Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእረኛው ዓይነት ጥንቃቄ

    ከበጎቹ መሃል አንዷ መጥፋቷን ያስተዋለ እረኛ በበረት ውስጥ በሰላም ወደሚገኙት መንጎች በግዴለሽነት እየተመለከተ “በረቱ በዘጠና ዘጠኝ በጎች ተሞልቶ እየተመለከትኩ አንድ የባዘነ በግ ፍለጋ መንከራተትና ራሴን ማድከም የለብኝም፡፡ ራሱ ከጠፋበት ሲመጣ የበረቱን በር ከፍቼ አስገባዋለሁ፡፡” አይልም፡፡ በጉ እንደጠፋ እረኛው ወዲያውኑ በሐዘንና በጭንቀት አይዋጥም፡፡ በዚያ ፋንታ መንጋውን ደጋግሞ ይቆጥራል፡፡ ከመካከላቸው አንዱ መጥፋቱን ሲያረጋግጥ ለደቂቃ እንኳ ሳያንቀላፋ ዘጠና ዘጠኙት በበረት ውስጥ ትቶ የባዘነውን በግ ፍለጋ ይወጣል፡፡ የጊዜው በውሽንፍርና በጨለማ መውደቅና የመንገዱ አደገኝነት መጨመር የእረኛውን ሥጋት ይበልጥ የሚያሳድግ፣ የፍለጋ ቁርጠኝነትና ጽናቱ እንዲጨምር የሚያደርግ እንደመሆኑያን የጠፋ በግ ለማግኘት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል፡፡ ChSAmh 340.2

    ራቅ ካለ አቅጣጫ እንደ ህልም የሚሰማው የተዳከመና የሚያለከልh ድምፅ ጭንቀቱንና ውጥረቱን ይቀንስለታል፡፡ የባዘነውን ድምፅ ተከትሎ ዥው ባለው አስፈሪ ገደል አፋፍ እየተንጠላጠለ--የገዛ ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ድምፁ እየተዳከመ፣ ሊሞት የተቃረበውን በግ ይፈልገዋል፡፡ በስተመጨረሻ--የጠፋውን በግ ማግኘቱ ያን ሁሉ ድካምና ልፋት የከበረ ያደርገዋል፡፡ በጉ ከመንጋው ጠፍቶ መጠነ ሰፊ ጉስቁልና ስላደረሰበት አይቆጣውም፣ አይገስጸውም፡፡ በአለንጋ እየገረፈ ወደ ቤት ሊነዳውም አይሞክርም፡፡ በዚያ ፋንታ በፍርሃት የራደውን ፍጥረት በደስታ ጫንቃው ላይ ይሸከመዋል፡፡ ቁስለት ወይም ጉዳት ቢገጥመው የልብ ትርታውና ሙቀቱ vይወት ይሰጠው ዘንድ በእቅፉ ውስጥ አጥብቆ ይይዘዋል፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 187, 188.ChSAmh 341.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents