Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሥልጠና የመስጠት ኃላፊነት

    በጢሞቴዎስ፣ በጳውሎስና በበርናባስ እንደ ተስተዋለው እነዚህ ተስፋ ሰጭና በችሎታ የተሞሉ ሰዎች ጌታን ሲቀበሉ በወይን ተhሉ ዙሪያ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ማሳየት በእጅጉ አስፈላጊ ነበር፡፡ ሐዋርያት ትተዋቸው ለአገልግሎት ወደ ሌላ ስፍራ በሚሄዱበት ወቅት የእነዚህ ሰዎች እምነት ከመጨመር ውጪ አልኮሰመነም፡፡ የጌታን እውነት መሰረት ያደረገ ትምህርት ተሰጥቶአቸው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም ራስ ወዳድ ያልሆነ አገልግሎት በመስጠትና ተግተው በቅንነት በመሥራት ለባልንጀሮቻቸው ደኅንነት እንዲተጉ ሥልጠና ወስደዋል፡፡ አዳዲስ ነፍሳትን በጥንቃቄ የማሰልጠኑ ሥራ ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ምድር ወንጌልን በመስበከ ለተቀዳጁት ጉልህ ስኬት ዓይነተኛ መንስኤ ነበር፡፡— The Acts of the Apostles, pp. 186, 187.ChSAmh 84.1

    ቤተ ክርስቲያናት ሲዋቀሩ የተወሰኑ አማኞች ይህን እውነት ይዘው ከውስጣቸው በመውጣት ወደ አዳዲስ ስፍራዎች ሄደው ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጹና ነፍሳትን እየማረኩ መገስገስ እንደሚኖርባቸው ግልጽ ሆኖ ሊቀርብላቸው ይገባል፡፡ ስለዚህ አባላት በሥራው የሚሳተፉ፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መhሊት ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ የሚያውሉና አእምሮአቸውን ለመምህሩ አገልግሎት ያሰለጠኑ ሊሆኑ ይገባል፡፡-Testimonies, vol. 3, p. 205.ChSAmh 84.2

    እምነታችንን በትhክል ሊወክል በሚችል መልኩ ራሱን በታማኝነትና በቅድስና ለሥራው አሳልፎ የሰጠ--ደረጃውን የጠበቀ የአእምሮ እጦት የወንጌል ተልዕኮ ያለማሰለስ አሳፋሪ ሁኔታ እንዲገጥው መንስኤ ሆኖአል፡፡ ወንጌላዊ መሆን የሚችሉ አያሌ ወገኖች ቢኖሩም ነገር ግን በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በኮሌጆቻችን በቅርብ የሚያውቋቸው ከእነርሱ ጋር የመሥራት ሸhም አይሰማቸውም፡፡ እግዚአብሔር በሙሉ ኃይላቸው የሚሰጡትን አገልግሎት እንደሚሻ አይገልጹላቸውም፣ አብረዋቸው ወይም በተናጥል ስለ እነርሱ አይጸልዩምስለዚህ ወደ አገልግሎት አይገቡም፡፡Counsels to Teachers, pp. 500, 501. ChSAmh 85.1

    በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ላፊነት ላይ ያሉ ሁሉ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ለእግዚአብሔር ሥራ የበኩሉን እንዲያበረክት ዕድል እንዲያገኝ የሚያስችል እቅድ ሊያወጡና መላ ሊመቱ ይገባል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሠራር ባለፉት ጊዜያቶች ሥራ ላይ ሲውል አልታየም፡፡ አባላት መልከሊቶቻቸውን ተጠቅመው ንቁ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ሲገባ ዕቅዶች ግልጽ ሆነው አልተቀመጡም እንዲሁም ሁሉ አቀፍ ትግበራ አልተካሄደም፡፡ ይህ ተግባራዊ መሆን ባለመቻሉ _ ለብርቱ _ እጦት መዳረጋችንን የሚያስተውሉ ጥቂት ናቸው፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 116.ChSAmh 85.2

    በእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን አባላት ጊዜአቸውን ነፍሳትን ለክርስቶስ በመመለስ ሥራ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል ሥልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት ብርሃን አስተላላፊዎች ካልሆኑ በቀር “እናንት የዓለም ብርሃን ናችሁ” ተብሎ እንዴት ሊነገር ይችላል? የክርስቶስ መንጋ ሸክም ያለባቸው ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ብዙዎችን ለሥራው ያድሙ:: Testimonies, vol. 6, p. 436.ChSAmh 85.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents