Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ደህንታችን ከክርስቶስ ጋርና እርስበርሳችን መተባበር ብቻ ነው፡፡

    ዓለም በክርስቲያናት መኻከል ያለውን አለመተባበር አተኩሮ በመመልከት ላይ ነው፡፡ አለማመንን በጣም ይደሰቱበታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በሕዝቡ መኻከል መለወጥ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ በዚህ መጨረሻ ቀናት ከክርስቶስ ጋርና እርስ በርሳችን መተባበር ብቻ ለኛ መድኅን ነው፡፡ ሰይጣን ወደ ቤተ ክርስቲያን አባሎቻችን እያመለከተ ‹‹ተመልከቱ እነዚህ ሰዎች በክርስቶስ ሰንደቅ ዓላማ በታች እየቆሙ እርስ በርሳቸው እንደምን ይጠላላሉ እነሱ የጦር ኃይሎቼን ከመዋጋት ይልቅ እርስ በርሳቸውን በመዋጋት በይበልጥ ኃይላቸውን ሲያባክኑ ሳለ እነሱን የምንፈራበት ነገር የለም›› ለማለት እንዲቻለው አናድርግ፡፡CCh 85.2

    መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ደቀ መዛሙርት ስለ ተነሳው አዳን የነፍሳት ደህንነት ስለ ሆነው አንዱን ምኞታቸውን ይሰብኩ ዘንድ ወጡ፡፡ ከጻድቃን ጋር በነበራቸው የትብብር ጣፋጭነት ተደሰቱ፡፡ ርህሩሆች አሳቢዎች ራስን ክጂዎች ለእውነት ሲሉ ማናቸውንም መሥዋዕት ሊያደርጉ ፈቃደኞች ነበሩ፡፡ እርስ በርሳቸው ዕለት ዕለት በሚያደርጉት ትብብር ክርስቶስ እንዲገልጹ ያዛቸውን ፍቅር ገለጹ፡፡ ራስን ባለመውደድ በተናገሩት ቃላትና አድራጎቶች በሌሎች ልቦች ውስጥ ይህንኑ ፍቅር ያቀጣጥሉ ዘንድ ተጣጣሩ፡፡CCh 85.3

    መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ የሐዋርያትን ልቦች የሞላውን ፍቅር ምዕመናን ዘወትር እንዲወዱ ነበር፡፡ ‹‹እንደ ወደድኋችሁ እላንትም ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ›› (ዮሐንስ፲፫፡፴፬) ላለው አዲሱ ትእዛዝ በፈቃደኝነት በመታዘዝ ወደፊት እንዲገሠግሡ ነበር፡፡ ፍላጎቶቹን ለመፈጸም እንዲቻላቸው ከክርስቶስ ጋር አጥብቀው እንዲተባበሩ ነበር፡፡ በጽድቁ ሊያጸድቃቸው የሚችለው የመድኃኒታችን ኃይል ያላቀ (የተከበረ) እንዲሆን ነበር፡፡CCh 85.4

    ነገር ግን የቀደምቶች ክርስቲያኖች በእርስበርሳቸው ጉድለቶችን ይፈላልጉ ጀመሩ፡፡ በስህሕተት ላይ በማረፍ ለግፍ መነቃቀፍ ሥፍራ ሰጥተው መድኅንንና እርሱ ለኃጢአተኞች የገለጸውን ታላቅ ፍቅር ሳያዩ ቀሩ፡፡ በውጫዊ የዘልማድ ሥነ ሥርኣቶች የጠበቁ ሆኑ፣ ስለ ሃይማኖትም ልበ ወለድ ታሪክ አሳቢዎች በመነቃቀፋቸው የበለጠውን ጥብቆች ሆኑ ሌሎችን በመንቀፍ ቅንዓት አድሮባቸው የገዛ ስህተቶቻቸውን ረሱ፡፡ ክርስቶስ ስለ ወንድማማችነት ፍቅር ያስተማራቸውን ትምህርት ረሱ፡፡ ከሁሉም የሚያሳዝነው ስለሚደረስባቸው ጥፋት አላወቁም፡፡ ደስታና ፍስሐ ከሕየወታቸው እንደ ተወገደና ወዲያውም የእዚአብሔርን ፍቅር ከልባቸው አስወግደው በጨለማ ውስጥ መዳከራቸውን አልተገነዘቡም፡፡CCh 86.1

    ሐዋርያው ዮሐንስ የወንድማማችነት ፍቅር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየመነመነ (እየቀዘቀዘ) መሔዱን ተገነዘበ ስለዚህ በዚህ ሐሳብ ላይ በተለይ ጸና፡፡ እርበርሳቸው ዘወትር ፍቅር እንዲኖራቸው እስከ ዕለተ ሞቱ ምዕመናንን መከረ፡፡ ለቤተ ክርስቲያናት የጻፋቸው መልእክቶቹ በዚህ ሐሳብ የተመሉ ናቸው፡፡ ‹‹ወዳጆቼ ሆይ እርሱ በርሳችን እንዋደድ›› ሲል ይጽፋል ‹‹ፍቅር ከእግዚአብሔር ናትና›› … እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኳልና በርሱ እንድንበት ዘንድ፡፡ … ወዳጆቼ ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ የወደደነ ከሆነ ለኛም እርስበርሳችን እንዋደድ ዘንድ ይገባናል›› ፩ ዮሐንስ መል ፬፣፯-፲፩፡፡CCh 86.2

    ዛሬ በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የወንድማማችነት ፍቅር በብዙ ጎድሎዋል፡፡ ብዙዎች መድኃኒታችንን እንወዳለን የሚሉ በክርስቲያናዊ ኅብረት ከነሱ ጋር የተባበሩትን ለመውደድ ችላ ይላሉ፡፡ እኛ ባንድ ኃይማኖት ያንድ ቤተ ሰብ አባሎች ነን ሁላችንም የዚያው የሰማያዊ አባት ልጆች ያው የተባረከው የዘላለም ሕይወት (ያለመሞት) ተስፋ ያለን ነን፡፡ እንግዲህ ባንድነት የሚያስተሳስረን ማሠሪያ እንደምን የጠበቀና የጸና ሊሆን ይገባል፡፡ የዓለም ሕዝብ ኃይማኖታችን የሚቀድስ አርአያ በልባችን ውስጥ የሚያስገኝ እንደሆነ ለማየት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ በሕይታችን ውስጥ ያለውን ጉድለት ሁሉ በምግባራችንም የምንገልጸውን ግድፈት ሁሉ ይመለከቱ ዘንድ ፈጣኖች ናቸው፡፡ እንግዲህ ኃይማኖታችንን እንዲነቅፉብን ምንም ምክንያት አንሰጥ፡፡ ፪28T240— 242;CCh 86.3