Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ባሉበት ሁናቴ ርካታን እንዳገኙ የሚሰማቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች

    ራሳቸውን ከአገልግሎት ገተተው ደግነትና ቸርነት የተላበሰ የአምልኮ ስሜት ያላቸውንና መልካም የማድረግ ፍቅር ያደረባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ተመልክቼ ነበር፡፡ እነዚህ ምንም የማያሳስባቸውና ባሉበት ሁናቴ ርካታ እንደተጎናጸፉ ሆኖ የሚሰማቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ምናልባትም ዕድሉ ተሰጥቶአቸው ቢሆን ወይም ይበልጥ የተመቻቹ ሁናቴዎች ቢገጥሟቸው ታላቅና መልካም ሥራ መሥራት ይችሉ እንደነበር አድርገው ራሳቸውን ይሸነግላሉ፡፡ በዚህም የተመቻቸ ያሉትን ዕድል እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ለደኻ ተገቢውን ክፍያ ለመፈጸም ይስነቆናሉ፣ የሚስኪኑን አስተሳሰብ እንደ ደካማ ይቆጥራሉ፡፡ ደኻውን ስለሚንቁ ለሌሎች በጎ ለማድረግም ሆነ በመhሊቱ እነርሱን ለመባረክ ሊጠራ እንደማይችል ያስባሉ፡፡ ስለዚህ ጥቅም ላይ ሊያውላቸው የሚገቡ፣ ካልተጠቀመባቸው ዝገት ሊበላቸው የሚችሉ ወይም ጉድጓድ ቆፍሮ ሊቀብራቸው የማይገቡ-ከገዛ ማንነቱ ሊወጡ የሚችሉ መክሊቶች ሊኖሩት አይችሉም ብለው ያምናሉ፡፡ ራሳቸውን ለስስትና ለራስ ወዳድነት አሳልፈው የሰጡለንፉግ ድርጊታቸውና ላባከኑት መክሊት ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡ ነገር ግን በቸርነት የተሞሉ ስሜቶች ያሏቸውና መንፈሳዊ ነገሮችን ለመለየት በተፈጥሮ 48 በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች ፈጣን የሆኑ - ገና አልመጣም ያሉትን የተሻለ ዕድል ፈዘው በመጠባበቅ ዝግጁነታቸው ፈቅደው ከያዙት ራስ ወዳድነት ጋር ልዩነት እንዲፈጥር እያደረጉ፤ የእነርሱን ሁናቴ ነፍሳቸው በስስት ከተሞላው ጎረቤታቸው ይልቅ የተሻለ አድርገው የሚያስቡ ከሆነ--በእርግጥ ራሳቸውን እያታለሉ ነው፡፡ ብዙ መክሊቶች በተሰጡን ቁጥር በስጦታዎቹ የመጠቀም ኃላፊነታችን ያንኑ ያህል ይጨምራል፡፡ ጌታ የሰጣቸውን መክሊቶች ጥቅም ላይ የማያውሉ ከሆነ ነፍሳቸው ከሚንቀው የጎረቤቶቻቸው ሁናቴ የተሻሉ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አገልጋይ “የጌታውን ፍላጎት እያወቀ ፈቃዱን የማያደርግ” ነው፡፡-Testimonies, vol. 2, pp. 250, 251. ChSAmh 48.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents