Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፲፮—ለተቸገሩትና ለሚሠቃዩት የክርስቲያን አስተያየት፡፡

    ዛሬ እግዚአብሔር ባልንጀራቸውን /ጐረቤታቸውን/ ይወዱ እንደሆን ያሳዩ ዘንድ ለሰዎች ምቹ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ባልንጀራውን በውነቱ የሚወድ ለድሆች ለተቸገሩት ለቆሰሉ፤ ለመሞት ዝግጁዎች ለሆኑት ምሕረት የሚያሳይ ነው እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ችላ የተባለውን ሥራውን እንዲወስድ የፈጣሪውን የግብረገብ (የሞራል) ምሳሌ በሰው ውስጥ ሊመልስለት (ሊያድስለት) እንዲሻ ይጠራዋል፡፡ ፩1WM49;CCh 125.1

    ለሌሎች የምናደርገው ሥራ ጥረት፤ ራስን መካድና ራስን መሠዋት የሚያስፈልገው ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ ልጁን በመስጠቱ ካደረገልን መሥዋዕት ጋር ልናመዛዝን የምንችል ትንሻ መሥዋዕት ምንድን ናትና ፪26T2X3;CCh 125.2

    የዘላለም ሕይወትን የመውረስ ሁኔታዎች (ውሎች) በመድኃኒታችን እጅግ ግልጽ በሆነው አኳኋን ይነገራሉ፡፡ የቆሰለና የተቀማው ሰው (ሉቃስ 10 ፴-፴፯) ለነሱ አሳቢነታችንን፤ ርህራኄያችንን፤ ፍቅራችንን በመንገልጽላቸው ዜጋዎች ይመሰላል፡፡ እኛ ልብ በምናደርጋቸው ሁኔታ ሥር የሆኑትን ችግረኞችንና ያልታደሉትን ችላ ብንላቸው እነማን እንደሆኑ ግድ የለም፤ የዘላለም ሕይወት የማግኘት ማረጎገጫ የለንም እግዚአብሔር ለሚፈልግብን ፍላጎቶች መልስ የምንሰጥ አይደለንምና ከኛ ጋር ስላልሆኑና ዘመዶቻችን ስላልሆኑ ለሰዎች የምንራራና የምናዝን አይደለንም፡፡ እንግዲህ የመጨረሻዎቹ ስድስቱ ትእዛዛት የሚታመኑበትን ሁለተኛውን ትልቅ ትእዛዝ የምትተላለፉ ሆናችሁ ተገኝታችኋ ል፡፡ በአንዲቱ ነገር የሚበድል በሁሉ የሚበድል ነው፡፡ ለሰዎች ፍላጎቶችና ችግር ልባቸውን የማይከፍቱ ከአሠርቱ ትእዛዛት በመጀመሪያዎቹ አራቱ ትእዛዞች ውስጥ እንደ ተነገረው ለአምላክ ፍላጎቶች ልባቸውን የሚከፍቱ አይደለም፡፡ ጣዖታት ልብንና ፍቅርን ይማርካሉ፤ አምላክም አይከበርም፤ ከፍ ያለ ሆኖም አይነግሥበትም፡፡፫33T 524;CCh 125.3

    በብረት ብዕር በቋጥኝ ላይ እንደሚቀረጸው በሕሊናም ሊቀረጽ (ሊጻፍ) ይገባል፤ ምሕረትን፤ ርህራኄንና ጽድቅን ችላ የሚል፤ ድሆችንም ችላ የሚል የሚቸገሩትን ሰዎች ለፍላጎታቸው ግድ የሌለው ቸርና ትሁት ያልሆነ ጠባይን በማጐልመስ (በማሻሻል) ረገድ አምላክ ከርሱ ጋር ሊተባበር ከማይችልበት ላይ ራሱን መምራቱ ነው፡ የሐሳብና የልብ (ካልቸር) ዕውቀት በጣም በቀላሉ የሚከናወነው፤ ፍላጎታቸውን ለመርዳት ጥቅማችንና መብታችንን ሰጥተን እንዲህ ያለው የመተዛዘን ርህራኄ ሲሰማን ነው፡፡ ለራሳችን የሚቻለንን ሁሉ ማግኘትና መጠበቅ የነፍስን ድህነት ያስገኛል፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ ባሕርይ ሁሉ በክርስቶስ መሥመሮች ላይ እየሰሩ እግዚአብሔር የመደበላቸውን ሥራ የሚያደርጉትን አቀባበላቸውን ይጠባበቃል፡፡፬46T262:CCh 125.4

    መድኃኒታችን ማዕረግንና የወገን ልዩነትን ዓለማዊ ክብርና ብልጽግናን አይመለከትም፡፡ በርሱ ዘንድ መልካም ጠባይና የሐሳብ ቅድስና ከፍ ያለ ዋጋንት አለው፡፡ ለብርቱና በዓለም ዘንድ ለተከበረው አያደላም፡፡ እርሱ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ የወደቀውን ነፍስ ወደ ራሱ ለመመለስ ይሻል፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት የመተዛዘን ርህራኄ የሚያደርገውን ከተከታዮቹ ማን እንደሆነ ለማየት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ ፭5 6T268;CCh 126.1

    ለቸርነት አድራጎት ለተደሳች ፊተ ገጽህ ተስፋ ላለው ቃሎችህ እንድትጨብጠው በእጅህም ጨበጣ ብቻ የሚጠራህ አይደለም፡፡ ያምላክን ችግረኞች ስትጐበኛቸው፤ አንዳንዶቹ ተስፋ የራቀባቸውን ታገኛለህ ለነሱ የፀሐይ ብርሃን አምጣላቸው፡፡ የሕይወትን እንጀራ የሚፈልጉ አሉ ከእግዚአብሔር ቃሕ አንብብላቸው፡፡ ምድራዊ ፈውስ ሊደርስባቸው ወይም ሐኪም ሊያድናቸው የማይችል ሌሎችም የነፍስ በሽታ አለባቸው፤ ወደ የሱስ አምጣቸው፡፡CCh 126.2