Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጥቅጥቅ ብሎ የበቀለውን ችግኝ ዘርዘር አድርገው የሚተhሉ ብልህ አትከልተኞች ያፈልጋሉ

    ሠራተኞች ወደ አውራ ጎዳናውና ጥቅጥቅ ወዳለው ቁጥቋጦ ይሂዱ፡፡ የዛፍ ችግኞች በጥሩ ሁኔታ የሚያድጉበት ዕድል እንዲያገኙእየነቀሉ ወደ የጸሎት አገልግሎትና የአምልኮ ጊዜ ተለያዩ ስፍራዎች የሚተክሉ የችግኝ ንቅለ ተከላ ሠራተኞች ያስፈልጉናል፡፡ በስተ ማዶ ወዳሉ አካባቢዎች ማምራት ለእግዚአብሔር ሕዝቦች የተሰጠ አዎንታዊ ተግባር ነው፡፡ ክፍተት መገኘት በቻለ ቁጥር ለእርሻ የሚሆነውን መሬት የሚመነጥረውና አዳዲስ ተጽእኖ ማሳደሪያ ማዕከላትን የሚያቋቁመው ኃይል ተቀናጅቶ ወደ አገልግሎት የሚገባበት ሥራ ይሠራ፡፡ እውነተኛ የወንጌላዊ ቅንአት ያላቸው-ጉባዔዎችን የማካሄድ ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች ብርሐናቸውንና ዕውቀታቸውን በቅርብም ሆነ በሩቅ ለማሰራጨት ይውጡ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 118.ChSAmh 255.1

    ብዙ ምዕመናንን ያቀፉት የአብዛኞቹ ታላላቅ ቤተ hርስቲያኖቻችን አባላት ተሳትፎ ከአነስተኞቹ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የማይባል ነው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በአንድ ቤተ hርስቲያን ውስጥ እንዲከማች በመፍቀድ ፋንታ እውነት ወዳልተዳረሰበት አካባቢ እንዲበታተን ቢደረግ ታላቅ ሥራ መሥራት በተቻለ ነበር፡፡ ጥቅጥቅ ብለው የተተከሉ ዛፎች በጥሩ ሁኔታ ሊያብቡ አይችሉም፡፡ ነገር ግን አትክልተኛው እጅብ ብለው ካደጉበት ስፍራ ነቅሎ እየዘረዘረ ሲተክላቸው የመቀጨጭም ሆነ የማጠር ችግር አይገጥማቸውም፡፡ ብዙ ምዕመናንን ባቀፉ ታላላቆቹ ቤተ hርስቲያኖቻችን አካባቢ ይኸው ተመሳሳይ ደንብ ሊተገበር ይገባል፡፡ ይህ ሥራ የሚያሻቸው አብዛኞቹ የቤተ hርስቲያን አባሎቻችን መንፈሳዊ ሞት እየሞቱ ይገኛሉ፡፡ የቀጨጩና አጥጋቢ ውጤት ማምጣት ያልቻሉ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ጥቅጥቅ በማለት ፋንታ ዘርዘር ቢደረጉ ጠንካራና ጤናማ ሆነው ለማደግ የሚያስችላቸው በቂ ስፍራ ይኖራቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 8 p. 244.ChSAmh 255.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents