Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፫—አምላክን ለመገናኘት ተዘጋጅ፡፡

    የጌታን መምጫ ማዘግየት የማይገባን መሆን አየሁ፡፡ መልአኩ «በምድር ላይ ለሚመጣው ተዘጋጁ ፤ ተዘጋጁ ፤ ምግባራችሁ እንደ ኃይማኖታችሁ ይሁን” አለኝ፡፡ ሐሳብ በአምላክ ላይ ሊጣል እንደሚገባና አርአያችን ለእግዚአብሔርና ለእውነቱ መናገር እንዳለበት አየሁ፡፡ የማንጠነቀቅና ቸልተኞች ስንሆን ጌታን ልናከብር አንችልም፡፡ ተስፋ የሌለን ስንሆን ልናመሰግነው አንችልም፡፡ ለራሳችን ነፍስ ደህንነት እንድናገኝና ሌሎችን እንድናድን ትጉዎች መሆን አለብን፡፡ ዋና ጉዳያችን ሁሉ ከዚህ ጋር ሊያያዝ አለበት ፤ ከዚህም ሌላ ያለን ነገር ሁለተኛው መሆን አለበት፡፡CCh 41.1

    በሰማይን ውበት አየሁ፡፡ መላእክት የፋስሐ መዝሙሮቻቸውን ሲዘምሩ ለየሱስ ምሥጋና ክብርና ውዳሴ ሲያቀርቡ ሰማሁ፡፡ በዚያን ጊዜ አስደናቂ ስለሆነው የእግዚአበሔር ልጅ ፍቅር አንዳች ነገር ለገነዘብ ቻልሁ፡፡ እርሱ በሰማይ የነበረውን ምሥጋና፤ ክብርንም ሁሉ ትቶ ፤ በደህንነታችን በጣም ስለተደሰተ ቁጣንና መናቅን ሰውም በርሱ ላይ ሊቆልልበት የቻለውን ሁሉ በትዕግሥትና በገርነት ቻለ፡፡ እርሱ ቆሰለ ተመታ ፤ ተደቀቀ፡፡ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተዘረጋ ፤ እጅግ አሰቃቂ በሆነው አሟሟት ተሠቃየ፡፡ ከሞት ሊያድነነን በደቡ ታጥበን በሚያዘጋጅልን መኖሪያዎች ከርሱ ጋር እንድንኖር የሰማይንም ብርሃንና ክብር እንድንደሰትበት፤ መላእክትም ሲዘምሩ ለመስማትና ከነሱ ጋር ለመዘመር ከሙታን እንነሳ ዘንድ፡፡CCh 41.2

    ሰማይ ሁሉ በደህንነታችን መደሰቱን አየሁ፤ እንግዲህ ቸልተኞች እንሁንን? ብንድንም ፤ ብንጠፋም እንደ ትንሽ ነገር ተመልክተነው የማንጠነቀቅ እንሁንን? የተደረገልንን መሥዋዕት እንናቀውን (እናቃልለውን)፡፡ አንዳንዶች ይህን አድርገዋል፡፡ የተሰጣቸውን መሕረት ተሳልቀውበታል፤ እግዚአብሔርም ፊቱን ይቋጥርባቸዋል፡፡ የእግዚአብሔርን መንፈስ ሁልጊዜ ማሳዘን የለም፤ እንግዲህ ቢያሳዝኑት ይለያቸዋል፡፡ ሰዎችን ለማዳን እግዚአብሔር ሊያደርግላቸው የሚቻለው ሁሉ ከተደረገ በኋላ ፤ የሱስ የሰጣቸውን መሕረት ማቃለላቸውን (መናቃቸውን) በሕይወታቸው ቢያሳዩ ሞት ፈንታቸው የሆናል፤ በውድም የሚዛ ይሆናለ፡፡ እነሱ ሊቀበሉ ያልፈቀዱትን ደህንነት ሊዋጅላቸው ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰማውን ጭንቀት ሊሰማቸው አለባቸውና የሚያስፈራ ሞት ይሆንባቸዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ዘላለማዊው ሕይወትንና የማይጠፋ ርስትን እንዳጡ ይገነዘባሉ፡፡ ነፍሳትን ለማዳን የተደረገው ታላቅ መሥዋዕት ከዋጋ የሚቆጠሩ መሆናቸውን ያሳየናል፡፡ ክቡር ነፍስ አንድ ጊዜ ሲጠፋ ለዘላለም መጥፋቱ ነው፡፡CCh 41.3

    አንድ መልአክ በእጆቹ ሚዛኖች ይዞ ቁሞ የእግዚአበሔርን ሕዝብ በተለይም የወጣቶችን ሐሳቦችና ጉዳይ ሲመዝን አየሁ፡፡ በአንዱ ሚዛን ውስጥ ወደ ሰማይ የሚያዘነብሉ (የሚያጋድሙ) ሐሳቦችና ጉዳይ ነበሩ፤ በሌላውም ውስጥ ወደ ምድር የሚያዘነብሉ ሐሳቦችና ጉዳይ ነበር፡፡ በዚህም ሚዛን ውስጥ የታሪክ መጻሕፍት ንባብ ሁሉ የልብስ አለባበስና የታይታ፤ የከንቱነት የትዕቢት ይህን የመሳሰሉ ሁሉ ተከተውበት ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ሚዛኖች ይዘው ቁመው ልጆቹ ነን የሚሉትን ፤ ማለት በዓለም ዘንድ የሞትን ለአምላክም ሕያዋን ነን የሚሉትን ሐሳባቸውን የሚመዝኑ ሲሆን እረ እንዴት ያለ ጥብቅ ጊዜ ነው በምድር ሐሳቦች ከራቱነትና ትዕቢት የተመላው ሚዛን በፍጥነት ወደ ታች ቁልቁል ሔደ፡፡ ክብደት በክብደት ላይ ተጫጫነ ከሚዛኑም ተንከባለለ ወደ ሰማይ ያዘነበለው በሐሳቦችና በጉዳይ የተመላው ወደ ላይ በፍጥነት ብድግ አለ፤ ሌላውም ወደ ታች ቁልቁል ሔደ እረ ምንኛ የቀለለ ነበር ይህን አንዳየሁት አድርጌ ላወሳ እችላለሁ ፤ ዳሩ ግን መልአኩ ሚዛኖችን ይዞ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሐሳቦችና ጉዳይ ሲመዝን እንዳየሁት በሐሳቤ ውስጥ የተቀረጸብኝን ጥብቅና ጥልቅ የሆነውን ሐሳብ ልሰጥ ከቶ አይቻለኝም፡፡ መልአኩም አለኝ ፤ «እንግዲህ ያሉት ወደ ሰማይ ሊገቡ ይችላሉን? የለም ፤ የለም ፤ ከቶ አይገቡም ፤ አሁን ያላቸው ተስፋ ከንቱ መሆኑን ንገሪያቸው ፤ በፍጥነትም ንስሐ ካልገቡና ደህንነት ካላገኙ መጥፋት አለባቸው»፡፡CCh 41.4

    የአምልኮት መልክ ማናቸውንም የሚያድን አይደለም፡፡ ሁሉም የጠለቀና ሕያው የሆነ ሁኔታ (ልምምድ) ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህ ብቻ በመከራ ጊዜ ያድናቸዋል፡፡ በዚያን ጊዜ እንዴት ያለ ዓይነት እንደሆነ ሥራቸው ይፈተናል፤ ወርቅ ፤ ብርና ክቡር ደንጊያዎች ከሆነ በእግዚአብሔር ድንኳን መሠወሪያ ውስጥ ይሸሸጋሉ፡፡ ሥራቸው እንጨት ድርቆሽና ገለባ ከሆነ ከአምላክ የቁጣው መዓት ምንም ሌጠብቃቸው አይችልም፡፡CCh 42.1

    ብዙዎች በመኻከላቸው ካሉት ጋር ራሳቸውን እንደሚለኩና ሕይወታቸውን ከሌሎች ሕይወት ጋር እንደሚያመዛዝኑ አየሁ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባም፡፡ ከክርስቶስ በቀር ማንም ምሳሌ ሆኖ የተሰጠን የለም፡፡ እርሱ እውነተኛ ምሳሌያችን ነው ፤ እርሱን በመከተል እያንዳንዱ ብልጫ እንዲኖረው መጣጣር አለበት፡፡ እኛ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሠራተኞች ነን አለበለዚያ ከጠላት ጋር አብሮ ሠራተኞች ነን፡፡ ከክርስቶስ ጋር እንሰበስባለን፤ ወይም ወዲያ እንበትናለን፤ እኛ ቁርጠኞች በምሉ ልብ ክርስቲያኖች ነን፤ አለበለዚያ ጨርሰን አይደለንም፡፡ ክርስቶስ «ሥራህን አወቅሁ ብርድ ትኩስም እንዳይደለህ ምነው ብርድ በሆንክ ወይስ ትኩስ፡፡ ነገር ግን ለብ ያልህ ነህና የበረድህ ያይደለህ የተኰስህም፡፡ እኔ ካፌ እተፋህ ዘንድ አለኝ” ይላል፡፡ ራእይ ፫፡፲፭-፲፮CCh 42.2

    ራስን መካድ ወይም ራስን መሠዋት ወይምን ለእውነት መቸገር (መሠቃየት) ምነ እንደሆነ ማወቅ አንዳንዶች እንዳዳገታቸው አየሁ፡፡ ዳሩ ግን ማንም መሥዋዕት ሳያደርግ ወየ ሰማይ የሚባ የለም፡፡ ራስን የመካድና የመሥዋዕት መንፈስ ሊወደድ ይገባል፡፡ አንዳንዶች ራሳቸውን ፤ አካሎቻቸውን በእግዚአብሔር መሠውያ ላይ አልሠውም፡፡ ችኩል ወረተኛ ወደ ሆነው አመል ያደላሉ ፤ በፍትወታቸውም ይደሰታሉ የእግዚአብሔርን ጉደይ ችላ ብለው ወደ ራሳቸው ጉደይ ያደላሉ፡፡ ለዘለዓለም ሕይዋት ማናቸውንመ መሥዋዕት ማቅረብ የሚፈቅዱ ያገኙታል ፤ ስለዚህ ለዚሁ መቸገር ይጠቅማል ፤ ራስን ለዚሁ መስቀልና ጣዖትን ሁሉ መሠዋት ይጠቅማል፡፡ እጅግ ታላቅ የሆነው ዘልዓለማዊው የክብር ክብደት ሁሉን ነገር ይውጣል ፤ የምድራዊ ደስታን ሁሉ ከንቱ ያደርገዋል፡፡CCh 42.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents