Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከነህምያ ሕይወት የምናገኛቸው ትምህርቶች

    ባለፉት ዓመታት የወንጌል ተልዕኮአችንን የሥራ ዕቅድና ክንውን በጓደኞቻችንና በጎረቤቶቻችን ፊት ስለማቅረብ አስፈላጊነት ስናገር ነህምያን በምሳሌነት ጠቅሼ ነበር፡፡ ወንድሞችና እህቶች ስለዚv የጸሎትና የእምነት ሰው ቅን ፍርድ ተሞክሮ ደግመው እንዲያጠኑ ልገፋፋቸው እመኛለሁ፡፡ ነህምያ ወዳጁ ወደነበረው ንጉሥ አርጤክስስ ገብቶ ለእግዚአብሔር ሥራ ግስጋሴ እርዳታ እንዲያደርግ በድፍረት ጠይቆ ነበር፡፡MS,, “Consecrated Efforts to Reach Unbelievers,” June 5, 1914. Solicited Means From Those Able to Bestow.-ChSAmh 236.2

    የጸሎት ሰዎች የተግባር ሰዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡ ለመሥራት ዝግጁና ፈቃደኞች የሆኑ አገልግሎት የሚሰጡባቸውን መንገዶችም ሆነ ለሥራው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ያገኛሉ፡፡ በአጠራጣሪ ሁናቴዎች ላይ ያልተማመነው ነህምያ አጥቶት የነበረውን የገንዘብ መጠን መለገስ ከቻሉ ወገኖች ማግኘት ችሎ ነበር፡፡-- Southern Watchman, March 15, 1904. ChSAmh 237.1

    በኃይል ታጅቦ ለመጣው ብርቱ ሥራ የተገለጸ ወኔ: በግዞት ስር ይማቅቅ የነበረው የተዋረደ ዝርያ አካል የነበረው ነህምያና የዓለም ልዕለ ኃያል አገ ንጉሥ የነበረው አርጤክስስ ፊት ለፊት ተገናኙ፡፡ ነገር ግን ከደረጃቸው አለመመጣጠን ይልቅ የትየለሌው በመሃቸው የነበረው የሞራል ርቀት ነበር፡፡ ነህምያ በነገሥታት ንጉሥ የቀረበለትን ግብዣ ለመቀበል ታዛዥ ነበር፡፡ “አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ ከእኔም ጋር ሰላም ይፍጠሩ፤ አዎን ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠሩ፡፡” ለብዙ ሳምንታት ወደ አምላካዊው መገኛ በጸጥታ ይልክ የነበረው ልመና ተመሳሳይ ነበር፡፡ አሁን ስለ እርሱ የሚሠራለት ሁሉን የሚያውቅና ሁሉን የሚችል ወዳጅ እንደነበረው ሲያስብ ብርቱ ወኔ ተሰማው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሡ በመግባት ከአገረ ገዥነት የንጉሣዊ ሥራው ፈቃድ ተሰጥቶት ወደ የሩሳሌም በማምራት የፈራረሰውን ቅጥር ዳግመኛ ጠንካራና አስተማማኝ ከተማ አድርጎ ለመገንባት እንዲፈቅድለት ለመጠየቅ ተመኘ፡፡ የዚህ ጥያቄ ውጤት ለአይሁድ ከተማና ሕዝብ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነበር፡፡ “መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ነበረችና ንጉሡም ፈቀደልኝ” -Southern Watchman, March 8, 1904. ChSAmh 237.2

    አስተማማኝ ሆኖ በሕግ የጸደቀ፡ ነህምያ ለንጉሡ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ዕቅዱን ለመተግበር የሚያስችለውን እርዳታ ለመጠየቅ ተበረታታ፡፡ ለተልዕኮው ክብርና ክብደት ለመስጠት እንዲሁም በጉዞው ጥበቃና ከለላ ለማግኘት ሲል ወታደራዊ አጀብ እንዲደረግለት አመቻቸ፡፡ ወደ ይሁዳ በሚያደርገው ጉዞ ከኤፍራጥስ ባሻገር አቋርጦ ለሚያልፍባቸው ግዛቶች ገዢዎች የተጻፈ ንጉሣዊ የይለፍ ደብዳቤ ያዘ፡፡ እንዲሁም ለየሩሳሌም ቅጥርና እርሱ ሊሠራ ላሰበው ቤት የሚውል የፈለገው ዓይነት እንጨት እንዲሰጠው የሚያዝበሊባኖስ ተራራማ ስፍራዎች ለሚገኘው ለንጉሡ ደን ጠባቂ የተጻፈ ደብዳቤ ያዘ፡፡ ነህምያ በአምላካዊው ሥራ መሳተፍ አንዴ ከጀመረ በኋላ ግስጋሴው እንዲገታ ሰበብ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ከወዲሁ መልክ በማስያዙ ረገድ ጠንቃቃ ሰው ነበር፡፡Southern Watchman, March 15, 1904.ChSAmh 238.1

    ነህምያ በሚያልፍባቸው ግዛቶች ሁሉ ለየአውራጃ ገዢዎች የተጻፉ ንጉሣዊ ደብዳቤዎችን መያዙ በአክብሮት የተሞላ አቀባበልና ፈጣን እርዳታ ለማግኘት አስችሎት _ ነበር፡፡ በፐርሽያ ንጉሥ ወታደሮች ታጅቦ የሚንቀሳቀሰውንና በአውራጃ ገዢዎች ይፋ አጽንኦት የተሰጠውን ባለሥልጣን አንድም ጠላት ለመዳፈር አልዳዳም፡፡ ነህምያ ያደረገው ጉዞ ሰላማዊና ውጤታማ ነበር፡፡Southern Watchman, March 22, 1904.ChSAmh 238.2

    መሰናhሎችን መጋፈጥ ፡ ነህምያ ለአንድ ብርቱ ተግባር ወደ የሩሳሌም መምጣቱን የሚያመላክተው ወታደራዊ አጀብ በእስራኤል ጠላቶች ላይ የምቀኝነትና የጥላቻ ስሜት አጫረ፡፡ በየሩሳሌም አጠገብ ሰፍረው የነበሩ የባዕድ አምልኮ ተከታይ ነገዶች ቀደም ባሉት ጊዜያት በአይሁዶች ላይ የስድብ ናዳና ጉዳት በማድረስ የጠላትነት ስሜታቸውን በማርካት ተጠምደው ነበር፡፡ በዚህ ክፉ ሥራ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘው የነበሩት አንዳንዶቹ የጎሳ መሪዎችሆሮናዊው ሰንበላጥ፣ አሞናዊው ጦቢያ እንዲሁም የጋሸሙ አሽዶድ ነበሩ፡፡ እነዚህ መሪዎች ከዚህ ጊዜ አንስቶ የነህምያን እንቅስቃሴ በዐይነ ቁራኛ በመከታተል በተቻላቸው መጠን እቅዱን ለማሰናከልና ሥራውን ለማስተጓጎል ሙከራ ማድረግ ጀመሩ፡፡--Southern Watchman, March 22, 1904.ChSAmh 238.3

    በግንባታው ሥራ ተሳታፊ በሆኑት ላይ ጥርጣሬና አለማመን በመንዛት በመሃላቸው መከፋፈል ለመፍጠር ከመሞከራቸው በተጨማሪ በሠራተኞች ጥረትና ድካም ላይ በመሳለቅ የተጀመረው ውጥን ከዳር ሳይደርስ አሳፋሪ ውድቀት ሊከተል እንደሚችል አበክረው ይናገሩ ነበር. ብዙም ሳይቆይ የቅጥሩ ግንባታ ሠራተኞች ይበልጥ በማያባራ ተቃውሞ በመዋጣቸው ከእንቅልፍ የለሾቹ ጠላቶቻቸው ሊሰነዘሩ የሚችሉ ድንገተኛ ጥቃቶችን ሊከላከሉና ሊያከሽፉ የሚችሉ የጥበቃ ጓዶች ተመደቡ፡፡ የጠላት ልዑካን ሐሰትነት ያላቸውን መረጃዎች በማናፈስ የግንባታውን ሠራተኞች ወኔ ለመስለብ ጥረት አደረጉ፡፡ ነህምያን ወጥመዳቸው ውስጥ ለመክተት የተለያዩ ሰበብ አሰባቦችንና ሴራዎችን መጎንጎን ጀመሩ፡፡ ይህን የማታለያ ውጥን ለማገዝ አንዳንድ ታማኝነት የጎደላቸው አይሁዶች ዝግጁነታቸውን አሳይተው ነበር... ከግንባታ ሠራተኞች ጋር የተቀላቀሉት ወዳጅ ነን ባዮቹ የጠላት ልዑካን--የዕቅድ ለውጥ እንዲተገበር፣ ግራ መጋባትና መደናገር እንዲከሰት እንዲሁም አለመተማመንና ጥርጣሬ እንዲሰፍን በማድረግ የሠራተኞችን ትኩረት ለመሳብ በተለያየ መንገድ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡--Southern Watchman, April 12, 1904. ChSAmh 239.1

    የዛሬዎቹ መሪዎች እየተጋጠሟቸው ያሉ ተመሳሳይ እንቅፋቶች: የነህምያ ተሞክሮ በዚህ ዘመን በሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦችታሪክ ይደገማል፡፡ በወቅታዊው እውነት ዙሪያ የሚሠሩ ወገኖች የሥራውን ጠላቶች ቁጣ ሳያነሳሱ ተግባራቸውን ማከናወን እንደማይችሉ ይረዳሉ፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ተሳታፊ በሆኑበት ሥራ ላይ እንዲያገለግሉ በእግዚአብሔር የተጠሩና አገልግሎታቸውም በእርሱ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም ከዘለፋም ሆነ ከፌዝ ማምለጥ አይችሉም፡፡ ሕልመኞች፣ የማያስተማምኑ፣ አፈንጋጮች፣ ግብዞች-የሚሉ ብቻ ባጭሩ ለጠላቶቻቸው ዓላማ ገጣሚነት ያላቸው የተለያዩ ውግዘቶች ይደርሱባቸዋል፡፡ እጅግ የተቀደሱት ነገሮች ፈሪሐ እግዚአብሔር በሌላቸው ሰዎች ዘንድ እንደ መሳለቂያ ሆነው ይታያሉ፡፡ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ኃይማኖተቢስነትና ጥላቻ የታከለበት መጠኑ ያልበዛ ፌዝና ቀልድ የተቀደሱትን ነገሮች የሚንቀውን ዘባች ስላቅ ለማነሳሳት በቂ ነው:፡ እነዚህ ከልክ ባለፈ ድፍረት የሚንቀሳቀሱ የተጃጃሉ ዕብሪተኞች አንዱ ሌላውን እየቀረጸ መንፈስ ቅዱስን በሚሳያ ተግባራቸው ይደፋፈራሉ፡፡ ንቀትም ሆነ ስላቅ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት የሚጎዱ፣ ሕመም ያላቸው ነገሮች ቢሆኑም ነገር ግን ለእግዚአብሔር እውነኞች የሆኑ ሁሉ በእነዚህ ውስጥ ማለፋቸው የግድ ይሆናል፡፡ ነፍሳት እንዲሠሩት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሥራ ከመሥራት ፊታቸውን እንዲመልሱ የሚያደርገው የሰይጣን ዘዴና ዕቅድ ነው፡፡-Southern Watchman, April 12, 1904.ChSAmh 240.1

    ተስፋ ቢሱን ጉልበት ማሰባሰብ:-ነህምያ በጸጥታና በምስጢር የቅጥር ዙሪያውን የግንባታ ሥራ አጠናቀቀ፡፡ “ለአይሁድ ወይም ከካህናቱ ወይም ለመኳንንቱ ወይም ለሹማምነቱ ወይም ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ገና ምንም የተናገርኩት ነገር ስላልነበር ወዴት እንደሄድሁ ወይም ምን እንዳደረግሁ ሹምምነቱ አላወቁም፡፡” ነህምያ በአስቸጋሪው የቅኝት ሥራው የወዳጆቹንም ሆነ የጠላቶቹን ትኩረት የመሳብ ምኞት ቢያድርበት ኖሮ ዘገባዎች ሥራውን የሚያከሽፍ ካልሆነም የሚያጓትት ችግር መፈጠራቸው አይቀሬ ነበር፡፡ የምሽቱን ጊዜ ለጸሎትና ለልመና ያዋለው ነህምያ ማለዳ ላይ መንፈሳቸው የተሰበረውን፣ ተስፋ ቢሶቹንና የተከፋፈሉትን ሕዝቦቹን ለማነሳሳት ጽኑ ጥረት ያደርግ እንደነበር ይታመናል፡፡-Southern Watchman, March 22, 1904.ChSAmh 240.2

    የከተማዋን ቅጥር መልሶ ስለ መገንባት አስመልክቶ ነህምያ የአገሬው ሕዝብ እንዲተባበረው የሚጠይቅ ንጉሣዊ ደብዳቤ ይዞ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በባለሥልጣናት ላይ ብቻ መተማመን ምርጫው አልነበረም፡፡ ለዚህ ቆርጦ ለተነሳበት ታላቅ ሥራ የልቦች ህብረት መፍጠርና እጅ ለእጅ መያያዝ አስፈላጊነት ሊያስገኝ የሚችለውን ስኬት በሚገባ የሚያወቀው ነህምያ ከዚህ ይልቅ የሕዝቡን መተማንና ሃሳብ ተካፋይ ስሜት ማግኘት ፈለገ፡፡ChSAmh 241.1

    ነህምያ ሕዝቡን በቀጣዩ ቀን በሰበሰበበት ወቅት ያለ እንቅስቃሴ ተዳፍኖ የተቀመጠውን ጉልበታቸውንና የተበታተነ ማንነታቸውን አንድ አድርጎ በሚያነሳሳ የተቀመረ አነጋገር ሞገታቸው. ነህምያ የቅጥር ግንባታው ሥራ በፐርሽያ ንጉሥና በእስራኤል አምላክ ጥምር ሥልጣን የተደገፈ መሆኑን ሙሉ ለሙሉ ግልጽ አድርጎ በፊታቸው በማስቀመጥ እነዚህ ሕዝቦች ይህን ብልጫ ያለው ጥቅምና ምቹ ሁናቴ ተጠቅመው የከተማውን ቅጥር ለመገንባት ከእርሱ ጋር ለመነቃነቅ ዝግጁ እንደሆኑ ጠየቃቸው፡፡ ይህ ልመናና ተማጽኖ በቀጥታ ወደ ልባቸው በመግባቱ የሰማያዊው በጎነት መገለጥ ፍርሐታቸውን ወደ ሐፍረት ለወጠው፡፡ “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ሲሉ በአዲስ ወኔና በአንድ ድምጽ ጮኹ፡፡-Southern Watchman, March 29,1904. ChSAmh 241.2

    ቅዱሱ የነህምያ ጉልበትና ከፍ ያለው ተስፋው ከሕዝቡ ጋር ግንኙነት መፍጠር ቻለ፡፡ በነህምያ የነበረው መንፈስ በእነርሱም ውስጥ ሲያድር በወቅቱ ወደ ነበረው የመሪያቸው የhንውን ወኔ ደረጃ ከፍ ኤሉ፡፡ እያንዳንዱ ሠራተኛ በተሰለፈበት መስክ ሌላው ነህምያ በመሆን ወንድሙን የሚጠብቅና ደግፎ የሚይዝ ሆነ፡፡-Southern Watchman, March 29, 1904. ChSAmh 242.1

    ለነUምያ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ከመጀመሪያዎቹ አንዱ የሆኑት የእስራኤል ካህናት፡-- የነህምያን ብርቱ የቅንአት መንፈስና ቅን ፍላጎት ከመጀመሪያ ተርታ ከተጋሩ መካከል የእስራኤል ካህናት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ወገኖች ከተቀበሉት ኃላፊነት አኳያ ሥራውን ለማጓተትም ሆነ ወደፊት ለማራመድ ብርቱ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ፡፡ በሥራው ጅማሮ ላይ የነበራቸው የመተባበር ዝግጁነት ለተገኘው ስኬት ያበረከተው አስተዋጾ አነስተኛ አልበረም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ተጽእኖ የማሳደርና የመምራት ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ወገኖች ተቀዳሚ ተግባር ለእግዚአብሔር መሥራት ሊሆን ይገባል፡፡ ለመንቀሳቀስ ፈቃደኛነት የሌላቸውና ቁርጠኝነት የሚጎድላቸው ከሆኑ ሌሎች ከነአካቴው ከእንቅስቃሴ የተገቱ ይሆናሉ፡፡ “ቅን ፍላጎታችሁ ብዙዎችን ለበጎ ሥራ አነሳስቶአል፡፡” ብርሐናቸው ብሩህ ሆኖ ሲበራ ከዚያ ከሚነደው ላይ በሺv የሚቆጠሩ ችቦዎች ይለኮሳሉ፡፡Southern Watchman, April 5, 1904. ChSAmh 242.2

    ነህምያ-የሥራው ኢደራጅ:-በአጠቃላይ ሕዝቡ ደስ ብሎት በአንድ ልብና ነፍስ የአርበኝነት እንቅስቃሴ ተነሳስቶ ነበር፡፡ የችሎታና ተጽእኖ ባለቤት የሆኑ ሰዎች በተለያዩ ደረጃዎች ይገኙ የነበሩትን ዜጎች በቡድን በመከፋፈል እያንዳንዱ የሥራ መሪ የቅጥሩን የተወሰነ ክፍል የመገንባት ኃላፊነት ወሰደ፡፡ ባተሌዎቹ ቡድኖች ኅብር ፈጥረው የፈራረሰውን የየሩሳሌም ቅጥር ያለመታከት ሲገነቡ መመልከት በእግዚአብሔርም ሆነ በመላእክቱ ፊት አስደሳች ትዕይንት ነበር፡፡ “ጎህ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ” ያለማቋረጥ ይደመጡ የነበሩትን የሠራተኞች ድምጽ መስማት ከፍ ያለ ደስታ ያጎናጽፍ ነበር፡፡Southern Watchman, April 5, 1904.ChSAmh 242.3

    የእውነተኛ መሪነት መገለጫ መንገዶ—ሥራው በትhክል ሲጀመር የነህምያ የጋለ ምኞትም ሆነ ጉልበት መቀዛቀዝ አላሳየም ነበር፡፡ የሥራው ጫና ይወድቅብኛል ብሎ በመፍራት እጆቹን አጣጥፎ አልተቀመጠም፡፡ በዚህ ፋንታ ለእያንዳንዱ እንቅፋትም ሆነ አስቸኳይ መፍትሔ ለሚሻ ጉዳይ ንቁ መመሪያዎችን እየሰጠ ሥራውን ያለማቋረጥ ይገመግም ነበር፡፡ አምስት ኪሎ ሜትሮች ገደማ ርዝመት በነበረው የቅጥር ሥራ ላይ የነህምያ ተጽእኖ ያለማቋረጥ ይታይ ነበር፡፡ ነህምያ የፈሩትን እያበረታታ፣ የሚተጉትን እያመሰገነና ወደ ኋላ የቀሩትን ይበልጥ ለሥራው እንዲነሳሱ እያደረገ ለወቅቱ ተገቢነት የነበሯቸውን ቃላት ጥቅም ላይ ያውል ነበር፡፡ ነህምያ አልፎ አልፎ በርቀት እየተሰባሰቡ በጽኑ ንግግር ውስጥ ለመሳተፍ በሚል-በተንኮል የተሞሉ ሴራዎችን የሚጎነጉኑትን፣ ወደ ቅጥሩ ሠራተኞች ቀርበው አስተሳሰባቸውን በመጠምዘዝ ሥራውን ለማስተጓጎል የሚሞክሩትን እያንዳንዱን የጠላቶቻቸውን እንቅስቃሴ እንደ ንስር ዐይን ገና በሩቁ ይከታተል ነበር፡፡ ትንሽዋን እንኳ ምልክት አክብሮ ለመቀበል ዝግጁ የነበረው የእያንዳንዱ ሠራተኛ ዐይን በነህምያ ላይ ተተከሎ ነበር፡፡ የነህምያ ዐይኖቹም ሆኑ ልቡ ቅጥሩ ዳግም እንዲሠራ ሥራውን በአገልጋዩ ልቦና ውስጥ ባኖረው፣ ሥራውን ሙሉ ለሙሉ በሚመራው በታላቁ የበላይ ተቆጣጣሪ ተነቃቅቶ ነበር፡፡ እምነትና የጀግንነት ወኔ በልቡ እየተበረታቱ በሄዱ ቁጥር ነህምያ “የሰማይ አምላh ያከናውንልናል!” በማለት በአድናቆት ይሰነዝራቸው የነበሩ ቃላት በሥራው በተሰማሩ ሠራተኞች ልብ ውስጥ በተደጋጋሚ ያስተጋቡ ነበር:፡--Southern Watchman, April 5, 1904.ChSAmh 243.1

    ነህምያና ባልደረቦቹ በገጠሟቸው አስቸጋሪ ሁናቴዎች መኮማተር አልደረሰባቸውም ወይም ፈታኙን አገልግሎት ላላለመጋፈጥ ምክንያት አልደረደሩም፡፡ የሥራ ልብሶቻቸውን በቀንም ሆነ በምሽት ሳያወልቁ ወይም የጦር መሣሪያዎቻቸውን ላፍታም ከእጃቸው ሳይነጥሉ የእንቅልፍ ሰዓታቸውን ሳይቀር መሥዋዕት አድርገው ነበር፡፡ “እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ ሰዎቼም ሆኑ ከእኔ ጋር ያሉት ጠባቂዎች ልብሳችንን አላወለቅንም፤ ለውሃ እንኳ በምንሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደያዘ ነበር፡፡”-- Southern Watchman, April 26, 1904. ChSAmh 244.1

    የእያንዳንዱን ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ተጽእኖ መከላከል፡ አብላጫዎቹ የእስራኤል መኳንንቶችና ገዢዎች የመጡባቸውን ዝና እንደ ያዙ በተሰየሙባቸው ኃላፊነቶች ላይ የሚቀመጡ ቢሆንም ነገር ግን ጥቂቶቹ የቴቁሐ መኳንንቶች “በአሠሪዎቻቸው ስር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም”፡፡ ታማኞቹ የቅጥር ሠራተኞች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በክብር ሲጠቀሱ ነገር ግን የታካቾቹ ትዝታ የሐፍረት ምልክት ሆኖ ለሁሉም ተከታታይ ትውልዶች በማስጠንቀቂያነት ተሰጥቶአል፡፡ ChSAmh 244.2

    ሥራው የእግዚአብሔር መሆኑን እያወቁ ነገር ግን ወደፊት በማራመድ ፋንታ ራሳቸውን በርቀት የሚያስቀምጡ ፈቃደኝነት የጎደላቸው ጥቂቶች በእያንዳንዱ ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ሰዎች ራስ ወዳዱን ግላዊ ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ሲሆን እጅግ ንቁና ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው፡፡ የእያንዳንዱ ተነሳሽነታችን ዓላማም ሆነ ግብ የሚጻፍበትን ሰማያዊ መዝገብ ማስተወስ ተገቢ ነው፡፡ በዚያ ስርዝ ድልዝ በሌለው መጽሐፍ ሁላችን እንዳኛለን፡፡ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ልንሰጥበት ይገባ የነበረ እያንዳንዱ ችላ የተባለ ዕድል በታማኝነት ይመዘገባል፡፡ እያንዳንዱ እምነታችንን ገልጠን ያሳየንበትና ትሑቱን ፍቅር የሰጠንበት ትዕይንት በዘላለማዊው ማስታወሻ ላይ ይሰፍራል፡፡--Southern Watchman, April 5, 1904.ChSAmh 244.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents