Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 16—ቤተ ክርስቲያንን የማስፋፋት እንቅስቃሴ

    መለኮታዊ ዕቅድ

    እግዚአብሔር ሕዝቦቹ በአንድ ስፍራ በብዛት ተከማችተው ወይም እጅብ ብለው እንዲገኙ ዓላማው አይደለም፡፡ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በምድር የእርሱ ተወካዮች እንደመሆናቸው በመላው አገር፣ ከተሞችና መንደሮች ተበታትነውና ተሰራጭተው ጨለማ በዋጠው ዓለም የብርሐን ጨረር ይፈነጥቁ ዘንድ የእርሱ እቅድ ነው::Testimonies, vol. 8, p. 244.ChSAmh 247.1

    ሕዝቦችን በአንድ ስፍራ ማከማቸት ወይም ከተለያዩ _ ስፍራዎች አሰባስቦ አነስተኛ ብርታት ወይም ተጽእኖ ሊፈጥሩ በሚችሉበት አንድ አጥቢያ ቤተ hርስቲያን ላይ ማከማቸት እግዚአብሔር እንዲያበራ ያስቀመጠውን ብርሃን አንስቶ ወደ ሌላ ስፍራ መውሰድ ነው::-- Testimonies, vol. 2, p. 633. ChSAmh 247.2

    የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኖች የጌታችንን ዓላማ ቢያስፈጽሙ ኖሮ በጨለማ በተቀመጡትም ሆነ የሞት ጥላ ባጠላባቸው ስፍራዎች የብርሐን ወጋገን በፈነጠቀ ነበር፡፡ ብዙ ቁጥር ያለው አማኝ በአንድ አሰባስቦ ከኃላፊነት በመራቅ ፋንታ መስቀሉን የሚሸከሙ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ወደ ተለያዩ ስፍራዎች በመበተን የክርስቶስ ብርሃን ከእነርሱ ወደ ሌሎች እንዲያንጸባርቅ መፍቀድና እርሱ እንደ ሠራ ለነፍሳት ደኅንነት መሥራት ይገባል፡፡ ይv ሲሆን “የመንግሥት ወንጌል” በፍጥነት እስከ ዓለም ዳርቻ ይሰራጫል፡፡-Thoughts From the Mount of Blessing pp. 42, 43. ChSAmh 247.3

    ወንድሞችና እህቶችበከንቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትመላለሱት ለምንድን ነው? የጠፋውን በግ ምሳሌያዊ ታሪክ በማጥናት በኃጢአት ምድረ በዳ የወደቀውን ነፍስ ለማዳን ብርቱ ጥረት እያደረጋችሁ እንደ እውነተኛ እረኛ ወደፊት ተራመዱ-- እየጠፉ ያሉትን ታደጉ፡፡Review and Herald, Dec. 12, 1893. ChSAmh 248.1

    የቤተ ክርስቲያኖቻችን ፈቃደኛ ወንጌላውያን በብዙ ውጣ ውረድ የጀመሩትን ሥራ በስኬት ማጠናቀቅ ይይችላሉ፡፡ ማንም ቢሆን ለምድራዊው ጥቅም ብቻ ብሎ ወደ አዳዲስ ስፍራዎች አይሂድ፡፡ ነገር ግን ለመተዳደሪያ የሚሆን ገቢ የሚገኝበት ክፍተት ሲገኝ በእውነት ላይ ስር የሰደደ ዕውቀት ያላቸው አንድ ወይም ሁለት ቤተሰቦች በወንጌላዊነት በአንድ ስፍራ ላይ አገልግሎት ለመስጠት ይሂዱ፡፡ ለነፍሳት ያላቸውን ፍቅር እያበለጸጉና ለእነርሱ የመሥራት ሸhም እየተሰማቸው እንዴት ወደ እውነት ሊያመጧቸው እንደሚችሉ ትምህርት ይቅሰሙ፡፡ የኅትመት ውጤቶቻችንን እያሰራጩ፣ ስብሰባዎችን በየቤቶቻቸው እያካሄዱና ከጎረቤቶቻቸው ጋር ትውውቅ እየፈጠሩ በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ሊያድሟቸው ይችላሉ፡፡ በዚvም የመልካሙ ሥራቸው ብርሐን እንዲያንጸባርቅ ማድረግ ይችላሉ፡፡--Testimonies, vol. 8, p. 245.ChSAmh 248.2

    የአገልግሎት ስፍራቸውን ለመለወጥ የሚመኙየእግዚአብሔር ክብር የሚታይባው፣ ለሌሎች መልካም የማድረግ ግላዊ ኃላፊነት የሚሰማቸውና ክርስቶስ ነፍሳትን ለማዳን የከበረ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ የሰጣቸውን ሕዝቦች የሚጠቅምና የሚያድን ተግባር የሚፈጽሙ ወንድሞችተጨባጭ አገልግሎት ሊሰጡባቸው ወደ ሚችሉባቸው አነስተኛ ወይም ከነጨራሹ ምንም ብርሐን ወደ ሌለባቸው ከተሞችና መንደሮች በማምራት በአገልግሎታቸውና ተሞክሮአቸው ሌሎችን ሊባርኩ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ በሁሉም አቅጣጫ የተበተኑ ምስhሮች ይኖሩት ዘንድ የወንጌል ሠራተኞች ወደ ከተሞችና መንደሮች እያመሩና የእውነት ብርሃን ገና ወዳልተዳረሰባቸው ስፍራዎች እየደረሱ የአምላካዊውን ትእዛዛት እውነቶች ከፍ አድርጎ የማውለብለብ ሥራ መሥራት ይፈለግባቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 2, p. 115.ChSAmh 248.3

    ለሌሎች አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ ተካፋይ የመሆንን ያህል ራስን መሥዋዕት አድርጎ የማቅረብ ቅንአት እንዲኖረንና ጠንካራ ብሎም የበለጸገ ጸባይ ባለቤት እንድንሆነ ሊያነሳሳን የሚችል ነገር የለም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ትስስር መፍጠር የሚፈልጉ አያሌ hርስቲያኖች የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን አባላት ጋር ሕብረት በመፍጠር የመጋቢውን ጥንቃቄ በማግኘት ደስተኛ ለመሆን በሚያድርባቸው ምኞት የትላልቅና ባለጸጋ ቤተ hርስቲያኖች አባላት ቢሆኑም ለሌሎች ጥቂት በማድረጋቸው ብቻ ደስተኞች ናቸው:፡ ይህ የሚከተሉት አካሄድ እጅግ የከበረውን በረከት ከማግኘት ይሰርቃቸዋል፡፡ብዙዎች ደስታቸውን መሥዋዕት ላደረጉበት ኅብረት ከፍተኛ ተጠቃሚ በመሆናቸው ለአገልግሎት ወደ ሚጠሩበት ለመውጣትና ኃላፊነትን መሸከም ለመማር ፍላጎታቸው ነው፡፡— The Ministry of Healing, p. 151.ChSAmh 249.1

    አምላካዊውን ሕግጋት የያዘው እውነት ፈጽሞ ያልተሰማባቸውይህ እውነት ከፍ ብሎ ሊውለበለብባቸው የሚገባ በሺ የሚቆጠሩ ስፍራዎች በአሜሪካ ይገኛሉ፡፡ ወደ መከሩ ስፍራ የሚገቡ በሺ የሚቆጠሩ ቢኖሩም ነገር ግን በአሁኗ ሰዓት ያለ ሥራ የተቀመጡትhርስቲያን መሆናቸውን በመጠራጠር እያነከሱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከየሱስ hርስቶስ ጋር ንቁ ኅብረት መፍጠር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን ስለ እነርሱ፡ “hእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን” ሊባል ይችላል፡፡ የሆነ ሰው መጥቶ ወደ ወይን ስፍራው ወስዶ አገልግሎት ላይ እንዲመድባቸው አየተጠባበቃችሁ ነው--ወይስ በሥራው አንዳችም ውጣ ውረድ እንዳይገጥማችሁ የወይን እርሻው ወደ እናንተ እንዲመጣ ይደረግብዬ ብዙዎችን መጠየቅ እወዳለሁ፡፡ መጠበቃችው በከንቱ ነው፡፡ አንገቶቻችሁን ቀና አድርጋችሁ በየትኛውም አቅጣጫ አሻቅባችሁ ብትቃኙ ለመታጨድ የደረሰውን መከር ታያላችሁ፡፡ በቅርብም ይሁን በሩቅ የምትሠሩት ሥራ ታገኛላችሁ፡፡ ከርስቶስ በፍርድ ቀን “መልካምና ታማኝ አገልጋይ” የሚላቸው ስንቶቹን ይሆን? መጨረሻው እየተቃረበ መሆኑን የሚመለከቱት መላእክት በሚያዩት ነገር ምን ሊሰማቸው እንደሚችል አስባለሁ፡፡ የእግዚአብሔርና እርሱ የላከው የየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት አለን እያሉ፣ አንድም ሳይሠሩ እጅብ ብለው ተቀምጠው ፕሮግራሞችን የሚካፈሉ አሉ፡፡ ሰብከቶች የገዛ ነፍሶቻቸውን ካልጠቀሙና ቤተ ክርስቲያንን ካላጠናከሩ ያለመርካት ስሜት ይታይባቸዋል... ለጊዜው ያላቸው የገንዘብ አቅም ገና እውነት ወዳልታወጀባቸው አጥቢያዎች ለመድረስ በቂ ሆኖ ካላገኙት ወይም ከአቅም በታች እየሠራ ከሆነየሱስ እነርሱን ለማዳን የሠራውን ሥራ አይሠሩም ማለት ይሆን?—General Conference Bulletin, 1893, p. 131. ChSAmh 249.2

    ታላቁን የወንጌል ተልዕኮ ወደ ባዕድ አገሮች ብቻ ሳይሆን ወደ ቅርብ አካባቢያችን ጭምር የመውሰድ ብርቱ አስፈላጊነት ይታየናል፡፡ ቅርባችን በሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ነፍሳትን የማዳን ጥረት አልተደረገም፡፡ ወቅታዊውን እውነት የሚያውቁ ቤተሰቦች የራሳቸውን ሳይሆን ነገር ግን አምላካዊውን መንገድ ተከትለው በእነዚህ ከተሞችና መንደሮች እየኖሩና የክርስቶስን ትእዛዛት እያስተማሩ በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ መንፈስ ብርሃን የማያመጡላቸው ለምንድን ነው? ChSAmh 250.1

    ቤተ ክርስቲያን የመልእክቱን መንፈስ በተጨባጭ ስታገኝ አማኞች ሙሉ ኃይላቸውን ተጠቅመው ክርስቶስ የሞተላቸውን ነፍሳት የማዳን ሥራ ይሠራሉ፡፡ _ መልእክቱ _ ወዳልተዳረሰባቸው አዳዲስ ስፍራዎች ይገባሉ፡፡ ለአገልግሎት ያልተቀቡ አገልጋዮች ሳይቀሩ ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች በመሆን ቤተ ክርስቲያናትን እየጎበኙ የቀረውንና ሊከስም ያለውን የማጠናከር ሥራ ይሠራሉ፡፡ የአገልግሎት ሥልጠና ሳይወስዱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ብርሃን ለሌሎች ለማብራት ወዳልተደረሰባቸው መንደሮችና ከተሞች የሚንቀሳቀሱ ይኖራሉ፡፡ እነርሱ ከሚገናኗቸው መሃል አንዳንዶች እጅግ ተስፋ የሚጣልባቸው ባይመስሉም ነገር ግን አስተምህሮአቸውና ምሳሌያቸው የሚያሳድረው ተጽእኖ የእውነትና የጽድቅ ደራሲ የሆነውን ጌታ መስህብ እንዲኖረው አድርጎ የሚያቀርብ፣ ወደ ክርስቶስ ሕብረት የሚያመጣና የመንፈሱ ተካፋዮች ሊያደርጋቸው የሚችል ሊሆን ይገባል፡፡ ChSAmh 250.2

    እውነት በማይታወቅበት ስፍራ የሚያገለግሉ በሥራው ልምድ ያላቸው ወንድሞች ለመሰብሰቢያ የሚያıለግል አዳራሽ ሊከራዩ ወይም ሌላ ምቹ ስፍራ አዘጋጅተው የሚመጡትን ሁሉ ሊያድሙ ይገባል፡፡ ከዚያም ለተሰበሰበው ሕዝብ እውነትን ያስተምሩ፡፡ ስብከት መስበክ ሳያስፈልጋቸው መጽሐፍ ቅዱስ አውጥተው እግዚአብሔር በቀጥታ በቃሉ አማካይነት እንዲናገር ይፍቀዱ፡፡ በስፍራው የተገኘው ታዳሚ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ “ጌታ እንዲህ ይላል” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንዳለ ሊያነቡ ይችላሉ፡፡ በጉልv የሰፈረውን ያልተወሳሰበ የወንጌል እውነት ካነበቡና ካብራሩላቸው በኋላ ይዘምሩ ይጸልዩም፡፡Review and Herald, Sept. 29, 1891, ChSAmh 251.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents