Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የዘላለማዊው ሕይወት ሽልማት

    እርዳታ ባስፈለገበት ሁሉ ጽኑና ልባዊ ጥረት የሚያደርግ ክርስቲያን ለእግዚአብሔርና ለሰብዓዊ ባልንጀራው ያለውን ፍቅር ያሳያል፡፡ ምናልባት አገልጋዩ ታማኝ አገልግሎቱን እየሰጠ ቢያልፍ ክርስቶስ ዕንቁዎቹን ወደ ራሱ ሊሰበስብ ሲገለጥ ዳግም ያኘዋል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 56.ChSAmh 375.4

    በአምላካዊ ደማነት የተሞላው አቀባበል፦ በዚህ ህይወት ከhርስቶስ ጋር ተባብረው የሠሩ ስለ እርሱ የተቀበሉት ሥቃይ እንደ ልዩ መብትና ጥቅም ተቆጥሮላቸው በዘላለም ደጃፍ ላይ ቆመው በደግነት የተሞላ አቀባበል ሲደረግላቸው... የዳኑትእነርሱን ወደ ከበረው አዳኝ ላመላከቷቸው ሰላምታ የቀርቡላቸዋል፡፡ ስለ እነርሱ መሥዋዕት ሆኖ ከእግዚአብሔር ህይወት ጋር የሚለካ ህይወት ላጎናጸፋቸው ለአርሱ በአንድ ላይ ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ አሁን ውያው አክትሞአል፡፡ ውጣ ውረዱና መከራው ዳመኛ ላያረሽ ተቋጭቶአል፡ የዳኑት በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ እንደተሰባሰቡ መላው ሰማይ የድል ዜማ ያዜማል፡፡ ሁሉም የአስደሳቹ ዝማሬ አካል በመሆን የታረደው በግ ከብርና ሞገስ፣ ምስጋናም ይገባዋል” ያሉ የዋጃቸውን ጌታ ያወድሳሉ፡The Ministry of Healing pp. 506, 507.ChSAmh 376.1

    በሕይወት መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ጸባያቸው በትህትና፣ ራስን በመካድና በቸርነት የተሞላ መሆኑን የሚያሳይ ከሆነ፤ የተባረከውን ማረጋ7ጫ ከክርስቶስ ይቀበላሉ “ደግ _ ድርገሃል” “እናንት አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፡” Testimonies, vol. 3, p. 525.ChSAmh 376.2

    ሰማያዊው ቅጥር- ዛሬ ቤተ ከርስቲያን በውጊያ ላይ ናት፡፡ ምንም እንኳ ዛሬ ራሱን ሙሉ ለሙሉ ለባዕድ አምልኮ ካስገዛው ጨለማ ዓለም ጋር ብንጋጠምም፤ ይህ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ውጊያ በድል የሚጠናቀቅበት ቀን እየተቃረበ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ እንደሆነ በምድርም የሚሆንበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ የዳኑት ሕዝቦች ከሰማይ ሕግ ውጪ የሚያውቁት ሌላ ሕግ የለም፡፡ የhርስቶስን ጽድቅ ሸማ የለበሱትና የምስጋናና የውዳሴ ካባ የደረቡት እነዚv ሕዝቦች አንድ ደስተኛ የተባበረ ቤተሰብ ይሆናሉ፡፡ መላው ተፈጥሮ በሚያስደምም ግርማና ተወዳጅነት ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ ያቀርባል፡፡ የጨረቃ ብርሃን የፀሐይን ያvል ሲያበራ ፀሐይ ደግሞ አሁን ካለው ሰባት እጥፍ ታበራለች፡፡ ዓመታት በደስታ ያልፋሉ፡፡ እግዚአብሔርና hርስቶስ “ከእንግዲህ ወዲህኃጢአት ወይም ሞት አይኖርም” ብለው ሲያውጁ የንጋት ከዋክብት በአንድ ላይ ይዘምራሉ፣ የእግዚአብሔር ልጆችም በደስታ እልል ይላሉ፡፡ The Ministry of Healing, p. 504. ChSAmh 376.3

    ሰማያዊ ደስታ:-የክርስቶስ ሠራተኞች ወደ እርሱ ደስታ መግባታቸው ሽልማታቸው ነው፡፡ ይህ ክርስቶስ ራሱ ከፍ ባለ ምኞት የሚከታተለው ደስታ “አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ... እፈልጋለሁ” ብሎ አባቱን በጠየቀው መሰረት ገቢራዊ መሆን የቻለ ነው::Testimonies, vol. 6, p. 309.ChSAmh 377.1

    ምድራዊው ሕይወታችን በኃጢአት የተገደበ ቢሆንም፤ አገልግሎት በመስጠት ከፍ ያለ ደስታና ትምህርት ማግኘታችን እሙን ነው፡፡ ሰብዓዊውን ኃጢአተኝነት ተከትሎ ሊስተዋል ከሚችል ማንኛውም ውሱንነት ነፃ ሆኖ በሚጠብቀን በወደፊቱ ዓለም የምንሰጠው ከፍ ያለ አገልግሎት እንዲሁም የምንማራቸው አዳዲስ ነገሮች የደስታችን ምንጭ ይሆናሉ፡፡ “የዚህ ምስጢር ክብርባለጠግነት... እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው፡፡”- Education, p. 309.ChSAmh 377.2

    የክርስቶስን ሥቃይ እንደተካፈሉ ሁሉ ወደፊት የሚገለጠው የአምላካዊ hብር ተካፋዮችም ይሆናሉ፡፡ ከእርሱ ጋር በአንድነት ያገለገሉና እርሱ የጠጣውን የሐዘን ጽዋ የተጎነጩ በክብር የተሞላው አምላካዊ ደስታ ተጋሪዎችና ወራሾች ይሆናሉ፡Thoughts From the Mount of Blessing p. 12.ChSAmh 377.3

    መልካም ዘር መግራት:- እያንዳንዱ የመንፈስ ቅዱስ ግፊት ሰዎችን ወደ መልካም እንደሚመራ ሁሉመንፈስ ቅዱስ እንዲሠራበት ራሱን ለዚህ ፈቃድ የሰጠ ማንኛውም ሰው ሕይወቱን ለደኅንነት ያበቃውን ተጽእኖ እንዲያይ ይደረጋል፡፡ Testimonies, vol, 6, p. 310.ChSAmh 377.4

    በእግዚአብሔር ፊት የቆሙት የተዋጁ ልጆቹታማኝና በትዕግሥት የተሞላ ልመናና ጽኑ ጥረት አድርገው ወደ ጌታ እቅፍ እንዲመጡ መንስዔየሆኗቸውን የከበሩ ነፍሳት ስም ይጠራሉ፡፡ በዚህ ምድር ከጌታ ጋር አብረው ሠራተኞች የነበሩ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ይቀበላሉ፡፡-Testimonies, vol. 8, pp. 196, 197. ChSAmh 378.1

    የዳኑት ነፍሳት ስለ እነርሱ ሸክም የነበራቸውን ወገኖች ሲገናኙና ሰላምታ ሲለዋወጡ መመልከት እንዴት ደስ ያሰኝ! ደግሞም ራሳቸውን ለማስደሰት ሳይሆን ነገር ግን ለሌሎች በረከት ለመሆን ስለ ምስኪኖች የኖሩ ነፍሳት ልብ ምንኛ እርካታ ያገኝ በዚያን ወቅት ይህን ተስፋ ያስተውላሉ “ትባረካለvም፡፡ እነዚህ ብድር ሊመልሱልv ስለማይችሉ በጻድቃን ተንሳኤ ብድራትህ ይመለስልሃል፡፡”— Gospel Workers, p. 519. ChSAmh 378.2

    በምድራዊው ህይወት ወደ ቤታችን ጋብዘን የረዳናቸውን፣ ከፈተና እንዲጠበቁ የታደግናቸውን ወጣቶች በሰማይ እናያለን፡፡ ገጽታቸው የእግዚአብሔርን ክብር በሚያንጸባርቅ ብርሃን ተሞልቶ እንመለከታለን፡፡ Testimonies, vol. 6, p. 348. ChSAmh 378.3

    በታላቁ የደኅንነት እቅድ የክርስቶስና የመላእክት አገልግሎት ባልደረባ ሆኖ መሥራት እንዴት ድንቅ ነው! ከቶ የትኛው ሥራ ይሆን ከዚህ ጋር የሚወዳደር!? ከእያንዳንዱ የዳነ ነፍስ ለእግዚአብሔር ክብር የሚገኝ ትርፍ ያለ ሲሆን፤ ይህ ክብር እንዲድን አገልግሎት በሰጠውና በዳነው ገጽታ ላይ ይንጸባረቃል፡፡--Testimonies, vol. 2, p. 232. ChSAmh 378.4

    በበጉ ደም የተዋጁት ጻድቃን ትኩረታቸውን ወደ ከበረው አዳኝ እንዲያደርጉ ከረዷቸው ነፍሳት ጋር ይገናኛሉ፡፡ ከነዚህ ነፍሳት ጋር የሚጨዋወቷቸው ሃሳቦች እንዴት የተባረኩ ይሆኑ! “በዓለም ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ ስመላለስ፤ ወደ እኔ ቀርበህ ትኩረቴን ብቸኛ ተስፋ ወደ ሆነው የከበረ አዳኝ እንዳደርግ ረዳኸኝ፡፡ ከዚያም ጌታን ተቀብዬ አመንኩ፡፡ ጢአቴን በመናዘዜ በየሱስ ክርስቶስበሰማያዊው ስፍራ ከቅዱሳን ጋር አብሬ ለመሆን በቃሁ፡” ሌሎች ሲናገሩ “...እኔ ባዕድ አምልኮ ይተገበርበት ከነበረ ምድር የመጣሁ የባዕድ አምልኮ ተከታይ የነበርኩ ሲሆን፤ ጓደኞችv በምቹው ቤትህ ውስጥ ስለ የሱስ መሰከሩልኝ፡፡ እኔም እንደ እውነተኛ አዳኜ አድርጌ ተቀበልኩት፡፡ ጣኦቴቼን ሰባብሬ ጥዬ እነሆ አሁን ፊት ለፊት የማየውን እግዚአብሔር ማምለክ ጀመርኩ፡፡ የደኅንነት ባለቤት በመሆኔ ከምወደው አምላh ጋር ለዘላለም እኖራለሁ፡፡ ቀድም ሲል በእምነት ያየሁትን ጌታ እነሆ አሁን ግን በዐይኖቼ እያየሁ— ይቅር ላለኝ፣ ለወደደኝና በገዛ ደሙ ከኃጢአቴ ላጠበኝ ለእርሱ ምስጋናዬን ማቅረብ እችላለሁ፡፡”— Gospel Workers, p. 518.ChSAmh 378.5

    ሌሎች ደግሞ የተራቡትን ላበሉና የታረዙትን ላለበሱ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ፡፡ “ነፍሴ ባለማመን ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴ ውስጥ ተከብባ በነበረችበት ወቅት፤ ተስፋ የሚሰጡና የሚያጽናኑ ቃላቶችን እንድትነግረኝ ጌታ ወደ እኔ ላከv፡፡ የምበላው ምግብ ሰጥተህ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ከፈትክልኝ አንቀላፍቶ የነረውን መንፈሳዊ ህይወት ቀሰቀስከው፡፡ እንደ ወንድምህ አድርገህ ቀረብከኝ፡፡ ሳዝን አዝነv፣ ስከፋ ተከፍተvእኔን ለማዳን የተዘረጋውን የክርስቶስ እጅ እንዲጨብጥ ነፍሴን መለስከው፡፡ እኔን የሚወደኝና የሚጠነቀቅልኝ አባት በሰማይ እንዳለኝ ነገርከኝ፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሰፈሩትን የከበሩ ተስፋዎች አነበብክልኝ፡፡ እርሱ እንደሚያድነኝ በመንገር በውስጤ መነቃቃት ፈጠርh፡፡ ክርስቶስ ለእኔ የከፈለውን መሥዋዕትነት ሳሰላስል ደንዳናው ልቤ ተለሳለሰ፣ ለእርሱም ተገዛ፡፡ የህይወት እንጀራ ተርቤ ስለነበር የሰማሁት እውነት ለነፍሴ የከበረ ሆነ፡፡ እነሆ አሁን ለዘላለም ድኜ ሕይወቱን ለእኔ የሰጠውን ጌታ ሳመሰግን ልኖር በዚህ አለሁ፡፡”— Gospel Workers, pp. 518, 519. ChSAmh 379.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents