Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተረጋገጠው ሽልማት

    እያንዳንዱ እንደ ችሎታው የሚሠራውን ሥራ የሰጠው እርሱ-የታማኙን አፈጻጸም ሳይሸልም ያልፍም፡፡ እያንዳንዱ ታማኝነትና ጠንካራ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ይታወሳል፤ የእርሱንም ድጋፍ ያገኛል፡፡ “ዘር ቋጥረው እያለቀሱ የተሰማሩ ነዶአቸውን ተሸከመው እልል እያሉ ይመለሳሉ”— Testimonies, vol. 5, p. 395.ChSAmh 369.4

    አገልግሎታችን የቱንም ያህል አጭር ወይም የተመጣጠነ ቢሆን፤ በተረዳነው እየተመላለስን ክርስቶስን የምንከተል ከሆነ ከእርሱ በምናገኘው ሽልማት ደስ እንሰኛለን፡፡ የምድር ታላላቅ ሰዎችና ጠቢባን የተቃወሙትን ደካሞችና ትሁታን ግን ይቀበሉታል፡፡ ወርቃማው የሰማይ በር ራሳቸውን ለሚክቡና ከፍ ከፍ ለሚያደርጉ ሊከፈት አይችልም፡፡ የታበየ መንፈስ ላላቸው መከፈት የማይችሉት ዘላለማዊ ደጆች ለዋሆቹ ህፃናት ወለል ብለው ይከፈታሉ፡፡ ውስብስብ ያልሆነውን እምነትና ፍቅር ጠብቀው ራሳቸውን በአምላካዊው አምሳል ያነጹ ቡሩካን በጌታ ይካሳሉ፡፡Christ’s Object Lessons, p. 404. በሥራው ግንባር ቀደም ሆነው ለከፈሉት መሥዋዕትነት አክሊል የሚደፉ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ይቀበላሉ፡፡- Testimonies, vol. 6, p. 348. ChSAmh 370.1

    እግዚአብሔር ያዘጋጀው ሽልማት እያንዳንዱን ሠራተኛ ሊያነሳሳና ሊያበረታታ ይገባል፡፡ በዚህ ህይወት ለእግዚአብሔር የምንሠራው ሥራ ብዙውን ጊዜ ፍሬ ዐልባ የመምሰል ሁኔታ ይታይበታል፡፡ መልካም ለመሥራት የምናደርጋቸው ጥረቶች ጽኑና በትጋት የተሞሉ ቢሆኑም ነገር ግን ለምናገኛቸው ውጤቶች ምስክር የመሆን አዝማሚያ አይታይብንም፡፡ እያንዳንዱን ጥረት እንደ መና መመልከት ይቀናናል፡፡ ሆኖም ሥራችን በሰማይ የተመዘገበ በመሆኑ የተዘጋጀልንን ሽልማት እናገኛለን፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 305.ChSAmh 370.2

    እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፣ ፍትሐዊ ተግባር፣ ይቅታና ርኅራኄ በሰማይ ተሰምቶ የማይጠገብ ጣዕመ ዜማ ነው፡፡ እጅግ የከበረውን ሽልማት የያዘው አብ በሰማይ ዙፋኑ ሆኖ እያንዳንዱን የእንቅስቃሴውን ተዋናይ በአንክሮ ይመለከታል “እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤ ይሆናሉ’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፡፡” በችግር ወይም በሥቃይ ላለው ወገን የሚደረግ እያንዳንዱ በምኅረት የተሞላ ድርጊት ለየሱስ እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡ ለደኻው ዕርዳታ የሚያደርግ ወይም በሥቃይና በጭቆና ላሉ የሚያዝንና ለወላጅ ዐልባዎቹ vጻናት ልቡ የመሚራራ ራሱን ከየሱስ ጋር በቅርብ ያስተሳስራል፡፡ --Review and Herald, Aug 16, 1881. ChSAmh 370.3

    ደስታ ፊቱን ላዞረባቸው፣ ለዐይነ ሥውሩ፣ ለአካለ ስንኩሉ፣ ለበሽተኛው፣ ባሏን በሞት ለተነጠቀችው፣ ወላጅ ለሌላቸው ልጆች የሚደረገውን እያንዳንዱ _ ምኅረት፣ ችሮታና ደግነት hርስቶስ ለእርሱ እንደተደረገ ይቆጥረዋል፡፡ እነዚህ የልካም ሽልማት ባለቤት የሚያደርጉ ተግባሮች በሰማይ መዝገብ ተጽፈው ተቀምጠዋል፡፡Testimonies, vol. 3, pp. 52, 513. ChSAmh 371.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents