Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አለማዳላት

    መድኃኒታችን በሰዎች መካከል በአካል በኖረበት ዘመን የድኾችን ዕጣ ፋንታ ተጋራ፡፡ በተግባር ስሜታቸውንና ችግራቸውን ሁሉ ስላወቀው ዝቅተኛ ሠራተኞችን ሁሉ ለማጽናናትና ለማበረታታት ቻለ፡፡ የየሱስን ትምህርት ጽንሰ ሃሳብ በትክክል ያስተዋለ ሰው የመደብ ልዩነት በማድረግ ባለጸጎች ከድኾች የበለጠ መከበር አለባቸው ብሎ ያምንም፡፡The De sire of Ages, p. 73.ChSAmh 334.4

    ብዙም ተስፋ የማይጣልባቸውና የማይስቡ ከሚመስሉ ነፍሳት ፊትዎንሲያዞሩ ክርስቶስ የሞተላቸውን ነፍሳት ችላ እያሉ እንደሆን አስተውለዋል? እርስዎ ለነዚህ ነፍሳት ጀርባዎን የሰጡባት ያቺ ቅጽበት የእርስዎን ርኅራኄ የሚሹባት ወሳኝ ጊዜ ልትሆን ትችላለች፡፡ ሰዎች ለአምልኮ በሚሰባሰቡበት (እያንዳንዱ ጉባዔ ዕረፍትና ሰላም የሚጠሙ ነፍሳት ይኖራሉ፡፡ ምናልባት አንዳንዶች ከቸልተኝነት ጋር የተጎዳኘ ህይወት የሚመሩ ቢመስሉ እንኳ ነገረ ግን ለመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ምላሸ ቢሶች አይደሉም፡፡ እነዚህን ጨምሮ ብዙዎች ለክርስቶስ መሸነፍ የሚችሉባቸው ሁናቴዎች ሰፊ ናቸው፡፡Christ’s Object Lessons, p. 191.ChSAmh 335.1

    አምላካዊውን ቃል ቢቀበሉ ለእኛም ክብር ያመጣልናል በሚል እሳቤ የወንጌልን ጥሪ አጥብበን ለተመረጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ማቅረብ የለብንም፡፡ መልእክቱ ለሁሉም መሰጠት አለበት፡፡ የሱስ ለመቀበል ክፍት የሆኑ ልቦች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ለማስተማር ዝግጁ ነው፡:The De sire of Ages, p. 194. ChSAmh 335.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents