Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    text missing

    ከንጹህ ፍቅር የተነሳ የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት ምናልባት በሰብዓዊው ዐይን እንደ አነስተኛ ወይም አሳፋሪ ተደርጎ ቢታይ እግዚአብሔር አብልጦ የሚመለከተው በግለሰቡ ውስጥ በሥራ ላይ ያለውን ፍቅር እንጂ መጠኑን ባለመሆኑ በእርሱ ዘንድ ሙሉ ለሙሉ ፍሬያማ ነው፡፡Testimonies, vol, 2, p. 135.ChSAmh 364.1

    የአገልጋይ ስም ብቻ ይዘው በሰብዓዊ መመሪያዎችና ትዕዛዞች ሥራውን ከእንቅስቃሴ ገትተው ለነፍሳት ጥልቅ ፍቅር ሳይኖራቸው ለመንቀሳቀስ ከሚሞክሩ አንድ መቶ ሰዎች ይልቅ ፈቃደኛ አእምሮ ያላቸው፣ ራስ ወዳድ ያልሆኑና በእውነት የተለወጡ አሥር ሠራተኞች የላቀ ተግባር ማከናውን ይችላሉ፡፡--Testimonies, vol. 4, p. 602. ChSAmh 364.2

    ጌታ ሊያደርግልዎ የሚችለው እንጂ አሁን አሉኝ የሚሏቸው ብቃቶችም ሆኑ ወደ ፊት አፈራቸዋለሁ የሚሏቸው ነገሮች የስኬት ባለቤት ሊያደርግዎ አይችሉም፡፡ ሰው ሊያደርግ በሚችለው ነገር ላይ እጅግ ዉሱን መተማመን ሊኖረን ሲገባ--እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ አማኝ ነፍስ ሊያደርግ በሚችለው ነገር ላይ ግን አብልጠን ልንተማመንና በሙሉ ልባችን ልንቀበለው ይገባል፡፡ ከእርሱ ታላላቅ ነገሮችን ሲጠባበቁና በእምነት እርሱን እየመሉ ሲያድጉ ለመመልከት ይናፍቃል፡፡ በጊዜአዊውም ሆነ በዘላቂው መንፈሳዊ ጉዳይ ላይ ማስተዋል ሊሰጥዎ ይመኛል፡፡ አእምሮዎን ስል በማድረግ ብልሃትና ችሎታ ሊሰጥዎ ይችላል፡፡ ተሰጥኦዎችዎን በሥራው ላይ እያዋሉ እግዚአብሔር ጥበብ እንዲሰጥዎ ሲለምኑት የልብዎን መሻት ያገኛሉ፡፡Christ’s Object Lessons, p. 146.ChSAmh 364.3

    የጸጋው ዘይት ሰዎችን እያጀገነ እግዚአብሔር እንዲሠሩ የመደበላቸውን የየዕለት ሥራ የሚሠሩበትን መነሳሳት ይሰጣቸዋል፡፡ አምስቱ ዝንጉዎች ልጃገረዶች መብራት ይዘው የነበረ ቢሆንም (የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዕውቀት) የክርስቶስ ጸጋ ግን አልነበራቸውም፡፡ አንዱ ቀን አልፎ ሌላው በመጣ ቁጥር ያንኑ የተለመደውን ውጫዊ የአምልኮ ሥርዓት ከመፈጸም ውጪ አገልግሎታቸው ሕይወት ዐልባና የክርስቶስን ጽድቅ የተራቆተ ነበር፡፡ የጽድቅ ፀሐይ በልቦቻቸው ማህደርም ሆነ በአእምሮአቸው አልበራም፡፡ ከሕይወታቸውና ጸባያቸው ጋር ስምሙ መሆን የነበረበት የክርስቶስ ነጸብራቅ የሆነው የእውነት ፍቅር በእነርሱ ዘንድ አልነበረም፡፡ የጸጋው ዘይት ከአገልግሎት ጥረታቸው ጋር አልተዋሃደም፡፡ ኃይማኖታቸው እውነተኛ ፍሬ ሳይኖረው በባዶ ቅርፊት ብቻ የተሸፈነ ነበር፡፡ የሥነ መለኮት ቅርጽ ከመያዝ ውጪ ተመጻዳቂዎችና በክርስትና vይወታቸው የተታለሉ ነበሩ፡፡ በየቀኑ ሕይወታቸው ተለማምደውት ቢሆን ብልህ ያደርጋቸው የነበረውን የክርስቶስ እውነት ከመማር የተሰናከሉ ሆነዋል፡፡-- Review and Herald, March 27, 1894. ChSAmh 364.4

    የእግዚአብሔር ሥራ በሰብዓዊው ወኪሎችና በመለኮት ህብረት ወደ ፍጻሜ ማምራት ይኖርበታል፡፡ ለራሳቸው በቂ ነገር ያላቸው ወገኖች በአምላካዊው ሥራ በጉልህ የሚታይ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የጸሎት vይወት ከሌላቸው ግን እንቅስቃሴአቸው ከንቱ ይሆናል፡፡ እነዚህ ወገኖች ከቀስተ ደመናው ክብ ዙፋን በፊት ወዳለው የወርቅ መሠዊያየመልአኩ ዕጣን መመልከት ቢችሉ ክርስቶስ ለእኛ የሠራልን መልካም ሥራ ከጸሎታችን ጋር መቀላቀል እንደሚኖርበት ይረዳሉ፡፡ ያለበለዚያ አገልግሎታቸው እንደ ቃየን ሥዋዕት ዋጋ ቢስና ከንቱ ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ጉልህ ሆኖ እንደሚታየው እኛም መላውን የሰብዓዊ ወኪል እንቅስቃሴ መመልከት ብንችል፤ ፍርድን ማለፍ በሚችለው በክርስቶስ መልካም ሥራ የተቀደሰው አገልግሎት ክንውን ማግኘት የሚችለው በጸሎት በመትጋት ብቻ እንደሆነ ባስተዋልን ነበር፡፡ እግዚአብሔርን የሚያገለግለውንና የማያገለግለውን ለይተን መመልከት በቻልን ነበር፡፡Review and Herald, July 4, 1893.ChSAmh 365.1

    ሥርዓታዊ አምልኮ ለዚህ ዘመን ችግር የመፍትሔ ሃሳብ የለውም፡፡ ማንኛውንም ውጫዊ ኃይማኖታዊ ሥርዓት መፈጸም ብንችልም ነገር ግን ዝናብ እንዳልወረደባቸውና ጠል እንዳላረሰረሳቸው የጊልቦዓ ተራሮች ለመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተራቆትን እንሆናለን፡፡ መንፈሳዊ ርጥበት ለሁላችንም ያስፈልገናል፡፡ ልባችንን የሚያለሳልስና ለአምላካዊ ፈቃድ የሚያስገዛ ብሩህ የጽድቅ ፀሐይ ጨረር ሊፈነጥቅልን የግድ ነው፡፡ ሁል ጊዜም ለመርኅ እንደ ጠጣር ዐለት ጽኑ አቋም ሊኖረን የተገባ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መርኅዎችን ልንማርና በተቀደሱ ተሞhሮዎች በተግባር ልንገልጻቸው ይገባል፡፡--Testimonies, vol. 6, pp. 417, 418. ChSAmh 366.1

    ስኬት ለአገልግሎት ጉልበትን የማፍሰስና የፈቃደኝነትን ያህል በተሰጥኦ ላይ አብልጦ ጥገኛ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለን የአስደናቂ ተሰጥኦ ባለቤት መሆናችን ሳይሆን—የየዕለቱን ተግባራችንን በንቃት ማከናወናችን፣ የደስተኛ መንፈስ ባለቤት መሆናችን፣ በአጉል ተጽእኖ ስር አለመውደቃችንና ስለ ሌሎች ደኅንነት ግድ የሚለን መሆናችን ነው፡፡ በትሁቱ ነፍስ ውስጥ ምርጥ የሆነ እውነተኛ ችሎታ ሊገኝ ይችላል፡፡ የተለመደው የዕለት ከዕለት አገልግሎት በፍቅርና በታማኝነት ታጅቦ መቅረብ ሲችል በእግዚአብሔር ፊት ውብና ያማረ ይሆናል፡፡--Prophets and Kings, p. 219. ChSAmh 366.2

    ጠንካራና ውበት የተላበሰ መደበኛ ባህሪ የሚነባው በግለሰቡ የሥራ ውጤት ነው፡፡ እናም ታማኝነት መጠኑ አነስተኛም ይሁን ግዙፍ የህይወታችን መገለጫ ባህሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ በአነስተኛ ነገሮች መታመን፣ አነስተኛ መጠን ያላቸው የደግነትና የታማኝነት ተግባራት መፈጸም፤ የህይወትን መንገድ አስደሳች ያደርጉታል፡፡ ሥራችን በምድር ሲጠናቀቅ፣ በታማኝነት የፈጸምናቸው አነስተኛ ተግባራት ሊጠፋ የማይችሉ መልካም ተጽእኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ 661 ChSAmh 366.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents