Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኃላፊነትና ተግባር

    የእውነትና የኃይማኖት ነጻነት አርማዎች ቀደም ካሉት ጊዜያት አንስቶ ለምዕተ ዓመታት የወንጌልን መልእክት አጉልተው ማቅረብ በቻሉና ለእግዚአብሔር ምስhር ሆነው ባለፉ አብያተ ክርስቲያናት መስራቾች ከፍ ብለው የተውለበለቡ ቢሆንም በምድር የመጨረሻ ውዝግብ ወቅት ይህ ኃላፊነት ለእኛ ይሰጠናል፡፡ ይህን ታላቅ ስጦታ የመሸከም ኃላፊነት የሚወስዱት እግዚአብሔር በቃሉ ዕውቀት የባረካቸው ይሆናሉ፡፡ አምላካዊውን ቃል እንደ መጨረሻ የሥልጣን እርከን አድርገን ልንቀበል ይገባል፡፡ ሰብዓዊ መንግሥት በለኮት ትእዛዝ ወደ ሥልጣን እንደመጣ በመቀበል ይህን አስተዳደር በሕጋዊ ግዛቶቹ ሁሉ መታዘዝ የተቀደሰ ተግባር መሆኑን መማር ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ትእዛዛት ከእግዚአብሔር ትእዛዛት ጋር ሲወዛገቡ ከሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ልንታዘዝ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከማንኛውም ሰብዓዊ ሕግ በላይ መታዘ ይጠበቅብናል፡፡ “ጌታ እንዲህ ሲል ተናግሮአል” የሚለው አምላካዊ ቃል ወደ ጎን ተደርጎ “ቤተ hርስቲያን እንዲህ ብላለች” ወይም “ንግሥት እንዲህ ብሎአል” በሚል ሊተካ አይገባም፡፡ የhርስቶስ አክሊል ከምድር ገዢዎች የራስ ወርቅ በላይ ከፍ ሊል ይገባል፡፡ The Acts of the Apostles, pp. 68, 69. ChSAmh 222.2

    እኛ እንደ ሕዝብ በእግዚአብሔር የተሰጠንን ሥራ አልሠራንም፡፡ አስገዳጁ የእሁድ ሕግ በሕሊና ነጻነት ዙሪያ ሊያደርስብን ስለሚችለው የከፋ ሁኔታ ግዝጁነት የለንም፡፡ እየተቃረበ ያለውን መቅሰፍት መመልከታችን ወደ ተግባር እንድንሸጋገር ሊያነሳሳን ይገባል፡፡ ማንም ቢሆን አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት መሰረት ጌታ ለሕዝቡ ጋሻ ይሆናል በሚል እሳቤ በተመቻቸ ሁኔታ ተረጋግቶ ክፉው የሚከሰትበትን ጊዜ አይጠባበቅ፡፡ እጆቻችንን አጣጥፈን በጸጥታ የምንቀመጥ ከሆነ ለአምላካዊው ፈቃድ በመሥራቱ ረገድ የሕሊና ነፃነት ተጠብቆ እንዲቆይ የምናበረክተው አንዳችም አስተሰዋጾ አይኖርም፡፡ ለረጅም ጊዜ ችላ የተባለውን ሥራ በስኬት እስክናከናውን አሰቃቂው ወቅት ይዘገይ ዘንድ ወደ ሰማይ የሚወጣ ጽኑና ብርቱ ጸሎት ልናደርግ ይገባል፡፡ አብልጠን በጸሎት እየተጋንና ከልመናችን ጋር ሕብር እየፈጠርን እንሥራ፡፡-Testimonies, vol. 5, pp. 713, 714. ChSAmh 223.1

    ሊመጣ ያለውን አደጋ በማዘግየቱ ረግድ የምንችለውን ሁሉ የማድረግ ኃላፊነት አለብን፡፡ ራሳችንን በበቂ ብርሃን በሰዎች ፊት በማስቀመጥ ጠባብነትንና ትምክvትን የማብረድ ብርቱ ጥረት ይጠበቅብናል፡፡ በሕሊና ነጻነት ዙሪያ ያሉ ተጨባጭ ርዕሰ ጉዳዮችን በመጠየቅና ይህን ነጻነት በሚገድቡ ውሳኔዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ውጤታማ ተቃውሞ ልናደርግ ይገባል፡፡Testimonies, vol. 5 p. 452. ChSAmh 223.2

    እግዚአብሔር ከፊት ለፊታችን አደጋ መኖሩን የሚያሳይ ብርሃን ሰጥቶናል፡፡ ሆኖም ይህን ጉዳይ ወደ ሕዝቡ ለማድረስ አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ከማድረግ ችላ ብለን እንዴት በፊቱ ትክክለኞች ሆነን መቆም እንችላለን? እነዚህን ብርቱ አጽንኦት የሚሹ ወቅታዊ ማስጠንቀቂያዎች ሳናቀርብ በመተዋችን ደስታ ማግኘት እንችል ይሆን?-- Testimonies, vol. 5, p. 712.ChSAmh 223.3

    ብሔራዊ ተሐድሶ አራማጆች በሐይማኖት ነጻነት ላይ ገደብ የሚጥለው ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ሲወተውቱ ቀደምት የኃይማኖት መስራቾች በሕይወት ኖረው እነዚህን ጥረቶች በቅንነትቢከላከሉ ምንኛ መልካም በሆነ ነበር፡፡ ለዚህ ዘመን ያስፈለገው የወቅታዊ እውነት ብርሐን በሕዝባችን ተጠብቆ መቆየት የቻለው በእግዚአብሔር ትእዛዝ አይደለም፡፡ የሦስቱን መላእhት መልእክት እየሰጡ ከሚገኙ አገልጋዮቻችን መሃል ሁሉም የመልእክቱን አንደምታ በጥልቅ አያስተውሉም፡፡ ብዙዎች ለብሔራዊ ተሐድሶ አራማጆች እንቅስቃሴ አነስተኛ አጽንኦት በመስጠታቸው ግዙፍ ትኩረት የመስጠቱን አስፈላጊነት በቅጡ አላሰቡበትም፡፡ እንደውም ይህን ማድረጋቸው ከሦስቱ መላእክት መልክት ያፈነገጡ ጥያቄዎች እንዲነሱ ጊዜ ይሰጣል የሚል ስሜት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ለዚህ ዘመን የተሰጠውን ታላቅ መልእክት በዚህ መልኩ የተረጎሙትን ወንድሞች ጌታ ይቅር ይበል፡፡— Testimonies, vol 5, p. 715. ChSAmh 224.1

    አስገዳጁ የእሑድ ሕግ በአሜሪካ የሚወጣበትን ጊዜ እየተመለከትን ብዙ ዓመታት አሳልፈናል፡፡ አሁን እንቅስቃሴውን ከፊታችን እየተመለከትን እንደመሆኑሕዝባችን ተግባሩን በአግባቡ ይወጣ ይሆን? ብለን እንጠይቃለን፡፡ ለኃይማኖት መብትና ጥቅም መከበር የቆሙ ከፊተኛው ረድፍ እንዲሰለፉ ጥሪ እያቀረብን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከፍ አድርገን በማንሳት የበኩላችንን ድጋፍ ማሳየት አንችል ይሆን? ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ የሚመርጡ -የጨቋኝ እጅ ጫና የሚሰማቸው ጊዜ በፍጥነት እየደረሰ ነው፡፡ የተቀደሱት አምላካዊ ትእዛዛት ሲረገጡ እንዳላየ በዝምታ እያለፍን ለእግዚአብሔር መስጠት የሚኖርብንን ክብር እንንፈግ? ፕሮቴስታንቱ ዓለም ወደ ሮም የማዘንበል ጠባይ እያሳየ ባለበት በዚህ ወቅት--የምንገኝበትን ሁናቴ በጥልቅ ተገንዝበን በመነሳት ከፊታችን ያለውን ፍልሚያ ከትhከለኛ አቅጣጫ እንመልከት፡፡ የመንጋው እረኞች ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው ለዘመኑ የተሰጠውን የወቅቱን መልእክት ያካፍሉ፡፡ በእውነተኛ የሐሰት አስተምህሮ ተቃውሞ ወይም ፕሮቴስታኒዝም መንፈስ ለመነሳሳት በመመኘት ዓለም እስካሁን ላገኘው የኃይማኖት ነፃነት ልዩ መብቶችና ጥቅሞች ዋጋ ሰጥቶእንዲንቀሳቀስ በማድረግ በትንቢቱ መሰረት የምንገኝበትን ስፍራ ለሕዝቦች እናሳይ፡፡Testimonies, vol. 5, p. 716. ChSAmh 224.2

    የአሜሪካ ሕዝቦች በጠላት የተቀናበረውን ይህን በሰብዓዊና ኃይማኖታዊ ነጻነት ላይ የተጋረጠ ብርቱ አደጋ ተቋቁው ለመግታት ሊነሳሱ ይገባል፡፡— Spirit of Prophecy, vol. 4, p. 382. ChSAmh 225.1

    እጆቻችንን አጣጥፈን ከመቀመጥ በቀር ለዚህ ቀውስ መገታት ማበርከት የምንችለው አንዳች ነገር የለ ይሆን?... ለዓመታት ከፈዘዝንበት እንድንነቃ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡- Review and Herald, Dec, 18, 1888. ChSAmh 225.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents