Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የብርቱ ልፋትና መሥዋዕትነት ፋና ወዎች

    በወጣቶቻችን ላይ ያለንን መተማመን ገልጠን ልናሳይ ይገባል፡፡ ብርቱ ልፋትና መሥዋዕትነት በሚጠይቀው በእያንዳንዱ አገልግሎት ወጣቶቻችን ፈር ቀዳጅ ሚና ሲጫወቱከፍተኛ የሥራ ጫና የተሸከሙ የክርስቶስ አገልጋዮች ደግሞ ከባድ ፍልሚያ ላይ የተሰማሩትን የመንከባከብ፣ የመምከርና የመባረክ _ አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል፡፡-Counsels to Teachers, pp. 516, 517. ChSAmh 42.2

    ወጣቶች ለአገልግሎት ይፈለጋሉ፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎት ሊሰጡ ወደሚችሉበት የአገልግሎት መስክ እንዲመጡ ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ ቤተሰብን ከሚያስተዳድሩና ከሚመሩ ጋር ሲነጻጸሩ ወጣቶች እምብዛም ጫና የሌለባቸና ከኃላፊነት ነፃ እንደመሆናቸው በሥራው ለመሳተፍ ከሌሎች ይልቅ ይበልጥ አመቺና ተስማሚ ናቸው፡፡ በተጨማሪ ወጣቶች ከአዲስ የአየር ንብረትና ማኅበረሰብ ጋር በፍጥነት ራሳቸውን ማለማመድ ስለሚችሉ እንደነዚህ ያሉትን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በተሻለ ተቋቁመው ማለፍ ይችላሉ፡፡—Counsels to Teachers, p. 517. ChSAmh 42.3

    በቤታቸው ትክክለኛውን ትምህርት የቀሰሙ ወጣቶች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ሥልጠና እንዲወስዱጥሩ ሆኖ የታቀደና በታማኝ አገልግሎት ያልተሸራረፈ እውነት አንግበው ወደ አዳዲስ ስፍራዎች እንዲያመሩ ሊበረታቱ ይገባል፡፡ በከተማ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ አገልጋዮቻችንና በሥራው ልምድ ካካበቱ ሠራተኞቻችን ጋር ተባባሪ በመሆን የምርጥ ሥልጠና ባለቤት ይሁኑ፡፡ ራሳቸውን በመለኮታዊው ምሪት ሥር በማዋልና በሥራው በሳል ተሞክሮ ባላቸው ወገኖች ጸሎት በመደገፍ መልካምና የተባረከ አገልግሎት ይስጡ፡፡ የወጣትነት አፍላ ጉልበታቸውን ተጠቅመው አገልግሎታቸው በሥራው በሳል ተሞክሮ ካላቸው ጋር ኅብር እንዲፈጥር ሲያደርጉ የሰማይ መላእክትን አብሮነት ያገኛሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አገልግሎት መስጠታቸው በሚያስገኝላቸው ልዩ መብትና ጥቅምይዘምራሉ፣ ይጸልያሉ፣ _ እምነታቸውን ያሳድጋሉ እንዲሁም በጀግንነትና በነጻነት ይሠራሉ፡፡ የሰማይ ወኪሎች መገኘት ለእነርሱና ለአገልግሎት አጋሮቻቸው የሚያጎናጽፋቸው ልበ ሙሉነትና መታመን--የጸሎት ህይወት ባለቤት፣ አመስጋኞችና ግልጽ ሆኖ የተቀመጠው እውነት ተከታዮች ያደርጋቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 119. ChSAmh 43.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents