Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፲፪—በምድር ያለችው ቤተ ክርስቲያን

    እግዚአብሔር ትእዛዛቱን የሚጠብቁ የተመረጡ ሕዝቡ የሆኑ በምድር ቤተ ክርስቲያን አለው፡፡ አርሱ የሚመራው ሕዝብን ነው እንጂ እዚህና እዚያ በየፊናቸው የተበታተኑና የተቅበዘበዙትን አይደለም፡፡ እውነት የሚቀድስ ኃይል ነው፣ ነገር ግን ጀግናዋ ቤተ ክርስቲያን ድል ነሺ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፡፡ በስንዴው መኻከል እንክርዳዶች አሉ፡፡ ‹‹ሔደን ብንለቅመው ትወዳለህን›› የሚል ነበር የአገልጋዩ ጥያቄ ነገር ግን ጌታው መለስ ‹‹አይሆንም እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከርሱ ጋር አንዳትነቅሉ›› ማቴ ፲፫፣፳፰-፳፱፡፡ የወንጌል መርበብ መልካካሞቹን አሣዎች ብቻ የሚይዝ ሳይሆን መጥፎዎቹንም ጭምር ነው ጌታም የርሱ የሆኑትን ብቻ ያውቃል፡፡CCh 102.1

    ከአምላክ ጋር በትህትና እንሔድ ዘንድ ተግባራችን ነው፡፡ እንግዳ የሆነ አዲስ መልእክት መሻት የለብንም፡፡ ያምላክ ምርጦች በብርሃን ውስጥ ለመሔድ የሚሞክሩት ባቢሎን እንደሆኑ ማሰብ የለብንም፡፡ ፩12 1T362;CCh 102.2

    በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፉዎች ቢኖሩም እስከ ዓለምም ፍጻሜ ድረስ ቢሆኑም እንኳ በነዚህ መጨረሻ ቀናት ቤተ ክርስቲያኒቱ በኃጢአት በረከሰውና በቀጨጨው ዓለም ብርሃን መሆን አለባት፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ደካማና ጎደሎ ሆና ልትገሥፅም ልታስጠነቅቅም ልትመክርም የሚስፈልጋት ብርትሆንም ቅሉ ክርስቶስ ከፍ ያለ ከበሬታ የሚሰጣት በምድር ያለችው ዓላማ ናት፡፡ ዓለም በሰብዓዊና በመለኮታዊ አማካዮች ተባባሪነት የሱስ በጸጋው በመለኮታዊ ምሕረቱ በሰው ልቦች ውስጥ ሙከራዎች የሚያደርግበት የሥራ መደብር ነው፡፡ ፪22T355;CCh 102.3

    እግዚአብሔር የተለየ (ዕውቅ የሆነ) ሕዝብ በምድር ቤተ ክርስቲያን የሆነች ለማንኛውም ሁለተኛ ያልሆነች ነገር ግን እውነትን ለማስተማር ላምላክም ሕግ ልትበቀል ችሎታ ካላቸው ከሁሉ በላይ የሆነች አለው፡፡ እግዚአብሔር በአምላክ የተሾሙ ወኪሎች ይኸውም የሚመራቸው ሰዎች የቀኑን ሙቀትና ሸክም የቻሉ የክርስቶስን መንግስት በዓለማችን ለማስፋፋት ከሰማያዊ መሣሪያዎች ጋር ተባብረው የሚሠሩ አሉት፡፤ እንግዲህ ሁሉም ከነዚህ ምርጥ ወኪሎች ጋር ተባብረው በመጨረሻም የጻድቃን ትዕግሥት ካላቸውና ያምላክ ትእዛዛትን ከሚጠብቁና የየሱስ ሃይማኖት ካላቸው መኻከል ይገኙ፡፡32TT361, 362;CCh 102.4