Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቅርበት ያለው ወዳጃዊ ግንኙነት መፍጠር

    ማንኛውም አማኝ በግል ረት ወደ ሕዝቦች እንዲቀርብ ይፈለጋል፡፡ ለስብከት የሚውለው ከፍ ያለ ጊዜ ሰዎችን በግል ለመድረስ ጥቅም ላይ ቢውል አመርቂ ውጤት መታየት ይችላል፡፡--The Ministry of Healing, p. 143. ChSAmh 162.1

    የአምላካዊው የጸጋ ቃል ወደ እያንዳንዱ ነፍስ መኖሪያ ስፍራ ይደርስ ዘንድ የጌታ ምኞት ነው፡፡ ይv ክርስቶስ ይጠቀምበት የነበረ አካሄድ በግል በሚደረግ የላቀ ጥረት እውን ሊሆን የግድ ነው፡፡ Christ’s Object Lessons, p. 229.ChSAmh 162.2

    በችሎታቸው ሳይመጻደቁ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በእምነት ሌሎችን የመርዳት ብርቱ ምኞት የሚያድርባቸው ወንዶችና ሴቶች ነፍሳትን ለhርስቶስ በመማረኩ አገልግሎት እጅግ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ናቸው፡፡ የሱስ ሊቀርቡት ምኞት ካደረባቸው ወገኖች ጋር ወዳጃዊ ግንኙነት እየፈጠረ ከዚህ ተመሳሳይ ሥራ ሠርቶአል፡፡--Gospel Workers, p. 194.ChSAmh 162.3

    ክርስቶስ ለሰዎች የነበረው ዓይነት ርኅራኄ ተላብሰን እያንዳንዳችን ነፍሳትን በግል እየቀረብንና ዘላለማዊ ሕይወት በሚያስገኙት በታላላቆቹ ጉዳዮች ዙሪያ እያወጋን ውስጣዊ ፍላጎታቸውን የመቀስቀስ ምኞት ሊያድርብን ይገባል፡፡ ምናልባት በግል የምንመሰክርለት ሰው ልብ እጅግ ከመደንደኑ የተነሳ አዳኙን ለእርሱ ማቅረብ ጥቅም የሌለው ሊመስል ይችላል፡፡ አመክንዮ ወደፊት መንቀሳቀስ ቢሳነውና የመነጋገሪያ ነጥቦች የማሳመን አቅም ቢያንሳቸው እንኳበወንጌል መልእክተኛው የግል ጥረት የሚተዋለው የክርስቶስ ፍቅር ድንጋዩን ልብ አለስልሶ የእውነት ዘር ሥር እንዲሰድ ማድረግ ይችላል፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 57. ChSAmh 162.4

    እያንዳንዳችን በግል በየአካባቢያችን ከሚገኙ ነፍሳት ጋር ትውውቅ እንፍጠር፡፡ ስብከት መሠራት ለሚኖበት ሥራ ተገቢውን ውጤት ማስገኘት አይችልም፡፡ እርስዎ ነፍሳትን በመጎብኘት በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የእግዚአብሔር መላእክት ይገኛሉ፡፡ ይህ ሥራ በውክልና፣ በገንዘብ ወይም በጉባዔ ላይ በሚቀርብ ስብከት ክንውን ማግኘት አይችልም፡፡ ይልቁንም የቤት ለቤት ጉብኝት በማድረግ፣ እርስ በርስ በማውራት፣ በመጸለይና የድጋፍ ስሜት በማሳየት ልቦችን ማሸነፍ ይቻላል፡፡ አንድ አማኝ ሊሰጥ የሚችለው ከፍ ያለ አገልግሎት ቢኖር ይኸው ነው፡፡ አገልግሎቱን ለመስጠት ቆራጥ፣ የማያወላውል፣ በትጋት የሚሠራ እምነት፣ ታካችነት የማይታየበት ትዕግሥትና ለነፍሳት ሊኖር የሚገባ ጥልቅ ፍቅር ወሳኝ ናቸው፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 41.ChSAmh 163.1

    የቤተ ክርስቲያን መሠረት የተጣለው ዮሐንስ፣ እንድርያስ፣ ስምዖን፣ ፊልጶስና ናትናኤል በተጠሩ ጊዜ ነበር፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ደቀ መዛሙርት ሁለቱን ወደ ክርስቶስ መራቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው እንድርያስ ወንድሙን ፈልጎ ካገኘው በኋላ ወደ መድኒታችን አመጣው፡፡ ቀጥሎም ፊልጶስ ተጠራና ናትናኤልን ፍለጋ ሄደ፡፡ ይህ ምሳሌ የግል ጥረት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለዘመዶቻችን፣ ለጓደኞቻችንና ለጎረቤቶቻችን ጥሪ ማድረግ እንዳለብን ሊያስተምረን ይገባል፡፡ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ተዋውቀናል እያሉ ነገር ግን አንድ ነፍስ እንኳ ወደ መድኃኒታችን ለማምጣት የግል ጥረት አድርገው የማያውቁ አሉ፡፡ ይህን ሥራ ለመጋቢው ይተዉለታል፡፡ መጋቢው ለተጠራበት ሥራ በቂ ሥልጠና ሊኖረው ቢችል እንኳ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለቤተ hርስቲያን አባላት የሰጠውን የሥራ ድርሻ እርሱ ማከናወን አይችልም፡፡ChSAmh 163.2

    ከአፍቃሪ ክርስቲያን ልብ የመነጨ አገልግሎት የሚያሻቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ጎረቤቶች፣ ወንዶችና ሴቶች--የቤተ ክርስቲያን አባላት የግል ጥረት አድርገውላቸው ቢሆን ለመዳን ሲችሉ የጠፉ ብዙ ናቸው፡፡ የግል ጥሪ የሚጠባበቁ ብዙዎች አሉ፡፡ በየቤተሰባቸን፣ በመኖሪያ ክልላችንና በምንኖርበት ከተማ ሁሉ በhርስቶስ ወንጌላዊነት የምንሠራው ብዙ ሥራ አለ፡፡ ክርስቲያኖች ከሆንን በዚህ ሥራ መደሰት አለብን፡፡ አንድ ሰው ንስሐ ገብቶ እንደ ተመለሰ የሱስ የከበረ ወዳጁ መሆኑን ለሌሎች ለማሳወቅ ወዲያውኑ ፍላጎት ያድርበታል፡፡ የሚያድነውና የሚቀድሰው እውነት በልብ ውስጥ ተከርችሞ መቀመጥ አይችልም፡፡The Desire of Ages, p. 14. ChSAmh 163.3

    በግል የሚደረግ የወንጌል አገልግሎት ብርሃን ወደ ሌሎች መስረጽ ከሚችልባቸው ውጤታማ መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በቤተሰብዎ መሃል፣ በጎረቤትዎ መኖሪያ እንዲሁም በታመመው ሰው አልጋ አጠገብ ተገኝተው የተረጋጋ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ማቀረብና የየሱስን ቃላት እውነት መናገር ሲችሉ--አብቦ ፍሪ ማፍራት የሚችለውን የከበረ ዘር ይዘራሉ፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 428, 429. ChSAmh 164.1

    ቀደም ባሉት ጊዜያቶች ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮች እንዳይበላሹ በጨው ይታሹ እንደ ነበር-ሰዎችን በግል መድረስ የምንችለው የማዳን ኃይል ያለውን ወንጌል ስንይዝ ነው፡፡ ሰዎች በግል እንጂ በጋራ አይድኑም፡፡ በግል ተጽእኖ ማሳደር መቻል በራሱ ኃይል እንደመሆኑ የዘላለማዊው ነገር ጥቅም ተጋሪ እንዲሆኑ ወደ ምንሻቸው ሁሉ መቅረብ አለብን፡፡--Thoughts from the Mount of Blessing, p. 36. ChSAmh 164.2

    የሱስ ሰው ሁሉ በነፍስ ወከፍ ለመንግሥቱ ታዳሚ የሚያደርገው ጥሪ ሊደርሰው እንደሚገባ ተገነዘበ፡፡ _ ለእነርሱ _ በጎ ሁሉ በመመኘት በመካከላቸው በመገኘቱ ልባቸውን ነካው፡፡ በዐውራ መንገዶች፣ በየግል ቤቶቻቸው፣ በጀልባዎች ላይ፣ በምኩራብ፣ በሐይቅ ዳርቻዎችና በሠርግ ድግሥ ላይ ፈለጋቸው፡፡ በየዕለት ተግባራቸው ተገናኛቸው፤ ስለ ዓለማዊ ጉዳያቸው ጭምር እንደሚጨነቅላቸው ተገለጸ፡፡ የመለኮትን በጎ ተጽእኖ በየቤቱ እንዲኖር ለማድረግ ትምህርቱን በየቤተሰቡ አዳረሰ፡፡ ብርቱ ርኅራኄው ልቦችን ወደ ራሱ መሳብ ቻለ፡፡The Desire of Ages, p. 151.ChSAmh 164.3

    ወደ ሰዎች ለመድረስ--ክርስቶስ የተጠቀመበት ዘዴ ብቻውን የእውነተኛ ስኬት ባለቤት ያደርጋል፡፡ የሰዎችን በጎ የሚሻው ክርስቶስ አብሮአቸው በመቀላቀል፣ርኅራኄ በማሳየትና በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በማገልገል በእርሱ እንዲተማመን አድርጎ ልባቸውን ማሸነፍ ቻለ፡፡ ከዚያም “ተከተሉኝ” ሲል ጥሪ አቀረበላቸው፡፡The Ministry of Healing p 143. ChSAmh 165.1

    እኛም ከክርስቶስ በተመሳሳይ ልንሠራ ይገባል፡፡ እርሱ በአይሁድ ቤተ አምልኮ፣ በመንገድ ዳር፣ በጀልባ ላይ፣ በፈሪሳዊው ግብዣ ወይም በቀራጩ ማዕድ ላይ በመገኘት ከፍ ላለው ሕይወት ተገቢነት ስላላቸው ነገሮች ለሰዎች ተናግሮአል፡፡ ከተፈጥሮ ጋር ቁርኝት ያላቸው ነገሮችም ሆኑ የየዕለት የሕይወት ክስተቶች ከእርሱ የእውነት ቃላት ጋር የቀረበ ትስስር ነበራቸው፡፡ በበሽታ የተያዙትን በመፈወሱ፣ ያዘኑትን በማጽናናቱና ልጆቻቸውን በእቅፉ አኑሮ በመባረኩ የአድማጮቹ ልብ ወደ እርሱ የተሳበ ነበር፡፡ ትኩረታቸው ከእርሱ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ--ከአንደበቱ የሚወጣው እያንዳንዱ ቃል ለእያንዳንዱ ነፍስ በሕይወት ላይ ሕይወትን የሚሰጥ ነበር፡፡ChSAmh 165.2

    ክርስቶስ የተጠቀመበት ዘዴ የእኛም ሊሆን ይገባል፡፡ ስለ አዳኙ ለሌሎች ለመመስከር የሚያስችሉንን ዕድሎች በማንኛውም የምንገኝበት ስፍራ መመልከት ይኖርብናል፡፡ መልካም በማድረጉ ረገድ ክርስቶስ የተወልንን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ለእርሱ የተከፈቱ ልቦች ለእኛም ይከፈታሉ፡፡ እንደ ነገሩ ሳይሆን ነገር ግን ከመለኮት ፍቅር በተወለደ ብልሃትና ጥንቃቄ “ከዐሥር ሺሆችም የሚልቅ” “እንከን የማይወጣለት” መሆኑን ልንነግራቸው እንችላለን፡፡ ሥራው የመናገር መክሊታችንን ተጠቅመን ወደ አገልግሎት ልንገባ የምንችልበት ከፍ ያለ ኃላፊነት ነው፡፡ ኃጢአትን ይቅር የሚል አዳኝ አድርገን—ክርስቶስን እናቀርብ ዘንድ እንሆ መልእክቱ ተሰጥቶናል፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 338, 339.ChSAmh 165.3

    የእርሱ መኖር ለቤተሰቡ ፍጹምና በጎ ተጽእኖ ነበረው፤ ሕይወቱም በሕብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች መካከል እንደ እርሾ ነበር፡፡ ሳይተናኮልና ሳይረክስ ስለ ምንም ሃሳብ በማይጨነቁ፣ በጋጠወጦች፣ በባለጌዎች፣ በማይራሩ ቀራጮች፣ በብኩኖች፣ በረከሱ ሳምራውያን፣ በአሕዛብ ወታደሮች፣ በሥርዓተ አልበኛ የገጠር ሰዎችና ቅልቅል በሆኑ ሕዝቦች መካከል ተመላለሰ፡፡ ሰዎች በከባድ ሸክም ምክንያት ዝለው ባያቸው ጊዜ የርኅራኄ ቃል ተናገራቸው፡፡ ሸክማቸውን ተጋራ፡፡ ከሥነ ፍጥረት ስለ እግዚአብሔር ፍቅር፣ቸርነትና ደግነት የተማረውን ትምህርት አስተማራቸው:፡ ChSAmh 166.1

    በትክክል ቢጠቀሙባቸው የዘላለም ብልጽግና የሚያስገኙላቸው የተከበሩ ተሰጥኦዎች ያሏቸው መሆኑን እንዲያውቁ ሁሉንም አስተማራቸው፡፡ የሕይወትን ከንቱነት አረም ነቀለ፡፡ እያንዳንዷ ደቂቃ ዘላለማዊ ውጤትን የምታስገኝ ስለሆነች እንደ ልዩ ጥሪት በጥንቃቄ እንድትያዝና ለተቀደሰ ተግባር እንድትውል በእራሱ አርአያነት አስተማረ፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ዋጋ ቢስ ነው ብሎ አላላፈውም፤ ነገር ግን ለእያንዳዱ ነፍስ ፈዋሽ መድኃኒት ሰጠ፡፡ በየትኛውም ሰብዓዊ ስብስብ መካከል ሲገኝ ለጊዜውና ለሁኔታው ተገቢ የሆነ ትምህርት ያቀርብ ነበር፡፡ ክፉና ዋጋ ቢስ ናቸው ለተባሉት ሰዎች ሁሉ ከክፉ ነገር የነጹና ደግ ለመሆን የሚያስችላቸውን ማረጋገጫ በፊታቸው በማቅረብ ለእግዚአብሔር ልጅነት የሚያበቃቸውን ባህሪ ለማግኘት እንደሚችሉ ተስፋ ሊያሳድርባቸው ፈለገ፡፡ በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ገብተው ከወጥመዱ ለመውጣት ያቃተቸውንም ተገናኛቸው፡፡ እንደነዚህ ላሉ ተስፋ ለቆረጡ፣ ለታመሙ፣ ለተፈተኑና ለወደቁ ሁሉ የሱስ የሚያስፈልጓቸውን የርኅራኄ ቃላት በሚያስተውሉት መንገድ ይነግራቸው ነበር፡፡ ሌሎች የተገናኛቸው ደግሞ ከነፍሳት ጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው በመታገል ላይ ነበሩ፡፡ ለእነዚህም የእግዚአብሔር መላእክት ከጎናቸው እንደሆኑና ድል እንደሚሱበማረጋገጥ እንዲበረቱ አደፋፈራቸው፡፡--The Desire of Ages, p. 91.ChSAmh 166.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents