Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሰማያዊ ወኪሎች ተባባሪነት

    የመላእክትን ሥራ ከመሥራታችን አስቀድሞ የአገልግሎቱን ምንነት በሚገባ ማስተዋል ይኖርብናል፡፡ እያንዳንዱ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ የሰማያዊ አካላት ትብብር እንደማይለየው በሚገባ ማስታወስ ይኖርበታል፡ በሰብዓዊው ዓይኖች የማይታዩት የብርሃን ኃይላትና ሠራዊት በአምላካዊው ተስፋ በማመን ራሱን ዝቅ ያደረገውን የትሁቱን አገልግሎት ይጎበኛሉ፡፡ በኃይል የሚያንጸባርቁት ኪሩቤል፣ ሱራፌልና የሰማይ “መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?” — The Acts of the Apostles, p. 154. ChSAmh 358.1

    ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ወደር የማይገኝለት ሠራተኛ እንደ ነበር እናስታውስ፡፡ የዘራውን ዘር ውሃ ያጠጣ የነበረ ይህ አምላh ወደ ልቦች የሚደርሰውን ቃል በአእምሮአችሁ ያኖራል፡ ፡Testimonies, vol. 9, p. 41. ራሳችሁን ለጌታ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ቀድሳችሁ ስጡ፡፡ ብርታታችሁ የሆነው እርሱቀኝ እጃችሁ በመሆን በምህረት የተሞላ ዕቅዱን ለመተግበር ያስችላችኋል፡፡— Testimonies, vol. 9, p. 41. ChSAmh 358.2

    ሰማያዊ አካላት ቆራጥ እምነትና በእንቅስቃሴ ወደ ፍጽምና የሚሄድ ባህሪ እንዲኖራቸው ከሚመኙ ሰብዓዊ ወኪሎች ጋር አብረው ይሠራሉ፡፡ ክርስቶስ በአገልግሎት ገበታ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ ሰው—እኔ እጆችህን ይዤ ልረዳህ ከጎንህ ነኝ—በማለት ይናገራል፡—Christ’s Object Lessons, p. 332.ChSAmh 358.3

    ሰብዓዊው ማንነት ከአምላካዊው ፈቃድ ጋር ትብብር መፍጠር ሲችል በኃይልና ልዕልና የተሞላ ይሆናል፡፡ የእርሱን ትእዛዝ ተከትሎ የሚሠራ ማንኛውም አገልግሎት በአምላካዊው ብርታት ክንውን ያገኛል፡፡Christ’ sObject Lessons, p. 333.ChSAmh 358.4

    እየጠፉ ላሉ ነፍሳት የምንሠራው ሥራ የመላእክትን ትብብር ያገኛል፡፡ ሰዎች ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተዘጋጅተው ይገኙ ዘንድ፤ ሺv ጊዜ ሺvአሥር ሺህ ጊዜ አሥር ሺህ የሚሆኑ መላእክት እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠውን ብርሃን በማስተላለፍ ከቤተ hርስቲያን አባላቶቻችን ጋር ለመተባበር በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 129. ChSAmh 359.1

    መላው የሰማይ መላእክት ከእኛ ጋር በተባባሪነት ለመሥራት ዝግጁ ናቸው፡፡ ሰማያዊው የተትረፈረፈ ጸጋ የጠፉትን ለማዳን በሚጥሩ ወገኖች ትእዛዝ ስር ይገኛል፡፡ ለከበሩት ነገሮች እጅግ ግዴለሽና ልባቸው የደነደነ ነፍሳት ጋር መድረስ ይችሉ ዘንድ የመላእክት እገዛ ከእርሶ ጋር ነው፡፡ አንድ ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ሲመለስ መላው ሰማይ ሐሴት ያደርጋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል በወርቃማ የበገና አውታሮቻቸው እግዚአብሔርና በጉ ለሰው ልጆች ስላሳዩት ምኅረትና በፍቅር የተሞላ ደግነት የምስጋና ዝማሬ ያቀርባሉ፡፡Christ’s Object lessons, p. 197.ChSAmh 359.2

    የገሊላን ዓሣ አጥማጆች የጠራው አምላክ አሁንም ሰዎችን ለአገልግሎት ይጠራል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በእኛ አማካይነት >ይሉን ለመግለጽ ፈቃደኛ ነው፡፡ ጉድለት ያለብንና ኃጢአተኞችም ብንሆን አምላክ ለሥራ ተባባሪነት ማለትም ከክርስቶስ እየተማርን እንድንለማድ ይጋብዘናል፡፡ በመለኮት አመራር ሥር ሆነን ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ያድመናል፡፡The Desire of Ages, p. 297.ChSAmh 359.3

    ክርስቶስ ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ለእርሱ ቀድሰው ለሚኖሩ ዋጋ እንደሚሰጥ ልብ አላሉ ይሆን? እንደ ተወዳጁ ዮሐንስ ስለ ስሙ ከባድ የሰማዕትነት ጽዋ ከሚጎነጩና በፈታኛ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ጋር አብሮ እንደሚሆን አላስተዋሉም? እርሱ ከታማኞቹ ጋር እየተገናኘና መንፈሳዊ አንድነት እየፈጠረ - ያበረታታቸዋል፣ ያጠነክራቸዋልም፡፡ ከሰብዓዊው ፍጡር ከፍ ብለው የተፈጠሩት መላእክት ለሰብዓዊው ፍጡር እንግዳ የሆኑ እውነቶችን በመናገር ሠራተኞቹን እዲያገለግሉ በእግዚአብሔር ይላካሉ፡፡ Testimonies, vol. 8, p. 17.ChSAmh 359.4

    መላው ሰማይ በእንቅስቃሴ የተሞላ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ክርሰቶስ የሞተላቸው ነፍሳት አስደሳቹን የመዳን የምስራች እንዲሰሙ ዕቅድ ነድፈው ከሚንቀሳቀሱ ጋር ተባባሪ ሆነው ለሥራት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ነፍሳት የደኀንነት ወራሾች እንዲሆኑ አገልግሎት የሚሰጡ መላእክት ለእያንዳንዱ እውነተኛ ሠራተኛ እንዲህ ይላሉ“እናንተ የምትሠሩት ሥራ ይህ ነው” “ሂዱ…..የዚህንም ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ ንገሩ” (ሐዋ. 5፡20)፡፡ መልእክቱ የተነገራቸው ትዕዛዙን ለመፈጸም ፈቃደኞች ከሆኑ ጌታ ለአገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟልቶና አመቻችቶ የሚሄዱበትን መንገድ ይጠርግላቸዋል፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 433, 434.ChSAmh 360.1

    በዚህ ዘመን እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ሌሎችን ለመርዳት በንቃት በአገልግሎት መሳተፍ ይኖርበታል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማስተዋል ያላቸው ሰዎች ብርሃንን እየናፈቁ ወደሚገኙ ወንዶችና ሴቶች ለመድረስ የሚያሳዩት መሻት የእግዚአብሔር መላእክትን ድጋፍና አብሮነት ያገኛል፡፡ አገልግሎታችን የመላእክትን አብሮነት ሲያኝ ማንም ወደ ፊት ለመንቀሳቀስ አይፈራም፡፡ ራሳቸውን ለአገልግሎት ቀድሰው የሰጡ ታማኞችን የአገልግሎት ጥረት ተከትሎ ብዙዎች ከጣኦት አምልኮ ሕያው አምላhን ወደ ማምለክ ይለወጣሉ፡፡ ኢያሌዎች በሰው ለተቋቋሙ ተቋማት አክብሮት መስጠታቸውን አቁመው ያለ ፍርሐት ከእግዚአብሔርና ከሕጉ ን ይሰለፋሉ፡፡Prophets and Kings, p. 171. ChSAmh 360.2

    የእግዚአብሔር አገልጋዮች ተስፋ አስቆራጭ በሚመስል ሁናቴ ውስጥ እያደረጉ ያሉትን ተጋድሎ በሰማያዊ ስፍራ ያሉ አለቆችና ባለሥልጣናት በአንhሮ እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ክርስቲያኖች መልካሙን የእምነት ገድል እየተጋደሉ የአዳኛቸውን አርማ አንግበው ሲገሰግሱየአዳዲስ ድሎችና ምርኮዎች ባለቤት እየሆኑ ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክብሮችና ማዕረጎች ይጎናጸፋሉ፡፡ ሁሉም የሰማይ መላእክት ለትሁቶቹና አማኞቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የጌታ ሠራተኞች በምድር የውዳሴ መዝሙር ሲያቀርቡ—የሰማይ መዘምራን ተቀላቅለዋቸው ለእግዚአብሔርና ለልጁ በአንድነት የምስጋና ዜማ ያሰማሉ፡፡The Acts of the Apostles, p. 154.ChSAmh 361.1

    አገልግሎቱን ስኬታማ የሚያደርገውና ወደ ፍጽምና የሚያመጣው ከሰብዓዊው ፍጡር የሚመነጭ ኃይል ሳይሆን የሰማይ _ ሰራዊት ከሰብዓዊው መኪል ጋር ጥምረት ፈጥረው የሚሠሩት እንከን የለሽ ሥራ ነው፡፡ ጳውሎስ ሊተክል፣ አጵሎስ ደግሞ ውሃ ሊያጠጣ ቢችልም የሚያሳድገው ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ ድርሻ ማከናወን አይችልም፡፡ ሆኖም የእርሱን ታላቅሠራተኛነት በማስተዋል እንደ ሰብዓዊ ወኪልነቱ ከመለኮት ብልህ ኃይላት ጋር ተባብሮ በቅንነትና በትህትና ምርጥ የሆነውን የግል ድርሻውን ማበርከት ይችላል፡፡ ምናልባት አገልጋዩ ቢያልፍ፤ ሥራው ወደ ፍጽምና ያመራል እንጂ አይቆምም፡፡ Review and Herald, Nov. 14, 1893. ChSAmh 361.2

    ማንኛውም ክርስቲያን ሁል ጊዜ ከጌታ የሚያገኘው እርዳታ አለ፡፡ ጌታ እኛን ሊረዳ የሚችልበትን መንገድ ላናውቅ ብንችልም— እርሱ ላይ የተማመኑትን እንደማይጥል ግን እናውቃለን፡፡ በሚያጉረመርሙና በሚያማርሩ ወገኖች ላይ ያነጣጠረው የጠላት ዓላማ ስኬት እንዳያገኝ ጌታ ስንት ጊዜ መንገዳቸውን በተደጋጋሚ እንዳስተካከለ ክርስቲያኖች በጥልቅ ያስተውሉ ይሆን? በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ተጠብቆ ሲቆይ የትኛውም ዓይነት ፈተና በእነርሱ ላይ ሥልጣን አይኖረውም፡፡ እግዚአብሔርን የጥበብና የብርታታቸው ምንጭ አድርገው ሲቆጥሩ የhርስቲያን አልግሉት በእነርሱ ውስጥ hንውን እንዲያገኝ የተመኘው ሥራ ፍጻሜ ያገኛል፡፡ Prophets and Kings, p. 576. ChSAmh 361.3

    የወንጌል ሥራ ተካፋዮች ሁሉ የእግዚአብሔር ረዳት እጆች ናቸው፡፡ መላእክት ተልዕኮአቸውን እንዲያከናውኑ አብሮነታቸውን የሚያሳዩአቸው ሰብዓዊ ወኪሎች፤ የመላእክት የሥራ ባልደረቦች ናቸው፡፡ መላእክት በድምፅ እየተነጋገሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ፡፡ ከሰማይ ወኪሎች ጋር ተባብረው የሚሠሩ ሰብዓዊ ፍጡራን የእነርሱ ዕውቀትና ተሞክሮ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡Education, p. 271.ChSAmh 362.1

    እያንዳንዱ ወንድና ሴት የጽድቅ የጦር ልብሱን ለብሶ ወደ ሥራ እንዲገባ ክርስቶስ ጥሪ ያቀርባል፡፡ እግዚአብሔር “እረዳሃለሁ..ቀኝ እጅህን እይዝሃለሁና” በማለት ይናገራል፡፡ ማንኛውንም የደረሰቦትን ፈተናም ሆነ ውስብስብ ችግር ለእርሱ ለአምላhዎ ይንገሩ፡፡ በእርሱ ላይ ያሎትን መተማመን በፍጹም መና አያስቀረውም፡፡ በደሙ የገዛት ቤተ ክርስቲያን አባላት ስለ የሱስ እያሰቡ... የእውነትን ዘር ለመዝራት ሲወጡ የማየትን ያvል Aክርስቶስ የከበረ ነገር የለም፡፡ ጌታ በብቸኝነት ሁናቴ ውስጥ ሳይሆን ነገር ግን ፈቃዱን ለመፈጸም በሚጠባበቁ አሥር ሺህ ጊዜ አሥር ሺህ የሰማይ መላእክት ተከብቦ ይገኛል፡፡ መተማኑን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ወደ ሚያደርገው ደካማ ቅዱስ ሄደው አገልግሎት እንዲሰጡ ያዛቸዋል፡፡ በከፍታ ወይም በዝቅታ ለሚኖሩ፣ ለሐብታሞች ወይም ለድኾች--ለሁሉም ተመሳሳይ የእርዳታ እጅ ተዘርግቶአል፡፡Southern Watchman, Nov. 7, 1905.ChSAmh 362.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents