Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከጥንቷ እስራኤል ውድቀት የምንማረው ትምህርት

    እስራኤላውያን ከነዓን ሲገቡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መላውን ግዛት የራሳቸው በማድረግ አምላካዊውን ዓላማ አላሳኩም፡፡ ይልቁንም የከነዓንን ግዛት ከፊሉን ብቻ ከያዙ በኋላ ተረጋግተው በመቀመጥ የድላቸውን ፍሬ ማጣጣም ጀመሩ፡፡ ወደ ፊት እየገፉና አዳዲስ መሬቶችን እያስለቀቁ የግዛታቸው አካል ማድረግ ሲገባቸው አለማመናቸውና ምቾት ወዳድነታቸው በዚያው ባሉበት ችምችም ብለው እንዲሰፍሩ መንስኤ ሆናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ ከእግዚአብሔር መነጠል ጀመሩ፡፡ አምላካዊውን ዓላማ ከመተግበር መሰናከላቸው የገባላቸውን በረከት መፈጸም እንዳይችል አደረገው፡፡ የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ተመሳሳይ ተግባር እየፈጸመች ይሆን? መላው ዓለም የወንጌልን መልእክት አጥብቆ እየሻተ ክርስቲያን ነን የሚሉ ግን ወንጌልን የራሳቸው ብቻ ልዩ መብትና ጥቅም አድርገው በጉባዔ ሲደሰቱበት መመልከት የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የደኅንነትን መልእክት ይዘው ወደ አዳዲስ ግዛቶች የመሄድና ከቆሙበት ባሻገር ያለውን ምድር የመቆጣጠር አስፈላጊነት አይሰማቸውም፡፡ ክርስቶስ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ስበኩ” በማለት የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ይቃወማሉ፡፡ በbይሁዳውያን ጉባዔ ከሆነው ያነሰ ጥፋተኞች ሆነው መታየት ይችሉ ይሆን?— Testimonies, vol. 8, p. 119. ChSAmh 257.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents