Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሙያ ነክ ትምህርት

    በድኽነት የሚኖሩ ምስኪን ቤተሰቦች እንዴት መተዳደሪያ የሚሆን ገቢ ፈጥረው ቤተሰባቸውን በውጤታማነት መምራት እንደሚችሉ የሚረዳቸው ትምህርት ከመስጠት የተሻለ የወንጌል ሥራ የለም፡፡ የእንዲህ ዓይነቱ እርዳታና ሥልጠና አስፈላጊነት በከተሞች ብቻ የተወሰነ ሊሆን አይገባም፡፡ ለኑሮ እጅግ አመቺና ሁሉም ነገር ተሟልቶባቸዋል በሚባሉት አገሮች እንኳ አያሌ ድኾች በብርቱ እጦት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ አብዛኛው ማኅበረሰብ በቂ ትምህርትና ሥልጠና ማግኘት ባለመቻሉ ቤተሰቦችየቤት ቁሳቁስ፣ አልባሳት፣ የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ መጻሕፍም ሆነ መሰረታዊ ነገሮች ባልተሟሉባቸው ደሳሳ ጎጆዎች ኑሮአቸውን ይገፋሉ፡፡ ጸንፈኛና ጨካኝ ነፍሶች፣ ልፍስፍስና ህመምተኛ አካላዊ ገጽታዎችሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ክፉና የተሳሳተ ልማድ ውጤቶች ገልጠው ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ከስር ጀምሮ ትምህርት ሊያገኙ ይገባል፡፡ በስንፍና የተሞላ፣ በሥራ ያልተጠመደና የተበላሸ ህይወት ሲመሩ በመኖራቸው የቀድሞውን ልማድ ለማረም የሚያስችል ሥልጠና ሊወስዱ የግድ ነው The Ministry of Healing p. 192. ChSAmh 177.2

    በድኽነት የሚኖሩ ወገኖች የሥራ ዕድል ማግኘት ይችሉ ዘንድ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ተቋማት በሚታነጹበት ዙሪያ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው:: የእንጨት ሥራ ባለሙያዎች አንጥረኞች እንዲሁም በተለያየ ጠቀሜታ ባላቸው የሙያ ዘርፎች የተሰማሩበቂ ዕውቀት፣ ሥልጠና ወይም ሥራ የሌላቸውን የማስተማርና የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው፡፡The Ministry of Healing p. 194.ChSAmh 178.1

    በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ከርስቲያኖች ለደኻው መኖሪያ በመሬታቸው ላይ በመቀለስ መሬቱን እንዴት እንደሚያርስና ውጤታማ እንደሚሆን ማሠልጠንና ትምህርት መስጠት ይችላሉ፡፡ የተለያዩ ሰብሎችን፣ አትከልቶችን ወይም ፍራፍሬዎችን እንዴት ማምረት እንደሚቻል በተግባር የታገዘ ሥልጠና ይስጧቸው፡፡The Ministry of Healing p. 193. ChSAmh 178.2

    ለድኾች አገልግሎት መስጠትን አስመልክቶ ለወንዶችና ለሴቶች የሚውሉ ሰፋፊ ዘርፎች አሉ፡፡ በምግብ ዝግጅት፣ በቤት አያያዝ፣ በልብስ ስፌት፣ በነርስነት--ለሁሉም ጠቃሚና አስፈላጊ አገልግሎቶችን መስጠት ይቻላል፡፡ በድኽነት ውስጥ የሚገኙ ወገኖች ስለ ምግብ አሠራር፣ የራሳቸውን ልብሶች እንዴት እንደሚሰፉና እንደሚጠግኑ፣ የታመሙትን እንዴት እንደሚንከባከቡና ቤታቸውን እንዴት በንጽህና እንደሚይዙ ይማሩ፡፡ ወንዶችና ሴቶች ልጆች የወንጌል አገልግሎት የምንሰጥባቸው ዘዴዎች የእጅ ሥራም ሆነ ሌሎች ጠቃሚ ሙያዎችን ይቅሰሙ-The Ministry of Healing p. 194. 30ChSAmh 178.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents