Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጀግኖችና እውነተኞች

    በአደጋ በተከበቡት በእነዚv ወቅቶች ቤተ ክርስቲያን እንደ ጳውሎስ ለሌላው ጥቅም ራሳቸውን ያስተማሩ፣ በአምላካዊው ነገሮች ዙሪያ ጥልቅ ተሞክሮ ያላቸው፣ በቅንነትና በቅንአት የተሞሉ ሠራተኛ ሠራዊቶች ያስፈልጓታል፡፡ ራሳቸውን ለአገልግሎት ቀድሰው የሰጡ፣ ስለ ሌሎች መሥዋዕትነት የሚከፍሉ፣ ፈተናና ኃላፊነትን የማይርቁ፣ ጀግኖችና እውነተኞች፣ ክርስቶስ በልባቸው ውስጥ “የክብር ተስፋ” የፈጠረባቸው፣ ከንፈሮቻቸው በቅዱስ እሳት ተነክተው “ቃሉን የሚሰብኩ” ሰዎች ሊኖሯት ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እንደነዚህ ዓይነቶቹን በመፈለግ እየጠወለገ፣ አደገኛ ስvተቶች ላይ እየወደቀ፣ ግብረገባዊው ማንነት እየተመረዘና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰብዓዊው ዘር ተስፋ እንደ ዋግ እየተመታ ይገኛል፡፡—The Acts of the Apostles, p. 507.ChSAmh 339.1

    በእልv አስጨራሽ፣ አደጋና ሽንፈት በተጋረጠበት፣ ሰብዓዊ ሥቃይ በበረታበት ውጊያ መሃል ነፍሳትን የማዳን ሥራ ሳይስተጓጎል ሊቀጥል ይገባል፡፡ በአንድ የውጊያ ዐውድ ጥቃት ከሚሰነዝሩ የወገን ጦሮች መሃል አንደኛው በጠላት መንጋ እንዲያፈገፍግ ሲገደድ አርማው ግን በተተከለበት መውለብለቡን ቀጥሎ ነበር፡፡ ኃላፊያቸው አርማውን ነቅለው እንዲያፈገፍጉ ትዕዛዝ ሲሰጥ“ይልቅስ ወታደሮቹን ወደ አርማው አምጣቸው! የሚል ጽሑፍ በአርማው ላይ ይነበብ ነበር፡፡ ወደ እያንዳንዱ ታማኝ የአምላካዊው ትእዛዛት ተሸካሚ ሠራተኛ በተዋረድ እየተላለፈ ያለው ሥራ ይኸው ነውተዋጊዎቹን ወደ አርማው ማምጣት! በሙሉ ልብ እንድንንቀሳቀስ ጌታ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ ክርስቲያን ተብለው የተጠሩ የእያሌዎች ኃጢአት ራሳቸውንም ሆነ የሚያውቋቸውን ወደ አምላካዊው ትእዛዛት ለማምጣት ወኔና ጉልበት ማጣታቸው እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡Testimonies, vol, 9, pp. 45, 46.ChSAmh 339.2

    የእነርሱ ብርታት፣ ወኔና አርአያነት በእጅጉ በሚፈለግበት የከፋ አደጋ ወቅት ትክክለኛውን ጽኑ አቋም ለመያዝ የሚርዱ ሰዎችን እግዚአብሔር መጠቀም አይችልም፡፡ ከሥልጣናትና ከኃይላት፣ ከዚv ጨለማ ዓለም ገዢዎችና ከመንፈሳዊ እርክስና ጋር ክፉውን በታማኝነት ለሚዋጉ ወገኖች እግዚአብሔር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ “ደግ አድርገሃል አንተ ታማኝ አገልጋይ” የሚላቸው እንደነዚህ ዓይነቶቹን ይሆናል፡፡--Prophets and Kings, p. 142. ወደ ዓለም ይዘውት የሚሄዱት አምላካዊ መልእክት የቱንም ያህል ከባድ ውጤት ሊያስከትል ቢችልና ያላቸውን ሁሉ የሚያሳጣ መሥዋዕትነት ቢያስከፍላቸው እንኳእውነትን እንደ ኤልያስ፣ ናታንና መጥምቁ ዮሐንስ በታማኝነትና በጀግንነት እንዲናገሩ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርባል፡፡Prophets and Kings, p. 142.ChSAmh 340.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents