁና መልእክተኛው መልአክ «ተከተይኝ» ሲል አዘዘኝ፡፡ እኔም የተሰበሰቡት ሰዎች ስለ ነገሩ አጥብቀው ወደሚከራከሩበት ክፍል ተወሰድሁ፡፡ የሰጡት የጋለ መግለጫ ነበር ግን በዕውቀት መሠረት የሆነ አይደለም»፡፡ ስለ ኤዲቶሪያል የአሜሪካን ሴንቲኔል ፖሊሲ ሲከራከሩ እንደ ነበሩም ነገረቻቸው፤ አለችም «ከሰዎቹ አንዱ የሴንቲኔልን ኮፒ ወስዶ እራሱ ላይ ከፍ አድርጎ ይዞ «ስለ ሰንበትና ስለ ዳግመኛ መምጣት የተጻፉት አርቲክሎች ከዚህ ወረቀት ካልወጣ እንግዲህ የረሊጅየስ ሊበርቲ አሶሲየሽን አባል አድርገነው ልንጠቀምበት (ልንቀበለው) አይቻለንም» ሲል አየሁ፡፡ ኤሌን ኋይት ራእዩ ከብዙ ወራት በፊት የታያት መሆኑንና በዚያው በታያት ራእይ መሠረት ምክር መስጠትዋን እያወሳች ላንድ ሰዓት ያህል ተናገረች፡፡ ከዚያ በኋላ ተቀመጠች፡፡CCh 27.4

    የጀኔራል ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት ስለዚሁ ምን እንደሚያስብ አላወቀም፡፡ እንዲህ ያለ ማናቸውም ስብሰባ ከቶ አልሰማም ነበር፡፡ ግን አንድ ሰው በክፍሉ በስተኋላ የነበረ ብድግ ብሎ መናገር ስለ ጀመረ ፤ እነሱ ነገሩ እንዲገለጽላቸው ብዙም አልቆዩም፡፡CCh 27.5