Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አሳማኙ ስብጥር

    ለዓለም አሳማኝ መሆን የሚችለው ከቤተ ክርስቲያን ምስባክ የሚደመጠው አስተምህሮ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው ሕይወት ነው፡፡ መደበኛው የወንጌል ሠራተኛ የወንጌልን ንድፈ ሐሳብ ሲያውጅ በቤተ hርስቲያን በተጨባጭ የሚታየው ቅድስና ደግሞ አምላካዊውን ኃይል ገልጦ ያሳያል፡፡— Testimonies, vol. 7, p. 16.ChSAmh 94.2

    ወንዶችና ሴቶች የቤተ ክርስቲያን አባላት ኃይላቸውን አሳስበው ከአገልጋዩና ከቤተ hርስቲያን መሪዎች ጋር በአንድነት ወደ ሥራው እስከሚገቡ በዚህ ምድር የተጀመረው የእግዚአብሔር ሥራ ፍጻሜ ማግኘት አይችልም፡፡--Gospel Workers, p. 352. ለነፍሳት ደኅንነት መሠራት ከሚኖርበት ሥራ ውስጥ ስብከት አነስተኛውን ክፍል ይወስዳል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ኃጢአተኞችን ስለ እውነት እየወቀሰና በደለኝነታቸውን እንዲመለከቱ እያደረገ በቤተ ክርስቲያን እቅፍ ያኖራቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የራሳቸውን የሥራ ድርሻ ይወጡ ይሆናል _ እንጂ ቤተ ክርስቲያን መሥራት የምትችለውን ሥራ ሊሠሩ አይችሉም፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 69.ChSAmh 94.3

    የእግዚአብሔርን እውነት የማሰራጨት ኃላፊነት ለጥቂት የተቀቡ አገልጋዮች ብቻ ተወስኖ የተቀመጠ አይደለም፡፡ ይልቁንም የእውነት ዘር የhርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን በሚሉ ሁሉ በውሃ ዳር ሊዘራ ይገባል፡፡ Review and Herald, Aug. 22, 1899.ChSAmh 94.4

    የወንጌል ሠራተኞችና የምዕመናን ትብብር አገልጋዮች አስደሳችና አሳማኝ ሰፊ ንግግር ቢያደርጉ፣ ቤተ ክርስቲያንን የመገንባትና የማበልጸግ ሰፊ ሥራ ቢሠራአባላቶቿ እንደ የሱስ ክርስቶስ አገልጋይነታቸው የድርሻቸውን ካላበረከቱ በቀር ሁል ጊዜም አቅመ ቢስና በጨለማ የተዋጠች ሆና ትቀራለች፡፡ ዓለም ክፉና በጽልመት የወደቀች እንደመሆኗ ጽኑና ዘላቂው ተምሳሌነት የበጎው ብርቱ ኃይል ነው፡፡-Testimonies, vol. 4, pp. 285, 286.ChSAmh 95.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents