Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 20—ወደ ባለሐብቶችና ተጽእኖ አሳዳሪዎች መድረስ

    ችላ መባል የሌለበት፡

    ወደ ባለ ሐብቶች ለመድረስ የሚያስችለን ሥራ መሠራት ይኖርበታል፡፡ ከሰማይ በአደራ ስጦታ የተቀበሉ ወገኖች ከአንቀላፉበት ነቅተው ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሕያዋንንም ሆነ ሙታንን በሚዳኘው አምላh ተጠያቂነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ባለ ጸጋው እግዚአብሔርን የሚወደውንና የሚፈራውን የእርስዎን አገልግሎት ይሻል፡፡ ብዙውን ጊዜ ባለ ሐብቱ በገንዘቡና በንብረቱ ስለሚመካ አደጋ ውስጥ እንዳለ አይሰማውም፡፡ ህሊናው ዘላለማዊ ዋጋ ወዳላቸው የከበሩ ነገሮች መሳብ ይኖርበታል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 230.ChSAmh 279.1

    በትምvርታቸው፣ በሐብታቸው ወይም በሙያቸው ከፍ ያለውን ደረጃ የተቆናጠጡ ለነፍሳት ደኅንነት ለሚሠራው ሥራ ድጋፍ እንዲያደርጉ አልፎ አልፎ ይጠየቃሉ፡፡ አብዛኞቹ ክርስቲያን ሠራተኞች እነዚህን ሰዎች ቀርበው ለማግባባት ያመነታሉ፡፡ ሆኖም እንዲህ መደረግ የለበትም፡፡ አንድ ሰው በውሃ ውስጥ እየሰመጠ እየተመለከትን ጠበቃ፣ ነጋዴ ወይም ዳኛ ነው ብለን እርዳታችንን ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም፡፡ ሰዎች ባለ ሥልጣን ወይም የትኛውም ዓይነት ሙያ ባለቤት ቢሆኑ ወደ ገደል አፋፍ እየተጣደፉ ሲሄዱ ብንመለከት ወደ ኋላ እንዲመለሱ ከመለመንና ከመወትወት አንቆጠብም፡፡ በተመሳሳይ እየጠፉ ያሉ ነፍሳትን ከማስጠንቀቅ ማንታት የለብንም፡፡ ለዓለማዊ ነገሮች ግልጽ ታማኝነት ካላቸው መሃል አንዳቸውም ችላ መባል የለባቸውም፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 230, 231. ChSAmh 279.2

    ከፍ ባለ ደረጃ የተቀመጡ ነፍሳትን ለመማረክ አድካሚ ሥራ መሥራት ይኖርብናል፡፡ ወደ _ ሠርጉ ግብዣ ይመጡ ዘንድ በጸጋ የተሞላውን ማደሚያ ማቅረብ ይጠበቅብናል፡፡Southern Watchman, March 15, 1904. ChSAmh 280.1

    ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ተለውጠው ወደ ሌሎች ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት ያግዙ ዘንድ የጌታ ምኞት ነው፡፡ የተሐድሶና የማቋቋም ሥራ እንዲሠራ አገልግሎቱን ማገዝ የሚችሉ የከበረውን የእውነት ብርሐን ተመልክተውና በጸባይ ተለውጠው ገንዘባቸውን ለአምላካዊው ሥራ ለማዋል ሲነሳሱ ለመመልከት ጌታ ይመኛል፡፡ በሩቅም ሆነ በቅርብ በማንኛውም የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወንጌል የሚሰሙበትን መንገድ በመክፈት እርሱ ያበደራቸውን በሥራው ላይ እንዲያፈሱ ያደፋፍራቸዋል፡፡ - Testimonies, vol. 9, p. 114. ChSAmh 280.2

    ከፍተኛ ገቢ ካላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚመደቡ ሰዎች ቅንነት በተሞላው ወንድማዊ ፍቅር ሊጠየቁ ይገባል፡፡ በንግድ ዓለም ውስጥ የተሰማሩ፣ በከፍተኛ ኃላፊነት የተቀመጡ፣ የሳይንስ ተመራማሪዎች እንዲሁም የወንጌል መምህራን ሆነው ነገር ግን አእምሮአቸው ለዚህ ዘመን ለተሰጠው እውነት ምላሽ ያልሰጠ ሰዎች ጥሪውን በቅድያ ሊሰሙ ይገባል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ግብዣው ሊቀርብ የግድ ነው፡፡Christ’s Object Lessons, p. 230. ChSAmh 280.3

    ወደ ወንጌል አገልጋዮችና ከፍ ወዳለው የሕብረተሰብ ክፍል ለመድረስ ጥረት ባለመደረጉ ስህተት ተሠርቶአል፡፡ ከእኛ እምነት ያልሆኑ ሰዎች አብልጠው በርቀት ኖረዋል፡፡ የአስተምህሮአቸውን ግልባጭ ለመቀበል ከእነርሱ ጋር አግባብ መፍጠር ባይኖርብንም _ ነገር ግን በጥንቃቄ፣ ChSAmh 280.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents