Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 9—እንድንነቃ የቀረበልን ጥሪ

    ጥሪ

    በዓለማቀፋዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ እንድንሆን የሚያድመው የወንጌል ደወል ጥሪ በመላው ቤተ ክርስቲያኖቻችን ያስተጋባ፡፡ የግዙፍ እንቅስቃሴ አካል የሆኑት፣ በኃያሉ መሪ የሚመሩት የቤተ ክርስቲያን አባላት በዓይን የማይታዩትን ተባባሪዎቻቸውንና የማይነጥፈውን የዕውቀት ምንጫቸውን እየተጠቀሙ ከቀድሞ የላቀ እምነትና ቅንአት ባለቤት ይሁኑ፡፡ ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር አኑረው በእርሱ እንዲመሩ የሚፈቅዱ ሁሉ በጌታ ገቢራዊ እንዲሆኑ የታቀዱትን በየደረጃው እውን የሚሆኑ ጽኑ hስተቶችን ያስተውላሉ፡፡ ሕይወቱን ለዓለም ሲል በሰጠው በእርሱ መንፈስ የተነኩ ከዚህ በኋላ እንደ ቀድሞው--አንችለውም ብለው _ እጆቻቸውን አጣጥፈው ያለ ሥራ አይቀመጡም፡፡ ሁሉን የሚችለው አምላክ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እንደሚያሟላ ስለሚያወቁ የሰማይን የጦር ትጥቅ ለብሰው፣ ወደውና ፈቅደው በድፍረት ወደ ውጊያው ያመራሉ፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 14.ChSAmh 106.1

    ከእንግዲህ እንንቃ! ጦርነቱ መነሳቱ ነው፡፡ እውነትና ሐሰት የመጨረሻው ውዝግብ ላይ እየደረሱ ነው፡፡ በልዑል አማኑኤል አርማ ሥር ተሰልፈን ዘላለማዊ ሽልማት የሚያስገኝልንን መልካሙን የእምነት ውጊያ እንዋጋ፡፡ እውነት ድል ያደርጋል፤ በእርሱ በወደደን ከአሸናፊዎች በላይ እንሆናለን፡፡ የከበሩት የምህ/ት ጊዜያት እያበቁ ነው፡፡ የሰማዩን አባት እንድናከብርና ለሞተልን ክርስቶስ ነፍሳት የሚድኑበት መንስኤ እንድንሆን ዘላለማዊ ሕይወት የሚያስገኘው ሥራ ተካፋዮች እንሁን፡፡Review and Herald, March 13, 1888.ChSAmh 106.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents