Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፰—ምስክሮችና አንባቢው፡፡

    ለሰብዓ ዓመታት ኤሌን ጂ ኋይት እግዚአብሔር የገለጸላትን ነገሮች ተናገረች ፤ ጻፈችም፡፡ ብዙ ጊዜያት፤ ምሥክሮቹ የተሰጡት ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የተሳሳቱትን ለማረም ነው፡፡ ብዙ ጊዜያትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲከተለው ስለሚፈልግበት እርምጃ ያመለክቱ ነበር፡፡ በየጊዜም ምሥክሮቹ ስለ ኑሮ አኳኋን ስለ ቤትና ቤተ ክርስቲያን የሚያወሱ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባሎች እነዚህ መልእክቶችን እንዴት ተቀበሉ?CCh 29.1

    ኃላፊዎች የሆኑ መሪዎች የተገለጸው የትንቢት ሥጦታ አገላለጹ እውነት መሆኑን ራሳቸው ለማረጋገጥ ከሥራዋ አቋም ስራዋን መረመሩ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ፤ «ትንቢትን አትናቁ፡፡ ሁሉን ፍተኑ በመልካሙም ተያዙ” ሲል ይመክረናል፡፡ ፩ ተሰሎንቄ ፭፡፳፡፳፩፡፡ የነቢዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መፈተኛዎች በሚስስ ኋይት ሥራ ላይ ምሥክርነቱ ቀርቦአል፡፡ ይኸውም፤ እንዲህ ስትል ጽፋለችና ያላት መሆንዋ ነው ፤CCh 29.2

    «ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር ነው ፤ አለበለዚያ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ከሰይጣን ጋራ በችርካነት ምንም ነገር አያደርግም፡፡ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የሠራሁት ሥራዬ የእግዚአብሔርን ማኅተም ይዞአል፤ አለበለዚያ የጠላት ማኅተም መሆኑ ነው፡፡ በጉዳዩ ከገሚስ ጐዳና የሚሠራ ስራ የለም»፡፡CCh 29.3

    መጽሐፍ ቅዱስ ነቢይ የሚፈተንበትን አራት መፈተኛዎች ይሰጣል፡፡ የሚስስ ኋይት ሥራ እያንዳንዱን ፈተና የሚቋቋም ነው፡፡CCh 29.4

    ፩፤ የእውነተኛው ነቢይ መልእክት ከእግዚአብሔር ሕግና ከነቢያት መልእክቶች ጋር ስምምነት ያለው መሆን አለበት፡፡ (ኢሳያስ ፰ ፳)፡፡CCh 29.5

    የኢ ጂ ኋይት ጽሑፎች የእግዚአብሔርን ሕግ ከፍ ያደርጋሉ ፤ እንዲያውም ወንዶችንም ሴቶችንም በሙሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ይመራሉ፡፡ እርሷ መጽሐፍ ቅዱስ የሃይማኖትና የግብረገብ ሕግ ፤ ታላቅም ብርሃን እንደሆነና ጽሑፎችዋም «አነስተኛ ብርሃን» የሆኑ የሚያነቧቸውን ሁሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመሩ እንደሆነ ታመለክታለች፡፡CCh 29.6

    ፪፤ የእውነተኛው ነቢይ ትንቢቶች መፈጸም አለባቸው፡፡ (ኤርሚያስ ፳፡፰፱)፡፡CCh 29.7

    የሚስስ ኋይት ሥራ ሕዝብን በመምራት ከዚያ ከሙሴ ጋር በጣም የሚመሳሰል ሁኖ ሳለ ፤ ሆኖም ስለሚሆኑት ብዙ ሁኔታዎች በትንቢታዊ አኳኋን ጽፋለች፡፡ የማተሚያ ቤት ሥራችን በ፲፰፻፵፰ ዓ.ም እ.ኤ.አ ሲጀመር ዓለምን እንደምን በብርሃን የሚከብ ሆኖ የሚያድግ መሆኑን ተናገረች፡፡ ዛሬ ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች ዋጋቸው ባመት ከ20,000,000 በላይ የሚገመቱትን ጽሑፎች (መጻሕፍት) አትመው ያወጣሉ፡፡CCh 29.8

    ፲፰፻፺ ዓ.ም እ.ኤ.አ ዓለም ጦርነት እንደማይሆንና ሺሁ ዓመት ሊነጋ ነው ብሎ በተናገረ ጊዜ ኤሌን ኋይት እንዲህ ስትል ጻፈች ፤ «ዓውሎ ነፋስ መምጣቱ ነው፤ ለቁጣውም መዘጋጀት አለብን፡፡ በሁሉም በኩል መከራ እናያለን፡፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ መርከቦች ወደ ጥልቅ ባሕሮች ይሠምጣሉ፡፡ መርከቦች ወደ ታች ይሠምጣሉ ፤ ሰብዓዊም ሕይወት በሚልዮን ይሠዋል»፡፡ ይህም በመጀመሪያውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ተፈጸመ፡፡CCh 29.9

    ፫፤ እውነተኛው ነቢይ የሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ አምላክም የሰውን ሥጋ መልበሱን ይናገራል፡፡ (፩ ዮሐ መል ፬፡፪)CCh 30.1

    ዘ ደ ዛየር ኤፍ ኤጅስ (የዘመናት መኞት) የተባለውን መጽሐፍ ስናነብ የኤሌን ጂ ኋይት ሥራ በዚህ መፈተኛ የተመዛዘነ እንደሆነ ይገልጸዋል፡፡ እነዚህን ቃላት ልብ አድርገህ ተመልከት፡፡CCh 30.2

    «የሱስ ባባቱ ዘንድ ሊቆይ በተቻለው ነበር፡፡ የሰማይን ክብር ይዞ የመላእክትን እጅ መንሳት በመቀበል በኖረ ነበር፡፡ ግን በትረ መንግሥቱን ባባቱ እጅ መልሶ ከዩኒቬርስም (ከዓለማትም) ዙፋን ወደ ታች ሊወርድ መረጠ ፤ በጨለማ ለሚኖሩት ብርሃን ለጠፉትም ሕይወትን ያመጣ ዘንድ»፡፡CCh 30.3

    ሁለት ሺህ ዓመታት ሊሆን ከተቃረበው ጊዜ በፊት ምሥጢራዊ የሆነ ድምፅ በሰማይ ከእግዚአብሔር ዙፋን ፤ «እነሆኝ እኔ እመጣለሁ” የሚል ተሰማ፡፡ «ቁርባንን መሥዋዕትንም አልሻህም ነገር ግን ሥጋዬን አዘጋጀኽልኝ፡፡ … እነሆኝ እኔ እመጣለሁ፡፡ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለኔ ተጽፍዋል ፈቃድህን አደርግ ዘንድ አቤቱ»፡፡ ዕብ ፲፡፭-፯፡፡ በነዚህ ቃላት ውስጥ ከዘላለማዊ ዘመናት ጀምሮ ተሠውሮ የነበረው ሐሳብ መፈጸሙ ይነገራል፡፡ ክርስቶስ ዓለማችንን ጐብኝቶ የሰውን ሥጋ መልበስ ሆነበት፡፡ … ይፈልጉት ዘንድ በዓለምም ፊት ምንም ውበት አልነበረውም ፤ ሆኖም ሥጋ የለበሰው አምላክ የሰማይና የምድር ብርሃን ነው፡፡ ክብሩ ተጋርዶ ነበር፤ ወዳዘንተኞችና ወደ ተፈተኑትም ሰዎች ይቀርብ ዘንድ ታላቅነቱና ግርማው ተሠወሩ»፡፡CCh 30.4

    ፬ ምናልባት የእውነተኛው ነቢይ ዋናው መፈተኛ በሕይወቱ በሥራውና በትምህርቶቹ አርአያነት ይገኝ ይሆናል፡፡ ክርስቶስ ይህንኑ መፈተኛ በማቴዎስ ፯፣፲፭፣፲፮፡፡ ‹‹ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ›› ሲል ተናገረ፡፡CCh 30.5

    የኤሌን ጂ ኋይትን ሕይወት ስንመረምር ከትምህርቶችዋ ጋር በመስማማትና ከነቢዩ ተስፋ ምናደርገውን በመጠበቅ እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት ኖረች ማለት አለበን፡፡ የትንቢትን መንፈስ ምክሮች የተከተሉትን በሕይወት ኖረች ማለት አለብን፡፡ የትንቢትን መንፈስ ምክሮች የተከተሉትን በህይወታቸው የተገለጸውን ፍሬ ስንመለከት መልካም መሆኑን እናያለን፡፡ ምስክሮቹ መልካም ፍሬ አፍርተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ስንመለከት፣ በነዚሁ ምክሮች ወደ ልዩ ልዩ የተግባር መሥመሮች መመራታችንን ስናውቅ የሚስስ ኋይት ሥራ ከዚሁ መፈተኛ ጋር ሚመዛዘን መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ ከሰብዓ ዓመታት በላይ በተጻፉት ጽሑፎች ውስጥ የትምህርቱ ኅብረት ለተሰጣት ሥጦታ እውነተኝነት ደግሞ ዓይነተኛ ምሥክርነት ይመሰክራል፡፡CCh 30.6