Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እውነተኛ ማንነት

    ለዓለም እንድናበረክት የተጠራንበትን የተቀደሰና የተከበረ መልእክት የሚያቀርቡ ወገኖች ህይወት ከልብ የመነጨ እውነተኝነት የሚታይበት እንጂ ከአንገት በላይ ሊሆን አይገባም፡፡ በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት የጽድቅ ባለቤቶች ስለሆኑትና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስለ ሚጠብቁ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን የሚያውቀው ዓለም በአንክሮ እየተመለታቸው ይገኛል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሕዝቦች በእምነታቸው መሰረት ሳይመላለሱ ሲቀሩ መጠቋቆሚያና መሳለቂያ ለማድረግ ጣቱን ይቀስርባቸዋል፡፡- Testimonies, vol. 9, p. 23. ChSAmh 313.3

    ሰዎች እጅግ ግሩም ስጦታ፣ መልካም ችሎታና ድንቅ ብቃት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ እንከን ወይም በምስጢር የተያዘኃጢአት ጸባይን ይሸረሽራል—የመርከብን ጣውላ መዝምዞ ቀፎ እንደሚያስቀር ምስጥ ጥፋትና ውድመት ያስከትላል! Testimonies, vol. 4, p. 90.ChSAmh 313.4

    ጳውሎስ በሄደበት ሁሉ የሰዎችን ልብ የሚነካው ሰማያዊ መሳጭ ትዕይንት አብሮት ይጓዝ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር ቅርበት የፈጠሩ ሁሉ ከክርስቶስ ጋር የነበረው ሕብረት ተጽእኖ ተሰምቶአቸዋል፡፡ የገዛ ሕይወቱ ለእውነት እርአያ በመሆን እውነትን በተጨባጭ ገልጦ ማሳየቱ ለስብከቱ ብርቱ ኃይል ለመሆን ችሎ ነበር፡፡ በዚህም እውነት ምን ይህል ብርቱ ኃይል እንዳለው _ መመልከት እንችላለን፡፡ በጥልቅ ያልተመረመረውና በቅጡ ያልተስተዋለው የቅድስና ህይወት ተጽእኖ ለክርስቲያኖች በጎ ምስክር መሆን የሚችል፣ ልብን የማሳመን ኃይል ያለው ብርቱ ስብከት ነው፡፡ ክርhር የሌላኛውን ወገን አፍ አሲዞ ምላሽ የሚያሳጣ እንኳ ቢሆን፤ ተቃውሞን ከማነሳሳት ውጪ የሚፈይደው አይኖርም፡፡ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመመላለስ ምሳሌ መሆን የሚችል ስብዕና ሙሉ ለሙሉ ለመቋም የማይቻል ብርቱ ኃይል አለው፡፡ --Gospel Workers, p. 59. ChSAmh 314.1

    እውተኛ ጸባይ ከውጭ ተሠርቶ በላይ የሚደረብ ሳይሆን ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈነጥቅ ነው፡፡ ሌሎችን ወደ ጽድቅ ጎዳና የምንመራ ከሆንን የጽድቅ መሰረታዊ ደንቦች በልባችን ውስጥ መቀረጽ አለባቸው:: በእምነታችን የኃይማኖትን ጽንሰ ሃሳብ እንገልጽ ይሆናል፡፡ሆኖም የእውነትን ቃል እንደ አርማ አጉልቶ የሚያሳየው ተግባራዊው መንፈሳዊነታችን ነው፡፡ ብርሃን ወደ ዓለም ሊተላለፍ የሚችለው በማይናወጥ ህይወት፣ በተቀደሰ አነጋገር፣ በማያወላውል ሐቀኝነት፣ በንቁ በጎ አድራጊ መንፈስና በፈሪሃ እግዚአብሔር አማካይነት ነው፡፡The De sire of Ages. p. 307.ChSAmh 314.2

    ነፍሳትን ማደፋፈርና የምክር አገልግሎት መስጠት ብዙውን ጊዜ የማይነጣጠሉ ርካሽ ፍሬዎች ሲሆኑ ነገር ግን በችግር ላለው መድረስ፣ አባት የሌላቸውንና መበለቲቱን መንከባከብ በተፈጥሮ ከመልካም ዛፍ በቅለው በበጎ ሥራ የሚገለጡ ልባዊ ፍሬዎች ናቸው: Testimonies, vol. 2, p. 24.ChSAmh 314.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents