Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተምሳሌታዊ አነጋገሮችን መጠቀም

    ሁለቱ ታላላቅ የፍቅር መርኅዎች ከፍ ያለውን ፍቅር ለእግዚአብሔር አምላክ መቸር እንደሚገባንና ራስ ወዳድ ያልሆነውን ፍቅር ለባልንጀራችን መንፈግ እንደሌለብን ይናገራሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ አራትና የመጨረሻዎቹ ስድስት ትእዛዛት በእነዚህ ሁለት መርኅዎች ላይ የተንጠለጠሉ ወይም ከእነርሱ ውስጥ በልጽገው የወጡ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ምሳሌያዊ አነጋገር ተጠቅሞ ከየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በጉዞ ላይ የነበረ ባልንጀራው በወንበዴዎች ሰለደረሰበት ዝርፊያና በሞት አፋፍ እስኪወድቅ ስለ መደብደቡ ለሕግ አዋቂው ገልጾለት ነበር፡፡ ካህኑም ሆነ ሌዋዊው ይህን በሥቃይ ላይ የነበረ ሰው ቢያዩትም ነገር ግን እጅግ ያስፈልገው ለነበረ ነገር ልባቸው ምላሽ ከመስጠት በመቆጠቡ ገለል ብለው አለፉ፡፡ እንደውም ባጠገቡ ላለማለፍ መንገዱን ተሻግረው ጉዞአቸውን በሌላ በኩል አደረጉ፡፡ ከዚያም አንድ ሳምራዊ ሰው በዚያ አቅጣጫ መጣ፡፡ ይህ ለእርሱ ባዕድ የነበረ ሰው እርዳታ እንደሚያስፈልገው ባየ ጊዜ ዝምድ፣ ያገር ልጅነት ወይም ኃይማኖት ሳይል በሥቃይ የነበረውን ሰው ለመርዳት ተንቀሳቀሰ፡፡ ሥቃዩን ለማስታገስ የሚችለውን እንክብካቤ ካደረገለት በኋላ ወደ እንግዳ ማረፊያ ወስዶ የሚያስፈልገውን ሁሉ ወጪ ሸፈነለት፡፡ChSAmh 267.1

    ይv ሳምራዊ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራው መሆኑን ክርስቶስ ተናግሮአል፡፡ ሌዋዊውና ካህኑ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የእነርሱ እርዳታና እገዛ እየተፈለገ ምላሽ የማይሰጡትን የአማኞች ክፍል ይወክላሉ፡፡ ይህ ክፍል በየትኛውም ዓይነት ኃላፊነት ላይ ቢቀመጥም እንኳ አምላካዊውን ሕግ ተላላፊ ነው፡፡ ሳምራዊው መልካም በማድረግ የእርሱን ምሳሌ በተግባር የሚገልጸውን ከክርስቶስ ጋር የተሰማራ እውነተኛ እርዳታ ሰጭ ክፍል ይወክላል፡፡ChSAmh 267.2

    ለአካል ጉዳተኞች ባላቸውን በሞት ተነጥቀው ቀኑ ለጨለመባቸው ሴቶች፣ ለወላጅ ዐልባ ህጻናትና በከፍተኛ እጦት ለሚሠቃዩ ወገኖች ርኅራኄ የሚያሳዩየዘላለማዊ ሕይወት ባለቤት የሚያደርጋቸውን አምላካዊ ፈቃድ እንደፈጸሙ አድርጎ ክርስቶስ ይመለከታቸዋል... ክርስቶስ ለምስኪን ነፍሳት የሚደረጉትን እነዚvን Aበ ቀናነት ያላቸውን በጎ ተግባራት ለእርሱ እንደተደረጉ ይቆጥራል፡፡ መልካሞቹ ተግባራት በሰማይ መዝገብ ይጻፋሉ— የከበረ ሽልማትም ያሰጣሉ፡፡ በተቃራኒው አደጋ ላይ ለወደቀው ባልንጀራቸው ቅንጣት ታከል በጎ ምላሽ ያላደረጉት ካህኑና ሌዋዊው እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ለገዛ ጥቅማቸው ብለው በሰዎች ላይ በደልና ጭቆና የሚያደርሱ ራስ ወዳዶች ክፉ ተግባር በሰማያዊው መዝገብ ላይ ይሰፍራል፡፡ እያንዳንዱ ኢፍትሐዊ ድርጊት፣ ምላሸ ቢስ ግዴለሽነትና ቸልተኝነት በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂነት ይኖረዋል፡፡ በመጨረሻ እያንዳንዱ እንደ በጎ ተግባሩ የተዘጋጀለትን ሽልማት ይቀበላል፡፡ Testimonies, vol. 3, pp. 511-513. ChSAmh 268.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents