Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአገልጋዩ ኃላፊነት

    የወንጌል አገልጋዮች ለቤተ ክርስቲያን አባላት ሊሰጡ የሚችሉት ምርጥ ዕርዳታ መስበክ ሳይሆን አገልግሎት የሚሰጡበትን ዕቅድ ማውጣት ነው፡፡ እያንዳንዱ አባል ለሌሎች ሊሠራ የሚችላቸው ሥራዎች ይሰጡት፡፡ አባላት የክርስቶስ ጸጋ ተቀባዮች እንደመሆናቸው ለእርሱ የመሥራት የውዴታ ግዴታ እንዳለባቸው መመልከት እንዲችሉ እገዛ ይደረግላቸው፡፡ አገልግሎት እንዴት መስጠት እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ትምህርት ይሰጣቸው፡፡ በተለይ አዳዲስ አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር እጅና ጓንት ሆነው አገልግሎት የሚሰጡበት ትምህርት ይሰጣቸው፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 82.ChSAmh 96.4

    አገልጋዮች አባላት በግል ከክርስቶስ ውጪ ወዳሉ ለመድረስ የሚያነሳሳቸውን እውነት ያዘለ መልእክት ይስበኩ፡፡ ግላዊ ጥረቶች በተቻለ መጠን እንዲበረታቱ ይደረጉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 124. ChSAmh 97.1

    አባላት በመንፈሳዊው ነገር ለማደግ ጌታ የሰጣቸውን—ነፍሳትን ወደ እውነት የመምራት ሸhም መሸከም እንዳለባቸው አገልጋዮች ትምህርት ይስጧቸው፡፡ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ የማይገኙ ሊጎበኙ፣ ከእነርሱ ጋር በአንድ ላይ ሊጸለይና አገልግሎት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ አገልጋዩ እንደ አገልጋይነቱ ሕዝቡን በእርሱ ላይ ብቻ እንዲተማመን አድርጎ ሊቀርጽ አይገባም፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶቻቸውን ተጠቅመው በዙሪያቸው ላሉ እውነትን እንዲያስተላልፉ ሊያተምራቸው ይገባል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት አገልግሎታቸውን በዚህ መልኩ ሲተገብሩ የሰማይ መላእክትን አብሮነትና እገዛ ያገኛሉ፣ እምነታቸውና ተሞክሮአቸው ይጎለብታል እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ይመሰርታሉ፡፡Gospel Workers, p. 200. ChSAmh 97.2

    አገልጋዩአማኝ ያልሆኑት እንዲያምኑ አጥብቆ መሥራት ሳይሆን ነገር ግን ተቀባይነት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ሥልጠና ለአባላት ሊለግስ ይገባል፡፡ አባላት ለሌሎች መሥራት የሚያስችላቸውን ጥልቅ ተሞክሮ ራሳቸው እንዲሽቱ አድርጎ በግል ማነሳሳትና ጥረት ማድረግ የእርሱ ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት አገልጋዩን በጸሎታቸውና በአገልግሎታቸው ሲደግፉ ጥረቱ በታላቅ ስኬት የታጀበ ይሆናል፡፡Gospel Workers, p. 196.ChSAmh 97.3

    አንዳንዴ የመጋቢው ሥራ ከቡድን የሥራ መሪ ወይም ከመርከብ ካፕቴን ጋር ተመሳሳይ _ ገጽታ ይኖረዋል፡፡ መሪዎቹ በበታቾች ላይ የመደቧቸው ኃላፊዎች የሥራው እንቅስቃሴ በትክክልና በፍጥነት መከናወኑን ከመቆጣጠር ውጪ አቸኳይ ሁናቴ ካልተፈጠረ በቀር ወደ ዝርዝር የሥራ ተግባራት የሚገቡበት አጋጣሚ አይኖርም፡፡ በአንድ ወቅት የአንድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ቀላል ጥገና ያስፈለገውን ማሽን ለማስተካከል ብቻውን ደፋ ቀና ሲልሥራው ላይ የተመደቡ ግማሽ ደርዘን ሠራተኞች ግን ያለ ምንም እንቅስቃሴ ቆመው እየተመለከቱ እያለ የድርጅቱ ባለቤት ይደርሳል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ኢፍትሐዊ ውሳኔ እንዳያሳልፍ በመጠንቀቅ በወቅቱ የተከሰተውን ተጨባጭ ሁናቴ በጥንቃቄ ከመረመረ በኋላ ሥራ አስኪያጁን ወደ ቢሮው አስተጠርቶ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ከሥራ ያሰናብተዋል፡፡ በሁናቴው ግራ የተጋባው ሥራ አስኪያጅ ማብራሪያ እንዲሰጠው ይጠይቃል፡፡ “እኔ የቀጠርኩv ስድስት ሠራተኞችን በሥራ ላይ እንድታሰማራ ነበር፡፡ ነገር ግን ስድስቱ ሠራተኞች ያለ ሥራ ቆመው አንተ ብቻህን የአንድ ሰው ሥራ እየሠራህ ደረስኩ፡፡ አንተ እየሠራህ የነበረውንሥራ ከፈቱት ከስድስቱ አንዱ ሊሠራው ይችል ነበር፡፡ስድስቱ ሠራተኞች እንዴት ያለ ሥራ መቆም እንዳለባቸው ታስተምራቸው ለነበርከው--የሰባት ሰው ደሞዝ የመክፈል አቅም የለኝም፡፡” ይህ ሁናቴ ምናልባትም ለሁሉም ሳይሆን ለአንዳንድ ክስተቶች ገጣሚ ሊሆን ይችላል፡፡ አያሌ መጋቢዎች የቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ በንቃት መሳተፍ እንደሚኖርባቸው አያውቁም ወይም ያንን ለመተግበር አይሞክሩም፡፡ ነገር ግን መጋቢዎች መንጋዎቻቸው በንቃት አገልግሎት ውስጥ እንዲሳተፉ አብልጠው ትኩረት የሚሰጡ hሆነ የላቁ መልካም ተግባራትን ማከናወን፣ ለጥናትና ለጉብኝት የበለጡ ጊዜያቶችን ማዋልና ብዙዎቹን የፍትጊያ መንስኤዎች ማስወገድ በቻሉ ነበር፡፡-Gospel Workers, pp. 197, 198. 71ChSAmh 97.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents