Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በከተሞች መሥራት

    እነሆ ታላቅ ሥራ መሠራት በሚኖርበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ በወንጌል እንደተተነበየው ምድሪቱ አምላካዊውን ቃልተርባለች፡፡ ለተራቡ ነፍሳት የሕይወት እንጀራ ሊሰጥ ይገባል፡፡ ይህን ሥራ ራሱን ለጌታ አገልግሎት ቀድሶ ለሰጠው መንገድ ጠራጊ ከመስጠት የበለጠ የተሻለ ዕድል አይኖርም፡፡ የከበረውን ወቅታዊ እውነት የያዙ በሺ የሚቆጠሩ መጻሕፍት በታላላቅ ከተሞች ነዋሪዎች ቤት ውስጥ ሊገኙ ይገባል፡፡ Southern Watchman, Nov. 20, 1902.ChSAmh 209.1

    ለነፍሳትን ደኅንነት መድኅን የሚሆኑ የተባረኩ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በኅትመት ሥራዎቻችን ቀርበዋል፡፡ መጽሔቶቻችንንም ሆነ ጋዜጦቻችንን በመሸጥ ሥራ ተሳታፊ መሆን የሚችሉ አያሌ ወገኖች አሉ፡፡ እየጠፉ ያሉትን ነፍሳት የማዳን ምኞት እንዲያድርብን ጌታ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ ሰይጣን የተመረጡትን እንኳ ለማሳት በሥራ የተጠመደ እንደመሆኑ ጊዜው በንቃት የምሠራበት ነው፡፡ መጻሕፍቶቻችንም ሆኑ መጽሔቶቻችን የሕዝብ አትኩሮት እንዲያገኙ በማድረግ ወቅታዊውን እውነት የያዘውን ወንጌል ሳንዘገይ ወደ ከተሞቻችን ማዳረስ ይጠበቅብናል፡፡ ተግባራችንን ከግብ ለማድረስ መንቀሳቀስ አይኖርብን ይሆን?— Testimonies, vol. 9, p. 63. ChSAmh 209.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents