Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሰይጣናዊው አፍዝ አደንግዝ

    የእግዚአብሔር ሕዝቦች የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ በመቀበል ምልክቶችን ተጠቅመው የሚገኙበትን ጊዜ ለይተው ሊያውቁ ይገባል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአተ ምልክቶች እጅግ ግልጽና ለጥርጣሬ የሚሆን ቀዳዳ እንኳ የሌላቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የጊዜውን ሁናቴዎች በመመልከት እውነትን እቀበላለሁ የሚል እያንዳንዱ ምዕመን ሕያው ሰባኪ ሊሆን ይገባል፡፡ ሰባኪዎችም ሆኑ ምዕመናን በንቃት ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ መላው ሰማይ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ የምድር ታሪክ ትዕይንት በፍጥነተ በመገባደድ ላይ ነው፡፡ እኛ በምድር የመጨረሻዎቹ በአደጋ የተሞሉ አስጊ ወቅቶች ላይ እንገኛለን፡፡ ከፊት ለፊታችን ታላላቅ አደጋዎች የተደቀኑ ቢሆንም እኛ ግን አልነቃንም፡፡ ከፍተኛ ተጋድሎ በሚጠይቀው አገልግሎት እንቅስቃሴና ቅንነት የጎደለው ማንነት አስፈሪ ገጽታ ይኖረዋል፡፡ የዚህ አፍዝ አደንግዝ መንስኤ ሰይጣን -- Testimonies, vol. 1, pp. 260, 261. ChSAmh 49.1

    ምዕመናን የከበረውን እውነት በማያውቁ ላይ ብርሃን በመፈንጠቅ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊት ስለማይለማመዱ አለማመን እንደከፈን ጨርቅ ቤተ ክርስቲያናችንን ገንዞ ይዞአል፡፡ ይቅር ተብለው ባገኙት ብርሃን ሐሴት የሚያደርጉ ነፍሳት እውነትን ለሌሎች ያሳውቁ ዘንድ ጌታ ጥሪ ያደርግላቸዋል፡፡--General Conference Bulletin, 1893, p. 133. ChSAmh 50.1

    የእግዚአብሔር ሕዝቦች እውነትን በማሰራጨት የድርሻቸው እንዳይወጡ፣ እጆቻቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡና በመጨረሻ ቀልለው እንዲገኙ ለማድረግ ሰይጣን እየሻተ ይገኛል፡፡Testimonies, vol. 1, p. 260. በሰው ልጆች ላይ ብርቱ አደጋ ተጋርጦአል፡፡ አያሌዎች እየጠፉ ነው፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ነን ከሚሉት መሃል የእነዚህ ነፍሳት ሸክም እየተሰማቸው ያሉ እንዴት ጥቂት ናቸው! የዓለም መዳረሻ ልብ አንጠልጣይ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ቢሆንም--ሟች ለሆነው ሰብዓዊ ፍጡር የተሰጡትን እውነቶች እናምናለን የሚሉትን አማኞች እምብዛም እያነቃነቀ ያለ አይመስልም፡፡ ሰብዓዊነት—ሰብዓዊነትን በመንካት ሰብዓዊነት ወደ መለኮት መሳብ ይችል ዘንድ ክርስቶስ ሰማያዊ መኖሪያውን ትቶ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ እንዲወስድ ያደረገው ፍቅር እጥረት በብዙዎች ዘንድ ይስተዋላል፡፡ የእግዚአብሔር ሐዝቦች የሚገኙበትን ሰዓት ግዴታና ተግባር ከማስተዋል የሚገታ በድን አፍዝ አደንግዝ አለ፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 303. ChSAmh 50.2

    ሰይጣን ኃይሉን አስተባብሮ ነፍሳትን ለመማረክ ግዴለሽ፣ ፈዛዛና ስንፍና የተጫናቸውን ክርስቲያኖች ይጠቀማል፡፡ ምንም እንኳ ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ሥራ ለክርስቶስ እየሠሩ ባይሆንም ከእርሱ ጋር እንደሆኑ የሚያስቡ ወገኖች ጠላት መግቢያ ቀዳዳ አግኝቶ ተጠቃሚ የሚያደርገውን ተግባር እንዲያከናውን እየፈቀዱለት ይገኛሉ፡፡ ለጌታ ትጉህ ሠራተኞች ከመሆን በመሰናከል--የተሰጣቸውን አገልግሎት ሲተዉም ሆነ መሰንዘር የነበረባቸውን ቃላት ሳይናገሩ ሲቀሩ ለክርስቶስ ሊያሸንፏቸውበእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች ይችሉ የነበሩ ነፍሳት በሰይጣን ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ይፈቅዳሉ፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 280. ChSAmh 50.3

    መጽሐፍ ቅዱስ ሳጠና በእነዚህ የመጨረሻ ጊዜያቶች በሚገኙ የእግዚአብሔር እስራኤላውያን ዙሪያ የማስጠንቀቂያ ደወል ሰማሁ፡፡ እነዚህ ወገኖች በማንቀላፋታቸውና አጥብቀው ከዓለም ጋር በመመቻቸታቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ለመመልከት አስቸጋሪ ነበር፡፡ በክርስቶስና በሕዝቡ መካከል የነበረው ርቀት እየሰፋ ይሄድ የነበረ ሲሆን በእነርሱና በዓለም መካከል የነበረው ደግሞ እየጠበበ የሚሄድ ነበር፡፡ የክርስቶስን ሕዝቦችና ዓለምን ይለዩ የነበሩት ምልክቶች ለመጥፋት ተቃርበው ነበር፡፡ የጥንት እስራኤላውያን ያደርጉ እንደነበረው በተመሳሳይ ሕዝቡ በዙሪያው ያለውን የጥፋት ርኩሰት ይከተል ነበር፡፡--Testimonies, vol. 1, p. 277.ChSAmh 51.1