Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስኬታማ እቅድ ማውጣት

    አማኝ ወዳልሆኑ ሕዝቦች ለመድረስ ከሚያስችሉን አዳዲስ እቅዶች አንዱ መከር የመሰብሰብ የወንጌል ዘመቻ ማድረግ ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተተገበረው ይህ አሠራር ለብዙዎች በረከት ከማምጣቱ በተጨማሪ ለወንጌል ሥራ የሚውለውን የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል በማስቻል በብዙ ስፍራዎች ስኬታማ ውጤት አስገኝቶአል፡፡ ከእኛ እምነት ውጪ የሆኑ ሰዎች በባዕድ አገሮች እየተካሄደ ካለው የሦስቱ መላእክት መልእክት ግስጋሴ ጋር የፈጠሩት ትውውቅ ባሳደረባቸው መነሳሳት የሰዎችን ልብና ሕይወት የመለወጥ ኃይል ካለው ከእንዲህ ዓይነቱ እውነት የመማር ብርቱ ፍላጎት አድሮባቸዋል፡፡ በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ወዳሉ ወንዶችና ሴቶች ለመድረስ ተችሎአል--የእግዚአብሔርም ስም ከብሮአል፡፡.--MS., “ Consecrated Efforts to Reach unbelievers,” June 5, 1914.ChSAmh 230.2

    አንዳንዶች ከማያምኑ ሰዎች ስጦታ ስለመቀበል ትክክለኛነት ሲጠይቁ ይስተዋላሉ፡፡ እስቲ ራሳቸውን “እውነተኛው የዚህ ዓለም ባለቤት ማነው?” ብለው ይጠይቁ፡፡ ለመሆኑ ቤቱ፣ መሬቱ፣ ወርቁም ሆነ ብሩ የማን ነው? በምድራችን ያለው የተትረፈረፈ ሐብት የእግዚአብሔር ሲሆን እርሱ ደግሞ ለሚታዘዙትም ሆነ ለማይታዘዙትበሁሉም እጅ አኑሮታል፡፡ ለሥራው ድጋፍ የሚሆን የተትረፈረፈ ገንዘብ ለመለገስ ዓለማዊውም ሆነ ጣኦት አምላኪው እጁን ይዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ልባቸውን ለመንካት ዝግጁ ነው፡፡ ሕዝቦቹ እነዚህን ሰዎች እንዴት በጥበብ ማግባባት እንዳለባቸው ሲማሩና ትኩረታቸውን ወደዚህ ልዩ መብትና ጥቅም መሳብ ሲችሉ ጊዜ ሳይወስድ ያደርገዋል፡፡ ለጌታ ሥራ የሚያስፈልገው ሁሉ አግባብ ባለው ብርሃን ገንዘብና ተጽእኖ ላላቸው ሰዎች ቢቀርብላቸው፤ የወቅታዊው እውነት ተልዕኮ ወደፊት እንዲገሰግስ ሊያደርግ የሚችል የድጋፍ እጃቸውን ሊዘረጉ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከዓለም ተነጥለው ለመመላለስ በመምረጣቸው አያሌ ልዩ መብቶችንና ጥቅሞችን መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡Southern Watchman, March 15, 1904.ChSAmh 231.1

    ጌታ ስለ ሕዝቡ ሲል የነገሥታትንና የገዢዎችን ልብ ዛሬም እየነካ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር ለሥራው ወደፊት መገስገስ ድጋፍ የሚያደርጉ ሰዎችን ሲያነሳሳ ለእርሱ በመሥራት ላይ የሚገኙ አገልጋዮች ለእነዚህ ነፍሳት ያላቸውን ተደራሽነት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የስጦታዎቹ መንስኤ የሆኑ ወኪሎች የእውነት ብርሃን አያሌ በጨለማ የተዋጡ ምድሮች ላይ የሚፈነጥቅበትን መንገድ ሊከፍቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ አምላካዊው ሥራ፣ በክርስቶስ ላይ ሊኖር ስለሚገባ እምነት ወይም ከቃሉ ጋር ዝምድና ላይኖራቸው ቢችልም ነገር ግን ስጦታዎቻቸውን ላለመለገስ መንስኤ የሚሆን አንድም ጉዳይ አይኖርም፡፡Southern Watchman, March 15, 1904.ChSAmh 231.2

    ጌታ ምድራዊውን ቁስ አማኝ በሆኑ እንዲሁም ባልሆኑ ሰዎች እጅ አኑሮአል፡፡ እነዚህ ሰዎች የጌታን ለጌታ በመመለስ በኃጢአት ለወደቀው ዓለም መሠራት የሚኖርበት ሥራ መሠራት ይኖርበታል፡፡ በዚህ ምድር እስከተመላለስንና የእግዚአብሔር መንፈስ ስለ ሰው ልጆች እስከ ቃተተ ድረስ ይህን የምንቀበለውን አምላካዊ ውለታ ለሌሎችም የማካፈል ኃላፊት ተሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ስለ ሥራው ክንውን ልባቸውን ከሚነካው ዓለማውያን እየተቀበልን በአምላካዊው ቃል የተገለጠውን የእውነትን ብርሃን መልሰን ለዓለም መስጠት ይጠበቅብናል፡፡Southern Watchman, March 15, 1904.ChSAmh 232.1

    ምንም እንኳ በአጠቃላይ--ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የዓለም ሐብት በክፉዎች እጅ የወደቀ ቢሆንም ነገር ግን የዓለም ሐብትና ንብረት የእግዚአብሔር ነው፡፡ “ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ... የእግዚአብሔር ነው፡፡” ብሩ የእኔ ነው ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ጸባኦት፡፡” “የዱር አራዊት ሁሉ፤ በሺ ተራራዎች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና፡፡ በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤ በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው፡፡ ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ ዓለምና በውጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና፡፡” ክርስቲያኖች የተሰጣቸውን ልዩ መብት፣ ጥቅምና ኃላፊነት በሙላት ተገንዝበው፣ ለትክክለኞቹ መርኅዎች ከፍተኛ ዋጋ ሰጥተውና ተንhባክበው—እያንዳንዱን ከሰማይ የሚላክላቸውን ዕድል የአግዚአብሔርን መንግሥት ለማፋጠን ጥቅም ላይ ማዋል ይኖርባቸዋል፡፡—Southern Watchman, March 15, 1904.ChSAmh 232.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents