Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 19—የአገር ውስጥና የውጪ የወንጌል ተልዕኮ

    ከውጭ ተልዕኮ ጋር እኩል ዋጋ የሚሰጠው ሥራ

    በአሜሪካ ያላችሁ ወንድምና እህቶቼ ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ እስካሁን ወዳልተደረሰባቸው ስፍራዎች ግቡ፡፡ ወቅታዊው እውነት ወደ ሌሎች አገሮች እንዲሰራጭ የእርዳታ እጃችሁን ከዘረጋችሁ በኋላ ኃላፊነታችሁን ተወጥታችሁ እንደጨረሳችሁ አድርጋችሁ አታስቡ፡፡ በውጪ አገራት የሚሠሩ ሥራዎች ቢኖሩም የዛኑ ያህል በአገር ውስጥ የሚሠራ አስፈላጊ ሥራ አለ፡፡ በአሜሪካ ከተሞች የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሕዝቦች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ የሰጠው ብርሐን ለእነዚvም ሰዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡Testimonies, vol. 8, p. 36. ChSAmh 275.1

    ራቅ ባሉ ስፍራዎች የሚኖሩ የተለያዩ ሕዝቦችን ለማስጠንቀቅ የሚያስችሉ ዕቅዶች እየተተገበሩ እያለ በዚvች አገር ዳርቻዎች ለሚገኙ የባዕድ አገር ሰዎች አብልጠን ልንሠራ ይገባል፡፡ በቻይና ያሉ ነፍሳት በደጃፋችን ጥላ ስር ካሉት በበለጠ የhበሩ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሩቅ ስፍራዎች ወደሚገኙ ነፍሳት በማምራት አምላካዊው በጎነት የሚከፍታቸውን በሮች እየተጠቀሙ ታማኝ አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ወደ ከተሞች መንደሮችና በአቅራቢያችን ወደ ሚገኙ የተለያዩ የውጪ አገር ዜጎች በማምራት የየግል ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡Review and Herald, July 25, 1918. ChSAmh 275.2

    በኒው ዮርh ከተማ ቺካጎና በሌሎች ታላላቅ የሕዝብ ማዕከላት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጪ አገር ዜጎች ቢኖሩም ለእነዚህ ሁሉ ማስጠንቀቂያው አልተሰጣቸውም፡፡ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መሃል ታላቅ ቅንአት ቢኖርም ነገር ግን ወደ ውጪ አገራት በመሄድ አገልግሎት የመስጠት ከፍ ያለ ተነሳሽነት አለ ብዬ መናገር አልችልም፡፡ ሆኖም በአቅራቢያችን ወዳሉ ከተሞች ሄዶ የመሥራት ሚዛናዊ ቅንአት የሚኖረን ከሆነ እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል፡፡ ሕዝቦቹ በማስተዋል ሊመላለሱ ይገባል፡፡ በከተሞች ለሚሠራው ለዚህ ሥራ ብርቱ አጽንኦት ሰጥተው ሊሳተፉ ይገባል፡፡ ለሥራው ራሳቸውን ቀድሰው የሰጡና ለአገልግሎቱ ገጣሚ መክሊት ያላቸው ሰዎች ወደ እነዚህ ከተሞች ተልከው ይሰማሩ፡፡ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ሠራተኞች ኃይላቸውን አስተባብረው ማስጠንቀቂያውን ለሕዝቡ ለማድረስ በአንድነት ይነሱ፡፡Review and Herald, July 25, 1918.ChSAmh 276.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents