Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 8—ክርስቲያን ኃይሎችን ማደራጀት

    የተደራጀ ኃይል አስፈላጊ ነው

    ያለን ጊዜ በጣም አጭር እንደመሆኑ ግዙፍ ሥራ መሥራት የሚያስችለንን ኃይላችንን ማደራጀት የግድ ነው፡፡-Testimonies, vol 9, p. 27. ለክርስቲያን ጥረት መሰረት የሆኑትን በጥሩ ሁኔታ የተደራጁ አነስተኛ ቡድኖችን ማወቀር አስፈላጊ መሆኑን እውነት የሆነው ጌታ ገልጦልኛል፡፡Testimonies, vol. 7, pp. 21, 22. ChSAmh 100.1

    በጥሩ ሁኔታ የተዋቀሩ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አገልጋይ አባላትን ያካተቱ ቡድኖች በእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ይሥሩ፡፡-Review and Herald, Sept. 29, 1891.ChSAmh 100.2

    በእያንዳንዱ ከተማ በመልካም ዲሲፕሊን በታነጹ ሠራተኞች የተደራጁ አንድ ወይም ሁለት ሳይሆኑ ብዙ ጓዶች ሊኖሩ ይገባል፡፡-General Conference Bulletin, 1893, p. 37.ChSAmh 100.3

    በቤተ ክርስቲያኖቻችን አገልግሎት ሰጭ የጓደኛሞች ኅብረቶች ሊኖሩ ይገባል፡፡ የተለያዩ ሰዎች-ሰዎችን በማጥመዱ ሥራ ግንባር ይፍጠሩ፡፡ ነፍሳትን በእርክስና ከተሞላው ምድር ወደ አዳኙ የክርስቶስ ፍቅር ንጽህና ለመሰብሰብ ጥረት ያድርጉ፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 21.ChSAmh 100.4

    የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በምድር የተመሰረተችው የወንጌል አገልግሎት ለመስጠት እንደመሆኑ በከፍታም ሆነ በዝቅታ የሚገኘው፣ ሐብታሙም ሆነ ደኻው የእውነትን መልእክት የሚሰማበት ዘዴ ተቀይሶለት መመልከት የጌታ ምኞት ነው፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 29. ChSAmh 101.1

    በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ የአባላት መጠን ከፍተኛ ከሆነ፤ አነስተኛ አኻዝ እንዲኖረው ይደረግ፡፡ ይኸውም የሚረዳው ለራሳቸው ለአባላት ለመሥራት ብቻ ሳይሆን አማኝ ላልሆኑት አገልግሎት ለመስጠት ጭምር ነው፡፡ በአንድ ቦታ ላይ እውነትን የሚያስተውሉ ሰዎች መጠን ከሁለትና ከሦስት የማይበልጥ ከሆነ ራሳቸውን በቡድን፣ በቡድን ያዋቅሩ-Testimonies, vol. 7, p. 22.ChSAmh 101.2

    በአንድ የውጊያ ዐውድ ስኬታማ ውጤት ለማስዝብ የሥርዓትና ደንብ መከበር አስፈላጊ ከሆነ፤ በተመሳሳይ ተጨባጭ ውጤት ለማግኘት በተሳተፍንበት የጦር ሜዳ ውሎ ከእነዛኞቹ ተቃራኒ ኃይላት የላቀ፣ እጅግ የከበረ ጸባይ ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡Testimonies, vol. 1, p. 649.ChSAmh 101.3

    ግዚአብሔር የሥነ ሥርዓት አምላክ ነው፡፡ እያንዳንዱ ከሰማይ ጋር ቁርኝት ያለው ነገር ፍጹም በሆነ ሥርዓት ውስጥ ይገኛል፡፡ ለሥርዓት ተገዢ መሆንና ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን ውስጥ መመላለስ የሰማይ ሠራዊት እንቅስቃሴ ማሳያ ነው፡፡ ስኬት ሊጎበኝ የሚችለው በሥርዓት የሚመራውንና እርስ በርሱ ስምሙ የሆነውን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእስራኤል ዘመን ከሆነው ያላነሰ ሥርዓትና ደንብ ዛሬም በአገልግሎት ውስጥ ተጠብቆ እንዲኖር ይጠይቃል፡፡ ለእርሱ እየሠሩ ያሉ ሁሉ በዘፈቀደና ያለ dቅድ ሳይሆን በማስተዋልና በብልሃት ያገልግሉ፡፡ ሥራውን በታማኝነትና በትክክል የሚያከናውን የአምላካዊው አዎንታ ማረጋገጫ የሆነው ማኅተም ይታተምለታል፡፡ Patriarchs and Prophets, p. 376.ChSAmh 101.4

    የቤተ ክርስቲያን አባላት የገዛ እምነታቸውን አጠንhረውና በዕውቀት በስለው የተቀበሉትን ብርሃን እንዴት ወደ ሌሎች ማስተላለፍ እንዳለባቸው መረዳት የሚያስችላቸው በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ ሥራ ሊሠራ የግድ ነው፡፡ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ለሌሎች ሲያስተላልፍ እምነቱ ይጠነክራል፡፡ በሥራ ላይ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት አለው፡፡ እኛ እያንዳንዳችን ሕያው በሆነው ዐለት ላይ የተገነባን ብርሃን አስተላላፊዎች ነን፡፡ እያንዳንዱ የእግዚአብሔርን ክብር ተቀብሎ በሚያጸባርቅ ክርስቲያን በከበረ ድንጋይ ይመሰላል፡፡— Testimonies, vol. 6, p. 435.ChSAmh 102.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents