Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ችግረኞችን እንደምን እንደምንረዳ፡፡

    ችግረኞችን የመርዳት ዘዴ (መቶድ) በጥንቃቄና በጸሎት ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለጥበብ አምላክን መሻት አለብን ባጭሩ ከሚያዩ ሟቾች የበለጠ ለፈጠራቸው ፍጥረቶች እንደምን እንደሚጠነቀቅ ያውቃልና፡፡ እርዳታቸውን ለሚለምን ሁሉ ያለ ጥንቃቄ የሚሰጡ አንዳንዶች አሉ፡፡ በዚህ የሚሳሳቱ ናቸው፡፡ ችግረኞችን ለመርዳት ስንሞክር፤ የቀናውን እርዳታ ዓይነት ልናደርግላቸው መጠንቀቅ አለብን፡፡ በተረዱ ጊዜ የተለየ የችግረኛ ዓላማ ራሳቸውን ለማድረግ የሚቀጥሉ አሉ፡፡ የሚደገፉበት ማናቸውም ነገር መኖሩን እስከሚያዩበት ጊዜ ድረስ ተደጋፊዎች ይሆናሉ፡፡ ለነዚህ ያልተገባ ጊዜ በስጠትና ጥንቃቄ በማድረግ እንዲማግጡ፤ ረዳተ ቢሶች፤ ብኩኖችና መሻትን የማይገዙ እንዲሆኑ እናደፋፍራቸው ይሆናል፡፡CCh 127.1

    ለድሆች ስንሰጥ፤ ‹ለብኩርንነት የማደፋፍር ነውንነ መርዳቴ ነውን ሰዎች እነሱን መጉዳቴ ነው› ብለን ማሰብ አለብን፡፡ ራሱን ኑሮ ሊያተርፍ የሚችል ማንም ሰው በሌሎች ላይ ለመታመን መብት የለውም፡፡CCh 127.2

    ያምላክ የሆኑ ወንዶችም ሴቶችም ማስተዋልና ጥበብ የላቸው ሰዎች ለድሆችና ችግረኞች መጀመሪያ ለኃይማኖት ቤተሰበ ለመጠንቀቅ ሊሾሙ ይገባል፡፡ አነዚህ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሪፖርት አቅርበው ምን ሊደረግላቸው እንደሚገባ መመካከር ተገቢ ነው፡፡ ፰86T277, 278;CCh 127.3

    እግዚአብሔር ይህን መልእክት የሚቀበሉትን ድሆች ቤተሰብ ሁሉ እንዲጠነቀቁላቸው አላፊ እንዲሆኑ አይፈልግም፡፡ ይህን ቢያደርጉ ተቀማጭ ገንዘብ የሚያልቅባቸው ስለሆነ ሰባኮቹ ወደ አዳዲስ ጣቢያዎች መግባትን መተው ይኖርባቸዋል፡፡ ከመትጋትና ከኢኮኖሚ ጉድለት የተነሣ ብዙዎች ድሆች ናቸው፤ በሚገባ ገንዘብን እነደምን እንደማጠቀሙበት አያውቁም፡፡ ሲረዱዋቸውም የሚጐዳቸው ነው፡፡ አንዳንዶች ሁልጊዜ ድሆች የሚሆኑ ናቸው፡፡ በተቻላቸው ጥቅም ማግኘት የሚገባቸው ከሆነ ለጉዳያቸው መርዳት አያስፈልግም ነበር፡፡ መልካም አገማመት የላቸውም፤ብዙም ቢሆን ትንሽም ቢሆን ሊያገኙ የሚላቸውን ገንዘብ ሁሉ ያባክናሉ፡፡CCh 127.4

    እነዚህ መልእክትን ሲቀበሉ፤ ከሐብታሞች ወንድሞቻቸው እርዳታ ሊያገኙ የሚገባቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ የነበራቸው አለኝታ ባይፈጸምላቸው ቤተ ክርስቲያ ኒቱን ይወቅሳሉ በኃይማኖታቸው የማይኖሩ እንደሆኑ ይከስሱዋቸዋል፡፡ በዚህ ነገር ተሣቃዮች መሆን የሚገባቸው እነማን ናቸውና ያመላክ ጉዳይ ሊቀጭጭ ይገባልንይ በልዩ ልዩ ሥፍራዎችም ያለው ግምጃ ቤት ለእነዚህ ትላልቅ የድሆች ቤተሰቦች ለመጠንቀቅ ሊያልቅ ይገባልንይ ወላጆች ተሣቃዮች መሆን አለባ ቸው በጠቅላላው ሰንበትን ከተቀበሉ በኋላ ከበፊቱ ይልቅ በታላቅ እጦት ላይ ሆነው መቸገር የለባቸውም፡፡ ፱917272, 273;CCh 127.5

    እግዚአብሔር ድሆቹን በየቤተ ክርስቲያን ዳርቻዎች (ወሰኖች) ውስጥ እንዲሆኑ ይተዋቸዋል፡፡ እነሱ በመኻከላችን ሁልጊዜ መሆን አለባቸው፤ ጌታም ለነሱ እንዲጠነቀቁ የግል ኃላፊነትን በቤተ ክርስቲያን ሁሉ አባሎች ላይ ያሳርፋል፡፡ እኛ ኃላፊነታችንን በሌሎች ላይ መጫን የለብንም በኛ ወሰኖች ውስጥ ላሉት፤ ክርስቶስ በኛ ሥፍራ ቢኖር ኑሮ ይገልጽ የነበረው ፍቅርና ርህራኄ መግለጽ አለብን፡፡ እንዲሁም በክርስቶስ መሥመሮች ለመሥራት እንዘጋጅ ዘንድ በዲሲፕሊን መሠልጠን አለብን፡፡ ፲106T272;CCh 128.1