Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የበለጸገ አነጋገር

    ብርቱ ሆኖ የበለጸገ የአነጋገር ክህሎት ጥቅም ላይ ማዋል ከእያንዳንዱ የክርስትና አገልግሎት ዘርፍ ይጠበቃል... ቋንቋችን ያልተበረዘና የታረመ፣ ንግግራችንና የድምጻችን ቃና የሰዎችን ልብ የሚነካ፣ ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላት ደግ፣ ትህትናና ምግባር የተላበሱ እንዲሆኑ አድርገን መለማመድ ይናርብናል፡፡— Christ’s Object Lessons, p. 336.ChSAmh 308.1

    እያንዳንዱ አገልጋይና ምህር ለሕዝብ የሚያቀርበው መልእክት በነፍሳት ላይ ዘላለማዊ ፍላጎት የሚያሳድር ሊሆን እንደሚገባ መጤን ይኖርበታል፡፡ በእነዚያ የተነገሩ እውነቶች በታላቁ የፍርድ ቀን ነፍሳት ይዳኛሉ፡፡ መልእክቱን የሚያቀርበው ሰው አኳኋን አድማጩ የተነገረውን እውነት እንዲቀበል ወይም እንዲቃወም ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ስለዚv ቃላቶች ለመስተዋል የሚጋብዙና ልብን የሚነኩ ሆነው ሊነገሩ ይገባል፡፡ የሚቀርበው ንግግር መልእክቱ የሚጠይቀውን ቅንነትና እርጋታ የተላበሰጉልv ሆኖ የቀረበና የመልእክቱ ጭብጥና ክብደት እንዲሰማ ሆኖ የበጸገ ይሁን፡፡Christ’s Object Lessons, p. 336.ChSAmh 308.2

    ሌሎችን ወደ አምላካዊው ፍቅር ቀለበት ለመሳብ በሚያደርጉት ጥረት የታረመ ቋንቋዎ፣ ከልብ የመነጨ አገልግሎትዎና በሐሴት የተሞላ ምግባርዎ ለጌታ ጸጋ ኃይል ምስክር ይሁን፡፡The Ministry of Healing p. 156.ChSAmh 308.3

    እያንዳንዱ ክርስቲያን የማይመረመረውን የክርስቶስ ባለጸግነት ለሌሎች እንዲገልጥ የተጠራ እንደመሆኑ ንግግሩ ፍጹም እንዲሆን መጣር አለበት፡፡ የሚያቀርበው የእግዚአብሔር ቃል (ድማጮቹ የሚስተዋል የፍቅር መልእክት ይሁን፡፡ እግዚአብሔር የሰብዓዊ መልእክተኞቹን አነጋገር ስድና ያልታረመ አድርጎ አላነጸውም፡፡ የሰማይ ሞገድ መተላለፊያ የሆነው ሰብዓዊው ፍጡር እንዲኮሰምን ወይም ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አምላካዊው ፈቃድ አይደለም፡፡Christ’s Object Lessons, p. 336.ChSAmh 308.4

    የእግዚአብሔር ሕዝቦች በትዕግሥት፣ በደግነት፣ በትህትናና በበገነት ተገቢውን ትምህርት ይቀስማሉ፡፡ ወዳጃቸው ክርስቶስ ግልብና ደግነት የጎደላቸውን ቃላት ወይም አጓጉል ስሜቶች እንደማይደግፍ ሁሌም እያስታወሱ እውነተኛውን የክርስትናን መልካም ምግባር በተግር ይለማመዳሉ፡፡ ከአንደበቶቻቸው የሚወጡ ቃላት ቁጥብና የሚያንጹ ይሆናሉ፡፡ ይህ ታላቅና ቅዱስ የሆነውን አገልግሎት እንዲያከናውኑ ከእግዚአብሔር የተበደሩት የንግግር ኃይል እንደ ከበረ መክሊት ይታያል፡፡-Gospel Workers, p. 97. ChSAmh 309.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents