Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    መንፈስ ቅዱስ እስከ ፍጻሜ በውስጣችን ይኖራል፡፡

    ክርስቶስ መለኮታዊ የመንፈስ ቅዱስ አነቃቂነት (ኃይል) ከተከታዮቹ ጋር እስከ ፍፃሜ እንደሚሆን ተናገረ፡፡ ነገር ግን ተስፋው እንደሚገባ አልተከበረም፤ ስለዚህ አፈጻጸሙ እንደሚቻል ሁኖ አለታየም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ በትንሹ የታሰበበት ነገር ነው፤ ውጤቱም ተስፋ ያደረጉት ያህል ብቻ ነው፤ ይኸውም የመንፈሳዊ ድርቀት፤ መንፈሳዊ ጨለማነት ፤ ብልሹነትና ሞት ነው፡፡ ትናንሽ ነገሮች ሐሳብን ይይዛሉ፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እድገትና ልማት የሚያስፈልጋትንና ሌሎችን በረከቶች ሁሉ በምላት የሚያመጣው ወሰን የሌሉው ምላቱ ቢሰጠውም እንኳ መለኮታዊው ኃይል የጐደለው ነው፡፡CCh 162.1

    የወንጌልን አገልግሎት አቅመቢስ የሚያደርገው የመንፈስ ቅዱስ መታጣት ነው፡፡ መማር፤ አክሊት፤ አንደበታምነት (አፈጮሌነት) የተፈጥሮ ወይም የተገኘው ሥጦታ ሁሉ ሊጨበጡ ይቻላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ካልተገኘበት ልብ አይነካም፤ ማንም ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር አይመለስም፡፡ በሌላም በኩለ እነሱ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት ቢያደርጉ፤ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች የነሱ ከሆኑ ደቀመዛሙርቱ እጅግ ድሆችና መሐይሞች የሆኑ ለልቦች የሚናገረው ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ እግዚአብሔር በዓለማት (በዩኒቨርስ) ውስጥ እጅግ ከፍ ያለ አነቃቂነት (ኃይል) ያጎርፉ ዘንድ መስኖች ያደርጋቸዋል፡፡CCh 162.2

    ለእግዚአብሔር መቅናት በታላቅ ኃይል ለእውነት ይመሰከሩ ዘንድ ደቀመዛሙርትን አንቀሳቀሳቸው፡፡ ይህ ቅናት ስለሚያድነው የፍቅሩ ታሪክ ፤ ስለ ክርስቶስና ስለ ተሰቀለው ለመናገር ቁርጥ ሐሳብ እናደርግ ዘንድ ልባችንን ማጋለ አይገባምን? ከልብ ለሆነው ጽኑ ጸሎት መልስ ሁኖ ያምላክ መንፈስ ዛሬ መጥቶ ለአገልግሎት ሰዎችን በኃይል የሚሞላቸው አይደለምን? እንግዲያውስ ለምንድን ነው ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ የደከመችና መንፈሰ ቢስ የሆነችው፡፡ ፬48T21,22;CCh 162.3

    መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን አባሎቻችንን ሐሳቦች ሲገዛ (ሲገታ) በቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ አሁን ከሚታየው በአነጋገርና በአገልግሎት ፤ በመንፈሳዊነት በጣም ከፍ ያለ ደረጃ ይታያል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባሎች በሕይወት ውኃ ይረካሉ (ይለመልማሉ) ሰራተኞችም በአንድ ራስ በክርስቶስ ሥር የሚሠሩ ጌታቸውን በመንፈስ፤ በቃል ፤ በአድራት ይገልጻሉ፤ የገባንበትን ታላቁን የመጨረሻ (የሚዘጋውን) ሥራ ወደፊት ለማፋጠን እርስ በርሳቸውን ያደፋፍራሉ፡፡ እግዚአብሔር ልጁን ለኃጢአተኞች ደህንነት እንዲሞት እንደላከው ለዓለም ምሥክርነትን የሚመሰክር ጥሩ የሆነ የኅብረትና የፍቅር መጨማመር ይሆናል፡፡ መለኮታዊ እውነት ከፍ ይላል፤ እንደሚነደው መብራት ሲበራ፤ በይበልጥ ደግሞ በግልጽ እናስተውለዋለን፡፡ ፭58T21,22;CCh 162.4

    የእግዚአብሔር ሕዝብ በበኩላቸው ምንም ጥረቶች ባያደርጉ ነገር ግን የሚያለመልማቸው በነሱ ላይ ወርዶ ስህተቶቻቸውን እንዲያስወግድላቸውና ግድፈ ቶቻቸውን እንዲያርምላቸው ቢጠባበቁት ከሥጋና ከመንፈስ እርኩሰት እንዲያነጻቸውና በሶስተኛው መልአክ ከፍ ባለው ጩኸት ውስጥ ለመግባት እንዲያስማማቸው (ተገቢዎች እንዲያደርጋቸው) በዚያ ላይ ቢታመኑ ጐደሎዎች (ቀልለው) ሆነው እንደሚገኙ ታየኝ፡፡ የሚያለመልመው (ዕረፍት የሚሰጥ) ወይም ከአምላክ የሆነው ኃይል፤ አምላክ የሚያዛቸውን ሥራ በመሥራት ማለት ከሥጋና ከመንፈስ እርኩሰት ሁሉ ራሳቸውን በማንጻት በፈርሀ እግዚአብሔር ቅድስናን በመፈጸም ለርሱ ራሳቸውን ባዘጋጁት ላይ ብቻ ይወርዳል፡፡ ፮61T619.CCh 162.5