Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ‹‹የሰንበትን ቀን አስብ›› ፡፡

    ጌታ በአራተኛ ትእዛዝ ፣ መጀመሪያ ላይ # አስብ ; ከብዙዎቹ ከትዳርና ከጉዳይ ጣጣዎች መካከል ፣ አው የሕጉን የተማላ ፍላጎት ከመፈፀም ራሱን ነፃ ለማውታት የሚፈተን እንደሆነ ወይም የተቀደሰውን ጠቃሚነቱን የሚረሳ መሆኑን አወቀ ስለዚህ ፣ የሰንበትን ቀን አስብ ትቀድሰው ሀንድ ሲል ተናገረ ፡፡ ዘፀዓት ፳፡፰CCh 44.2

    ሳምንት ሁሉ ሰንበትን በሐሳባችን መያዝና በትእዛዙ መሠረት እንጠብቀው ዘንድ ዝግጅት ማድረግ አለብን ፡፡ ሕጋዊ ነገር ስሆነ ሰንበትን እንድንጠብቅ ብቻ አይደለም ፣ በሕይወትም ሥራ ሁሉ ላይ የሚያሰገኘውን መንፈሳዊ ጥቅም ማስተዋል አለብን ፡፡ በነሱና በእግዚአብሔር መካከል ምልክት መሆኑን ሰንበት የሚመለከቱ ፣ የሚቀድሳቸው አምላክ መሆኑንም የሚያሳዩ የመንግስቱን ደንቦች(ፕርንስፕልስ) የሚያመለክቱ ናቸው የመንግስቱን ሕጎች ዕለት ተዕለት ፀሎታቸው ይሆናል፡ ሁሉ ቀን በመልካም ሥራ ብርሃናቸው ለሌሎች ይበራል፡፡CCh 44.3

    ለእግዚአብሔር ሥራ ለክንውኑ በሆነው ረገድ ሁሉ የመጀመሪያው ድል ነሺነት በቤት ሕይወት መሆን አለበት፡፡ እዚህ ለሰንበት ዝግጅት መጀመር አለበት፡፡ ሳምንቱን ምሉ ቤታቸው፣ ልጆቻቸው ለላይኛው ግቢዎች የሚዘጋጁበት ትምህርት ቤት እንደሆነ ወላጆች ያስቡ፡፡ ቃሎቻቸው የቀና ቃላት ይሁኑ፡፡ ልጆቻቸው ሊሰሙ ያልተገቡ ቃላት ከከንፈሮቻቸው አያምልጡ፡፡ መንፈሳቸው ከብርስጭት ነጻ ይሁን፡፡ ወላጆች በሳምንቱ ውስጥ ለርሱ ታሰለጥኑ ዘንድ ልጆችን በሰጣችሁ ቅዱስ አምላክ ፊት ኑሩ፡፡ ሁሉም በሰንበት በጌታ መቅደስ ውስጥ ያመልኩት ዘንድ እንዲዘጋጁ በቤታችሁ ያለችውን ትንሹአን ቤተክርስቲያን ለርሱ አሠልጥኑ፡፡ በየጧትና ማታ ለእግዚአብሔር ልጆቻችሁን በደሙ የተገዙ ውርስ አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡ እግዚአብሔርን ማፍቀርና ማገልገል ከፍ ያለ ተግባራቸው እንደሆነ አስተምሩዋቸው፡፡CCh 44.4

    ሰንበት እንዲህ ሲታሰብ ሥጋዊው ጉዳይ በመንፈሳዊው ላይ ጣልቃ ይገባ ዘንድ አይፈቀድለትም፡፡ ለስድስቱ የሥራ ቀናት የሆነውን ተግባር ለሰንበት ማስቀረት አይገባም፡፡ አምላክ ባረፈበትና እረፍት ባደረገበት ቀን በጸሎት አገልግሎቱ ተካፋዮች ለመሆን እጅግ የደከምን (የሰለቸን) ሁነን፣ በሳምንቱ ውስጥ በሥጋዊ ሥራ ኃይሎቻችን ይህን ያህል የተዳከሙብን አይሆኑም፡፡CCh 45.1

    በሳምንቱ ሁሉ ውስጥ ለሰንበት ዝግጅት ቢደረግም አርብ ዕለት የተለየ የዝግጅት ቀን መሆን አለበት፡፡ በሙሴ አማካይነት ጌታ ለእሥራኤል ልጆች፣ ‹‹ነገ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕረፍት ነው፡፡ የምትጋግሩትን ጋግሩ ወጥም የምትሰሩትን ስሩ ከርሱ የቀረውንም ለነገ ጠብቁት›› አላቸው፡፡ ‹‹ሕዝቡም ኢየዞሩ ይለቅሙት (መናን) ነበሩ፡፡ በወፍጮም ይፈጩት ወይም በሙገጫ ይወቅጡት ነበሩ፡፡ በምንቸትም ይቀቅሉት ነበሩ፡፡ እርሱንም እንጎቻ ደርጉት ነበሩ›› ዘፀዓት ፲፮፣፳፫ ዘሁልቁ ፲፩፣፰ ለእሥራኤል ልጆች ከሰማይ የተላከላቸውን እንጀራ በማዘጋጀት ረገድ የሚደረገው አንዳች ነገር ነበር፡፡ ጌታ ይህ ሥራ አርብ ዕለት በመዘጋጃ ቀን ሊደረግ እንደሚገባ ነገራቸው፡፡CCh 45.2

    ዓርብ ዕለት ሰንበት ዝግጅቱ ይፈጸም፡፡ ልብስ ሁሉ በዝግጅት መሆኑን ምግብም ሁሉ መሠራቱን እይ፡፡ ጫማዎቹ ይጠረጉ ገላም መታጠብ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ የሚቻል ነው፡፡ ደንብ ብታደርግ ልታደርገው ትችላለህ፡፡ ልብሶችን ለመጠቃቀም፣ ምግብን ለመሥራት አለማዊ ተድላ ልንሻበት ወይም ለማናቸውም ዓለማዊ ሥራ ሰንበትን መስጠት የለብንም፡፡ ከፀሐይ ግባት በፊት ዓለማዊ ሥራ ይወገድ፣ ዓለማዊ ወረቀቶችንም ገለል ማድረግ ነው፡፡ ወላጆች ሥራችሁንና ለምን ሐሳብ እንደሆነ ለልጆቻችሁ ግለጹላቸው እነሱም እንደ ትእዛዙ ሰንበትን ይጠብቁ ዘንድ በዝግጅታችሁ ተካፋይ ይሁኑ፡፡CCh 45.3

    የሰንበትን መጨረሻ ጊዜ አጥብቀን (በቅናት) መጠባበቅ አለብን፡፡ ጊዜው ሁሉ የተቀደሰ ቅዱስ ጊዜ መሆኑን አስብ፡፡ ከተቻለ፣ አሠሪዎቹ ለሠራተኞቻቸው ከዓርብ ቀትር ጀምሮ ሰንበት እስኪጀመር ሰዓታት መስጠት አለባቸው፡፡ የጌታን ቀን በጸጥታ አእምሮ እንዲቀበሉት ለዝግጅት ጊዜ ስጣቸው፡፡ በእንዲህ ያለ እርምጃ በሥጋዊ ነገሮች እንኳ ምንም የሚጎድልህ የለም፡፡CCh 45.4

    በመዘጋጃ ቀን ልናስብበት የሚገባን ሌላ ሥራ አለ፡፡ በዚህ ቀን በወንድሞች መኻከል በቤተሰብ ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው መለያየት ሁሉ ሊወገድ ይገባል፡፡ መማረርና ቁታ ክፋትም ከነፍስ ይወገድ፡፡ በትሑት መንፈስ፣ ‹‹እርሱ በርሳችሁ ተናዘዙ በኃጢአታችሁ አንዱም ላንዱ ይጸልይለት እንድትፈወሱ›› ያዕቆብ ፭፣፲፮፡፡CCh 45.5

    በሰማይ አምላክ ፊት የተቀደሰውን ሰንበት ማፍረስ ሆኖ የሚቆጠረው ነገር ሳይነገር ወይም ሳይደረግ ቀርቶ በሰንበት ሊነገር ወይም ሊደረግ አይገባም፡፡ እግዚአብሔር በሰንበት እለት ሥጋዊ ሥራን እንድንተው ብቻ አይደለም የሚፈልገው አእምሮ በተቀደሱት ሐሳቦች ላይ ያርፍ ዘንድ እንዲሰለጥንም ነው፡፡ ስለ ዓለማዊ ነገሮች በመነጋገር፣ ቀላልና የቀልድ ጨዋታ በመጫወት አራተኛውን ትእዛዝ በገሃድ ይተላለፉታል፡፡ በአእምሮ ትዝ የሚለንን ማናቸውንም ነገር ወይም ሁሉን ነገር መነጋገር የገዛ ቃላችንን መነጋገራችን ነው፡፡ ከቀናው መራቅ ሁሉ ወደ ባርነትና ኩኔኔ ይመራናል፡፡ ፫32T703;CCh 45.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents