Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 18—የወንጌል ጉባዔ

    የክርስትና አገልግሎት ድጋፍ ሰጭ መርኀ ግብር

    የወንጌል ጉባዔ ማካሄድ የተሰጠንን ሥራ ከዳር ከምናደርስባቸው ጠቃሚ መንገዶች መሃል አንዱ ነው፡፡ የሕዝቦችን ትኩረት መማረክ የሚያስችለን እጅግ ውጤታማ ዘዴ ነው፡— Testimonies, vol. 6, p. 31.ChSAmh 269.1

    የባዕድ ወሰኖችንና ጠባብነትን ጥሰን በማለፍ ለሕዝቡ እጅግ ዋጋ ያለውን፣ የከበረውን እውነት እንዴት ማቅረብ እንደሚኖርብን ባለማወቃችን ግራ መጋባትና መደናገር ይታይብን ነበር፡፡ ይህን ሥራ ከፍጻሜ ለማድረስ የወንጌል ጉባዔ አንዱና እጅግ አስፈላጊው መሣሪያ መሆኑን ጌታ አስተምሮናል፡፡Testimonies, vol, 6, pp. 31, 32.ChSAmh 269.2

    ዓላማ፡ በአንድ ላይ የመሰባሰብ ዓላማ ምንድን ነው? ሁላችን በአንድ ላይ በጸሎት እየተጋን መሆኑን ለእግዚአብሔር መንገሪያ መንገድ ነው? በአንድ ላይ ስንሰባሰብ አንዱ ለሌላው አስተሳሰቡንና ስሜቱን በማካፈል ያነቃቃዋል፡፡ አባላት ይበረታታሉ፣ የብርሐን ጨረሮች ይፈነጥቃሉ፣ አንዱ ከሌላው ጋር የሚፈጥረው ትውውቅ ብሩህ ተስፋና ምኞት እንዲበረታታ ያደርጋል፡፡ ጽኑውና ከልባችን በእምነት የምንጸልየው ጸሎት ከብርታት ምንጫችን መታደስና ጥንካሬ ያስገኝልናል፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 578...ChSAmh 269.3

    የወንጌል ጉባዔያችን ሌላም ዓላማ አለው. . በሕዝባችን መካከል መንፈሳዊ ህይወት እንዲበረታታ ያደርጋል … እግዚአብሔር እጅግ የተቀደሰውን ሥራ እጃችን ላይ አኑሮአል፡፡ ለዚህ ሥራ ገጣሚ ሆነን ክንውን እንድናገኝ አምላካዊውን መመሪያ ለመቀበል በአንድ ላይ መሳሰብ ይኖርብናል፡፡ አምላካዊውን ቅዱስ ሕግ ለዓለም በማሳየቱ ረገድ እያንዳንዳችን የተጠራንበትን የአገልግሎት ዘርፍ በማስተዋል “እነሆ! የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፡29) እያልን አዳኙን ከፍ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በአገር ቤት የምንሠራውን ሥራ ማስተዋል እንችል ዘንድ በአንድ ላይ ተሰባስበን መለኮታዊውን መነካት መቀበል ያሻናል፡፡Testimonies, vol 6, pp. 32, 33. ChSAmh 270.1

    በአግባቡ የሚሰራጭ የወንጌል ጉባዔመጋቢዎች ሽማግሌዎችና ዲያቆኖች ለአዳኙ የላቀ ፍጹም ሥራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ዕውቀት የሚያገኙበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ የወንጌል ጉባዔ አማኞች ሊረዳቸው የሚችለውን ትምህርት ቀስመው ሌሎችን የሚረዱበት ስፍራ እንደመሆኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌ የቤተ ክርስቲያን አባላት የጌታን መንገድ ይበልጥ በተሻለ መንገድ መማር የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥራል፡፡— Testimonies, vol. 6, p. 49.ChSAmh 270.2

    ባለፉት ዓመታት ባደረግናቸው የወንጌል ጉባዔዎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች እነዚህን ያሌ የከበሩ ዕድሎች ተጠቅመው ሕዝባችንን ማስተማር የሚችሉባቸውን መንገዶች ማዳበር ችለዋል፡፡ የሦስቱን መላእክት መልእክት እውነት እንዴት በተጨባጭ ለሐዝባችን ብሎም ለጓደኞቻቸውና ለሚያውቋቸው ሁሉ ማቅረብ እንደሚችሉ ትምህርት አግኝተውበታል፡፡ ሰዎች በማኅበረሰባቸው መሃል እያሉ የወንጌላዊ አገልግሎት በመስጠት ራሳቸውን ችለው መኖር የሚያስችላቸውን ትምህርት አግኝተዋል፡፡ ብዙዎች በዓመት አንዴ የሚደረገውን የወንጌል ጉባዔ ከተካፈሉ በኋላ ከቀድሞው በላቀ ቅንአትና ዕውቀት ለመሥራት የሚያስችላቸውን መነሳሳት አግኝተዋል፡፡ በወንጌል ጉባዔ ተካፋይ ለሚሆኑ የቤተ ክርስቲያን አባላት ከዚህ ቀደም በተለምዶ ይሰጥ ከነበረው ጠለቅ ያለ ተጨባጭ መመሪያ መስጠት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፡፡ በዓመት አንድ ጊዜ የምናካሂደው የወንጌል ጉባዔ ዓላማ ሁሉም ሰው ወንጌልን ማዳረስ የሚችልበትን ዕውቀት የሚያገኝበት ተጨባጭ ዘዴ መሆኑን ከጀነራል ኮንፈረንስ አንስቶ እያንዳንዱ ሠራተኛም ሆነ ወንድምና እህት ሊያስታውስ ይገባል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 81. ChSAmh 270.3

    አንዳንድ የኮንፈረንሶቻችን መሪዎች እነዚህን ተጨባጭ ዘዴዎች የያዙ መመሪያዎች ለማስተዋወቅ ሲያመነቱ ተስተውለዋል፡፡ አንዳንዶች ከማስተማር ይልቅ ለመስበክ ያዘነበለ ተፈጥሮ አላቸው፡፡ አማኞች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የወንጌላዊን ሥራ እንዴት በተጨባጭ መሥራት እንደሚችሉ ትምህርት መስጠት የምንችልበትን ዓመታዊውን የወንጌል ጉባዔ መርጎ ግብር ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 82.ChSAmh 271.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents