Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወንጌል አገልግሎት ሥርዓተ ትምህርት

    ብዙዎች ተገቢው ትምህርትና ማበረታታት ተሰጥቶአቸው ሥራውን እንዴት መጀመር እንዳለባቸው ሥልጠና ከተሰጣቸው በሥራው ለመሰማራት ፈቃደኞች ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን የክርስቲያን ሠራተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ሊሆን ይገባል፡፡ አባላት የጥቅስ ንባብን እንዴት ማቅረብ እንዳለባቸው፣ የሰንበት ትምህርት ጥናት መርኀ ግብርን እንዴት መምራትና ማስተማር እንዳለባቸው፣ _ ለደኻው _ መስጠት ስለሚኖርባቸው እርዳታና ለታመመው ማድረግ ስለሚኖርባቸው እንክብካቤ እንዲሁም ላልተለወጠው ልብ በምን መልኩ መሥራት እንደሚኖርባቸው ሊማሩ ይገባል፡፡ የጤና ትምህርት፣ የምግብ ዝግጅትና ሌሎች አያሌ ክርስቲያናዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ መስኮች ሊኖሩ የግድ ነው፡፡ ትምህርቱ በቃል ብቻ ሳይወሰን ተግባርን ያካተተና በሙያው በቂ ልምድ ባካበቱ መምራን ሊሰጥ ይገባል፡፡ መምራን ከሕዝቡ ጋር አብረው በመሥራት የመሪነት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ሌሎች ደግሞ ከእነርሱ ጋር ኅብረት ፈጥረው ከምሳሌነታቸው ይማሩ፡፡ በአንድ ነገር መልካም ምሳሌ መሆን ብዙ ትምህርቶች ከማስተማር የላቀ ዋጋ አለው:፡-The Ministry of Healing, p. 149.ChSAmh 82.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents