Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መንፈሳዊ ጽልመት

    በዚህ ወቅት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ቤተ hርስቲያኖች ላይ መንፈሳዊ ጽልመት ይሰፍናል፡፡ መለኮታዊ የሆኑትን ነገሮች ከማስተዋል መሰናከል ወይም አላዋቂነት እግዚአብሔርንና እውነትን ከዕይታ ይሰውራል፡፡ የክፉው ሰራዊት ኃይሉን በብርታት እያሰባሰበ ነው፡፡ ሰይጣን መላውን ዓለም በቁጥጥሩ ስር እንደሚያውል አድርጎ ባልደረቦቹን ይሸነግላል፡፡ የቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በከፊል የቆመ ሲሆን ሰይጣንና ሰራዊቱ ግን በስፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ የክርስትና የእምነት ተቋማት በራስ ወዳድነትና ትዕቢት በመጠላለፋቸው ዓለምን እየለወጡ አይደለም፡፡ ሌሎችን ወደ ንጹህና ከፍ ያለው ደረጃ መምራት ከመቻላቸው አስቀድሞ የሚለውጠው አምላካዊ ኃይል በውስጣቸው ሊሰማቸው ይገባል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 65.ChSAmh 76.1

    እንደ ጥንቱ ሁሉ ዛሬም በጣም አስፈላጊ የሆነው የአምላካዊ ቃል እውነት በሰብዓዊው መላምትና ግምት ገሸሽ ተደርጎአል፡፡ አያሌ የወንጌል አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መልእክት ሙሉ ለሙሉ በአምላካዊ መልእክትነት ይቀበሉም፡፡ አንዱ አዋቂ አንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲቃወም ሌላው ደግሞ በሌላኛው ክፍል ላይ ጥያቄ ያነሳል፡፡ ግላዊ ውሳኔና አስተያየታቸውን ከዓለም _ ምርጥና የላቀ አድርገው እየተከሉና የገዛ ሥልጣናቸውን መሰረት ያደረገ ትምህርት እየሰጡ መለኮታዊ እውነታ በተቸረው የአምላካዊ ቃል ላይ ውድመት ያደርሳሉ፡፡ የክህደት ዘር በስፋት እየተሰራጨ መላውን ግዛት ያካልላል፡፡ ሰዎች ግራ ከመጋባታቸው የተነሳ የትኛውን ማመን እንዳለባቸው ማወቅ ተስኖአቸዋል፡፡ አእምሮ ትክክል ብሎ ለመያዝ የተቸገረባቸው አያሌ እምነቶች ተስፋፍተዋል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 39.ChSAmh 76.2

    እርክስና ከዚህ ቀደም ደርሶበት የማያወቀውን እርካብ እየተቆናጠጠ ሲመጣ አያሌ የወንጌል መልእክተኞች “ሰላምና ደኅንነት” በመሻት የጩኸት ድምጾቻቸውን ያሰማሉ፡፡ የእግዚአብሔር ታማኝ መልእክተኞች ግን በጽናት መሥራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ሙሉ የጦር ልብስ ለብሰው ያለ ፍርሐት በድል አድራጊነት ከመገስገስና ለዚህ ጊዜ የተሰጠውን እውነትበቅርባቸው ላሉ ከማጋራት ውጪ ©ጊያቸውን አያቆሙም፡፡The Acts of the Apostles, p. 220.ChSAmh 76.3

    የኃይማኖቱ ዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል በዚህ ዘመን እንዲሰማ የሆነበት ምክንያት አለ፡፡ ለእግዚአብሔር ምህረት የተሰጠው ቦታ ኢምንት ሆኖአል፡፡ ብዙሃኑ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ሕግ ዋጋ በማሳጣት የሰው ሥርዓት የሆነውን ትምህርት በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ በምድራችን ላይ በሚገኙ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የእምነት መጉደል ተንሰራፍቷል፡፡ የእምነት መጉደል ወይም ጎዶሎ እምነት ሰፋ ባለ አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስን በግልጽ መካድ ማለት ሳይሆን በክርስትና ሽፋን ስር ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር መገለጫ አድርጐ አለማመን ነው፡፡ ጽኑ እምነት እና ጥልቅ ኃይማኖተኛነት ለባዶ የስመ ኃይማኖተኛነት ቦታቸውን ለቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ክህደትና ዓለማዊ መንፈስ ተንሰራፋ፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ተናግሮአል “በሎጥ ዘመንም እንዲሁ ነበር... የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል” (ሉቃስ 17፡ 28፣ 30)፡፡ በየዕለቱ የሚስተዋለው ክስተት የአምላካዊውን ቃል ፍጻሜ ማግኘት ይመሰክራል፡፡ ዓለም በፍጥነት ለመጥፋት እየተቃረበች ነው፡፡ በቅርቡ የሚገለጠው አምላካዊ ፍርድ ኃጢትንና ኃጢአተኞችን ያጠፋል፡፡-የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት፡ ገጽ 182: ChSAmh 77.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents